31/03/2026
አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ Sanitary (የንጽህና አጠባበቅ) ዘርፍ ለከተማችን ወጣቶች ያዘጋጀውን የ45 ቀናት አጭር ስልጠና በይፋ ጀምሯል!
የኮሌጁ ምክትል ዲን ከፍተኛ ኢንስትራክተር አለምነው ዋኘው ዛሬ ስልጠናውን የጀመሩ ሰልጣኞች በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የታገዘ እውቀት በመቅሰም ራሳቸውን ለስራ ዓለም ብቁ የሚያደርጉበት ጉዞ ጀምረዋል ብለዋል። ም/ዲኑ አክለውም ኮሌጃችን ወጣቶች የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለተከታታይ 45 ቀናት ውስጥ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ም/ዲኑ በመጨረሻም የከተማችን ወጣቶች በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል የነገ ህይወታቸውን የሚቀይር ሙያ እንዲጨብጡ መልእክት አስተላልፈዋል ።
አይከል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