08/09/2020
በአጠገባችን በአሉ ነገሮች ራሳችንን ማከም
በዓለም ላይ 66 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ባህላዊ መድኃኒቶችን ከበሽታ ራሱን ለማዳንና ሕመምን ለማስታገስ ይጠቀማል፡፡ በአገራችን ለረጅም ዓመታት በአያት በቅድማያቶቻችን ተፈትነው ውጤት ያመጡና ዛሬም ቢሆን አብዛኛው ሕዝባችን የሚጠቀምባቸው ከአካባቢያችን በቀላሉ የምናገኛቸውን መድኃኒተ ሕጸዋት እናስተዋውቃችሁ፡፡
1.ዝንጅብል ወቅጦ ውሃ ውስጥ ጨምሮ በማፍላት መጠጣት ለጉንፋንና ለቶንሲል ፍትሁን መድኃኒት ነው፡፡ እንዲሁም ለሆድ መንፋት አንድ ፍንካች ዝንጅብልና አንድ ቁንጥር ጨው በአንድ ላይ አኝኮ በመዋጥ ይጠፋል፡፡
2. ሁለት ሁለት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ተፈጭቶ በወተት በቀነ ሦስት ጊዜ መዋጥ እና ጦስኝ እንደ ሻይ ተፈልቶ በየለቱ መጠጣት ወይም እንዲሁም የግብጦ አረቄ በየዕለቱ በአነስተኛ መጠን መጠጠታት የደም ግፊትን ለመቆጣጠርና ለመቀነስ ይረዳል፡፡
3. ጤና አዳም አኝኮ መዋጥ ወይም ማሽተት ለሆድ ቁርጠት ወይም ለልብ ድካም እጅግ ጠቃሚ መድኃኒት ነው፡፡
4. የዱባ ፍሬ መብላት ለኮሶና ለስኳር ሕመም ወሳኝ መድኃኒት ነው፡፡
5. ነጩን የእንቁላል ክፍል አድቅቆ ለጨቅላ ሕፃን ማጠጣት ተቅማጡ ቶሎ እንዲቆምለት ይረዳል፡፡
6. የግራዋ ቅጠል ቅጠሉ ተቀንጥሶ በውሃ በማፍላት በላዩ ላይ ሲቀመጡ የፊንጢጣ ኪንታሮትን ይፈውሳል፡፡
7. የካሞሚል ቅጠል በሻይ መልክ መጠጣት ለሆድ ቁርጠትና ለእንቅልፍ ማጣት ሲበዛ ጠቃሚ ነው፡፡
8. የችፍርግ ስር በወር አበባ ጊዜ ማኘክ ሆድ ቁርጠትን ይፈውሳል፡፡
9. የባሕር ዛፍ ቅጠልና ዳማከሴ ቀቅሎ መታጠን ከጉንፍን ለመላቀቅ የታወቀ መድሃኒት ነው፡፡
10. ሒና ፀጉር ለማቅለምና ራስን ለማቀዝቀዝ፡፡
11. የፓፓያ ስርና ቅጠል በልኩ እየተፈላ ቢጠጣ የወባ በሽታ ያስታግሳል፡፡
12. የሾላ ፍሬ ፍሬው ይሰነጠቅና እንደ ሻይ ተፈልቶ መጠጣት ለአስም ሕመም ጠቃሚ መድኃኒት ነው፡፡
13. ጣዝማ ማር፡- ለአስምና ለደረቅ ሳል ያገለግላል፡፡
14. የቡና ዱቄት፡- ከወለላ ማር ጋር ተደባልቆ ምግብ በልተው ሲያበቁ በማንኪያ መላስ ለአሜባና ለኮሌራ በሽታዎች ያገለግላል፡፡
15. ቀበርቾ ለሆድ ቁርጠትና ለራስ ምታት ያገለግላል፡፡ እየተወቀጠ በትንሽ ስኒ ቢጠጣ ለሆድ ድርቀት ያገለግላል፡፡መጠኑ አንድ ትንሽ ማንኪያ መሆን አለበት፡፡
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!
ምስጋናችን ከልብ ነው!
© Hakim-bet.com