አልዓዛር ንጉሴ ደመቀ ዘ ደብረብርሃን

አልዓዛር ንጉሴ ደመቀ ዘ ደብረብርሃን 🇪🇹ትዕግስት ካለ ሁሉም 🇪🇹
🇪🇹...........ይቻላል!........🇪🇹

የደብረ ብርሃን ከተማ የባህል ቡድን ተቋቁሞ በቦርዱ ጸደቀ፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ደብረ ብርሃንና አካባቢው በኪ...
03/07/2025

የደብረ ብርሃን ከተማ የባህል ቡድን ተቋቁሞ በቦርዱ ጸደቀ፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ደብረ ብርሃንና አካባቢው በኪነጥበብ ዘርፍ የገዘፈ ታሪክ ያለውና የመካከለኛ ዘመን ስልጣኔ መነሻ እንደኾነ አስታውሰዋል፡፡

የዘርፉን ልማት ወደ ነበረበት ከፍታው ለመመለስ የደብረ ብርሃን ከተማ የባህል ቡድን መቋቋሙ ትልቅ የስኬት መጀመሪያ እንደኾነም ነው የተናገሩት።

በቁጭት የባህል ቡድን ለማቋቋም ከታቀደ ዓመታት መቆጠራቸውን አንስተው ዛሬ እውን በመኾኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ለዚህ እንዲበቃ ላስተባበሩና ለሰሩ የባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወደ ስራ ሲገባ ብዙ ተግዳሮቶች እንደሚገጥሙ ታሳቢ በማድረግዳ የችግሩ የመፍትሄ አካል በመኾን የቡድኑ አባላት ሥራቸውን መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክለዮሃንስ በበኩላቸው ከቦርዱ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት ተቋማቸው 27 አባላት ያሉት የደብረ ብርሃን የባህል ቡድን ማደራጀት መቻላቸውን አብራርተዋል፡፡

የባህል ቡድኑን አርቲስት ነፃነት ዘውዴ የሚመሩት ሲሆን ነባርና ዕምቅ አቅም ያላቸው ወጣት ሙያተኞች የተካተቱበት ስለመኾኑም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ ይኾናል ብሎ ከመጠበቅ ይልቅ የሚገጥማቸውን ችግር ተቋቁመው በማለፍ ዓላማቸውን ለማሳካት መዘጋጀት እንዳለባቸው ለቡድኑ አባላት መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ እታፈራሁ ተሰማ ናቸው፡፡

የደብረ ብርሃን አባሳደር መኾናቸውን ተገንዝበው እንቅስቃሴያቸውንና ሥራቸውን በጥንቃቄ እንዲሠሩ መክረዋል።

የባህል ቡድኑ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ የሚመለከታቸው አካለት ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

✍️ሀሙስ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዲስ ክስተት ተፈጥሯል።በወላይታ ሶዶ ከተማ እና በሀምቦ ጠበላ ከተማ በሌሎች አጎራባች ከተሞችም በሰማይ ላይ ምንነቱ ያልታወቀ እሳት ያለው ነገር ታይቷል፡፡ ም...
09/01/2025

✍️ሀሙስ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዲስ ክስተት ተፈጥሯል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ እና በሀምቦ ጠበላ ከተማ በሌሎች አጎራባች ከተሞችም በሰማይ ላይ ምንነቱ ያልታወቀ እሳት ያለው ነገር ታይቷል፡፡ ምናልባት ተወርዋሪ ኮኮብ(metro star) ይሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ክስተቱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በደቡባዊ አሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቦረና ላይ በስፋት እንደተከሰተ ታወቋል፡፡

✍️   ማክሰኞ ታህሳስ 29/2017 ዓ.ምእንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!! በዓሉ የመተሳሰብና የአብሮነት ይሁንልን ፈጣሪ ተወልዶ ለ...
07/01/2025

✍️ ማክሰኞ ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!
በዓሉ የመተሳሰብና የአብሮነት ይሁንልን ፈጣሪ ተወልዶ ለአለም ብርሀን እንዳመጣ ሁሉ ለሀገራችንም የምህረት ብርሀን ያውርድልን!!

🇪🇹   አረፋ(ሰኞ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም)🇪🇹"ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!" 👍አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፦ 'አጼ ምኒልክና ራስ ጎበና አብረው ነው ያደጉት። አብ...
06/01/2025

