25/05/2022
"ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንዲራ ውጪ በት/ቤታችን ውስጥ አይሰቀል " የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች
አዲስ አበባ ቃሊቲ ገላን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተፈጠረው ምንድን ነው?
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን for more information join our telegram channel
( t.me//NATIONALEXAMSRESULT )
ባሳለፍነው ሳምንት የገላን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦሮምያ ክልል ባንዲራ እንዲሰቀል እና የክልሉ መዝሙርም እንዲዘመር ይታዘዛል። ይሁንና ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር እና ባንዲራ ውጪ አንዘምርም አንሰቅልምም በሚል ቅሬታቸውን ያሰማሉ።
ከትናንት ወዲያ ሰኞ ዕለት ደግሞ ጠዋት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ከተዘመረ እና ብሔራዊ ባንዲራ ከተሰቀለ በኋላ የኦሮምያ ክልል ባንዲራ ሊሰቀል እና የክልሉ መዝሙር ሊዘመር ሲል ተማሪዎች ወደክፍል መግባት ይጀምራሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና አንዳንድ መምህራን በግዴታ ካልዘመራችሁ ባንዲራውንም
ካልሰቀላችሁ ብለው ተማሪዎችን ማስገደድ ሲጀምሩ ተማሪዎች ይህንን ሳይቀበሉ ቀርተው ወደ ክፍላቸው ይገባሉ። ትናንትናም እንዲሁ ይቀጥላል።
ዛሬ ጠዋት ግን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቁጥራቸው ብዙ የሚሆኑ በከፊል የታጠቁ ፖሊሶችን በጊቢው ውስጥ እና አካባቢ በማሰማራት በግዴታ ሊያስዘምራቸው በመሞከሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማሰማት ይጀምራሉ። ኃይል በመጠቀም ለማስገደድ የሞከሩ መምህራንም ነበሩ።
የተማሪዎቹን ጩኸት የሰማው የአካባቢው ኅብረተሰብ እና ወላጆችም በመደናገጥ ወደ ትምህርት ቤቱ ያመራሉ። ተማሪዎችም በዚህ ሁኔታ መማር እንችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን ሁኔታው ሳይባባስ ወደቤት ተበትነዋል።
ተጨማሪ መረጃ አጣርተን እናደርሳለን
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
For more info. Join us on Telegram
t.me//NATIONALEXAMSRESULT