🇪🇹 አረፋ(ሰኞ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም)🇪🇹
"ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!"
👍አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፦ 'አጼ ምኒልክና ራስ ጎበና አብረው ነው ያደጉት። አብረው ነበሩ፣ ይነጋገሩ ነበር። አሁን እኔና አንተ እንደምንነጋገረው። አጼ ምኒልክ ራስ ጎበናን "ማንም የለም ከጎኔ መጥተህ እርዳኝ" ባሏቸው ግዜ "እኔ ኦሮሞ ነኝ ካንተ ጋር መስራት አልችልም" ብለዋል ራስ ጎበና? አላሉም፡፡ ምኒልክ ከራስ ጎበና ጋር ፈረስ ጉግስ ይጫወቱ ነበር፣ የአጼ ምኒልክን ችግር አዩ፣ ገባቸው። እሽ እከተልሃለሁ አሏቸው። ምን ስራ ትሰጠኛለህ አላሉም፣ "እሽ እከተልሃለሁ ነው" ያሉት፡፡ እሳቸው እንግዲህ አጼ ምኒልክ ሸዋን ይዘዋል፣ ወለጋ፣ ሃረር ከእርሳቸው ኮማንድ ውጭ ነው። ኦሮሞ ግን እንደተበታተነ በየአገሩ ቀረ፣ ይህንን ለማሰባሰብ አጼ ምኒልክ ጎበናን መረጡ። ተስማሙ አብረው መጡ፣ ወደ አዲስ አበባ፡፡ 'ይገለኛል፣ ይጠላኛል' ለምን አልተባባሉም? እንደዛሬው ልዩነት አለን ብለው አላሰቡም፡፡ "አንድ አገር ነን" ብለው ነው ያሰቡት፡፡ ልዩ ልዩ አገርም አለን ብለው አላሰቡም። ጎበናም ምንም ሳይጠይቁ ከእርሳቸው ጋር ገቡ አብረው በሉ ጠጡ ተጋቡ፡፡ ይህንን ነው የማውቀው። ሁለቱም አይፈራሩም አብረው ነው ለዘመናት የኖሩት። ተጋብተው ተዋልደዋል።"

❓ሸገር ታይምስ፡- አጼ ምኒልክን ለኦሮሞ የተለየ ጥላቻ አንዳላቸው አድርገው የሚያነሱ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ነገር እንዴት ያዩታል?

👍አቶ ቡልቻ፡- 'በፍጹም ዳግማዊ ምኒልክ ለኦሮሞ ጥላቻ የላቸውም። "አሮሞ የሚባል ስም አልወድም እገላቸዋለሁ፣ ወላይታን አልወድም እፈጃቸዋለሁ፣ አደሬን አልወድም...." ብለው አንድን ህዝብ መርጠው ጠላቴ ነው ብለው አያውቁም፡፡ አስበውትም አያውቁም። አገር እንዲሰለጥን፣ ህዝብ ሁሉ እንዲሰለጥን ነው የተቻላቸውን ሁሉ ያደረጉት። ለአንድ ህዝብ የተለየ ጥላቻ ኖሯቸው ይህንን ህዝብ እንውጋው ብለው ይነጋገራሉ ብዬ መገመት እንኳን አልችልም፡፡ እሳቸው ለአገራቸው ስልጣኔ ነው የለፉት፤ ማንንም አይጠሉም ነበር።'

04/01/2025

ሰው መሆን ምንድ ነው❓

ክቡር ዶ/ር አርቲስት  🇪🇹ቆሜ ልመርቅሽ🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቆሜ ልመርቅሽ ተቀበይኝ እማ ሕይወትን መርቀሽ ሰጥተሽኝ እኔማይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም፣ኢትዮጵያ ዕ...
03/01/2025

ክቡር ዶ/ር አርቲስት 🇪🇹ቆሜ ልመርቅሽ🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቆሜ ልመርቅሽ ተቀበይኝ እማ
ሕይወትን መርቀሽ ሰጥተሽኝ እኔማ
ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም፣
ኢትዮጵያ ዕድሜ ላንቺ ያላየሁት የለም።

አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና።

ትንቢትሽ ይፈፀም ከመሬት ጠብ አይበል፣
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ገድልሽ ይንበልበል፤

ሰንደቅሽ ከፍ ይበል ይቁም ለዘላለም፣
ሰላም፣ ጥጋብ፣ ደስታ፣ ይታይብሽ ዓለም።

ሴራው ይክሸፍበት የመታብሽ አድማ፣
እጁን ሣር ያድርገው ጉልበቱን ቄጤማ፤

ካቀባበለብሽ ብረት ከደገነ
አምላክ ያግዝልሽ ላንቺ የወገነ፤

ፀሎትሽ ይሰማ አምላክ ይለመንሽ፣
ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ፤

አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና፤

በሰው ሀገር ምድር ለተበተኑት፣
ለልጆችሽ ሁኚ ዞሮ መግቢያ ቤት፤

በዓለም አደባባይ ከመንግሥታት ደጅ
ሞልቶሽ ተርፎሽ እንጂ ጎድሎብሽ አትሂጅ፤

ጎተራሽ አይጉደል አይድረቅ ሌማትሽ
ከክፉ ሰውሮ ያድንሽ እምነትሽ፤

ላንቺ የማይተኙ የማያንቀላፉ፣
ብን ይበሉ እንደጉም ከምድረ ገጽ ይጥፉ፤

ካረግንልሽ በላይ የምትሆኝልን፣
መጠሪያ እናታችን አንቺው ቆዪልን !!!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹ግጥም ፦ ያይራድ አላምረው
🇪🇹ዜማ፦ ሞገስ ተካ
🇪🇹ቅንብር፦አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ

01/01/2025

ተማሪ ቁጭ ብሎ መምህር የቆመው፣
አትደናገሩ ሁሉም በጊዜ ነው ሁሉም ቦታ እኮ አለው።

  የከርሞ ሰው በይንሰኞ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም
29/12/2024

የከርሞ ሰው በይን
ሰኞ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም

Address

Dabra-Berhan

Telephone

+251116811099

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አልዓዛር ንጉሴ ደመቀ ዘ ደብረብርሃን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share