DTU College of Health sciences.

DTU College of Health sciences. Debre Tabor University College of Health Sciences has introduced “Innovative Curriculum” since its foundation.

An innovat curriculum is for problem-solving, creativity and imagination. Its approach is student-centered making the learner the major player

29/05/2026
የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅት ስልጠና ሰጠ​ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለዳግማዊ ...
28/05/2026

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅት ስልጠና ሰጠ

​ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.

​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ትምህርት ዘመን የሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅትና ማጠናከሪያ ስልጠና ሰጠ።

​ስልጠናው በዋናነት ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚገጥማቸውን ፍርሃትና ጭንቀት በማስወገድ፣ በራስ መተማመናቸውን እንዲጨምሩና ያላቸውን እውቀት በሙሉ አቅማቸው ተጠቅመው ለላቀ ውጤት እንዲበቁ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እያደረገ ስላለው ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አምሳሉ በለጠ እንደገለጹት፤ ተማሪዎች በተለይም በፈተና ወቅት የሚከሰትባቸውን ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና መቋቋም የሚያስችላቸውን አቅም ማጎልበት ይኖርባቸዋል። አያይዘውም «ጭንቀትና መረበሽ የተሞላበት አዕምሮ እምቅ አቅምን ስለሚገታ፣ ተማሪዎች ራሳቸውን በማረጋጋት ለጥሩ ውጤት መዘጋጀት አለባቸው» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​በመስኩ ምሁራን እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ላይ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑት ተማሪዎቻችን ከቀሰሙት እውቀትና ክህሎት ባሻገር፣ የፈተና ስነ-ልቦና ዝግጅታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉባቸው በርካታ ጠቃሚ ነጥቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

​የጤና ሳይንስ ኮሌጁ መሰል ማህበረሰብ አቀፍ የስነ-ልቦና ድጋፍ ስልጠናዎችን ለአካባቢው ተማሪዎች በዓመቱ ውስጥ በተያያዥነት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

📖​Debre Tabor University has a Historical Duty to Answer Tewodros’s Quest for Knowledge!

👉 Telegram=https://t.me/DTUniversity

28/04/2026

⏰ Upcoming Event:

⏰ 1 Day left !!

5th Annual National Research Conference

​Debre Tabor University is honored to host its 5th Annual National Research Conference, a platform dedicated to bridging the gap between academic research and sustainable societal growth. Under the inspiring motto, "Debre Tabor University Has a Historical Duty to Answer Tewodros’s Quest for Knowledge!", DTU invites you to join this prestigious gathering.

​📜 Grand Theme

​"Research, Technology Transfer, Community Engagement, and Culture for Sustainable Development"

​📍 Event Information
​Date: April 30 – May 05, 2026 (Miazia 22 – 27, 2018 E.C.)
​Venue: Aleqa Tekile Gebrehana Hall
​Host: Debre Tabor University

​💡 Why Attend?

​This conference serves as a vital hub for:

📖​Innovation: Exploring the latest in technology transfer and scientific advancements.

📖​Culture: Integrating traditional values and cultural heritage into modern development.
​Impact: Strengthening the bond between the university and the community through actionable research.

📖​DTU looks forward to welcoming researchers, students, and community leaders as It fulfills its' historical duty to advance knowledge and development.

​Debre Tabor University

Dear Researchers,We are honored to invite you to submit your scholarly work to the Journal of Interdisciplinary Science ...
22/04/2026

Dear Researchers,
We are honored to invite you to submit your scholarly work to the Journal of Interdisciplinary Science and Technology (JIST).
We welcome submissions of original articles, review papers/meta-analyses, and case reports across a wide range of disciplines, including:
• Medicine and Health Sciences
• Agriculture
• Engineering and Technology
• Social Sciences
• Humanities
• Business & Economics (FBE)
• Law
• Natural Sciences
• 📌 Submission Link: https://www.dtujist.com/index.php/jist/about/submissions

Sincerely,

The Journal of Interdisciplinary Sciences and Technology (JIST) publish original contributions in both basic and applied research across medicine and health sciences, social sciences, natural sciences, engineering, and agriculture.

🌿 የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የትንሣኤ በዓልን ከመምህራኖቻቸው ጋር በድምቀት አከበሩ ።
13/04/2026

🌿 የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የትንሣኤ በዓልን ከመምህራኖቻቸው ጋር በድምቀት አከበሩ ።

የትንሳኤ በዓል በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በድምቀት ተከበረ​የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ የሥነ-አእምሮና...
12/04/2026

የትንሳኤ በዓል በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በድምቀት ተከበረ

​የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ የሥነ-አእምሮና የሱስ ታካሚዎችን ለማበረታታት የታለመ የጋራ የምሳ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

በዝግጅቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የደብረ ታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮችና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደብረ ታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅና የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ገብሬ ድንቃየሁ፤ መሰል የሱስ ማገገሚያ ተቋማት በሀገራችን ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለወደፊቱም ተቋማቱ እንዲስፋፉና በማዕከሉ የሚገኙ ታካሚዎች በፍጥነት አገግመው ለቤተሰባቸውና ለሀገራቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ በለጠ በበኩላቸው፤ ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

​ምስጋና ለባለቅን ልቦች

የተሃድሶ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጌታሰው ለጋስ በመርሃ-ግብሩ ላይ ለተገኙ አካላትና ተቋሙን በውጭ ሀገር ሆነው ለሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም ለበዓሉ መርሃ-ግብር መሳካት በምዕራብ አውስትራሊያ ፐርዝ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ፋሲካ አዳነ
አቶ እንዳልክ ታደሰ እና አቶ አማኑኤል ጋሻው ላደረጉት የላቀ ድጋፍ ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።

ባለቤታቸውን ለማሳከም በማዕከሉ የሚገኙ አንድ አባወራ በሰጡት አስተያየት፤ በዓልን ከቤተሰብ ርቆ ማክበር የሚፈጥረውን የብቸኝነት ስሜት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች አብረዋቸው በመሆኑ እንደረሱት ገልጸዋል። "ከገዛ ቤተሰቦቻችሁ ይልቅ እኛን አስቀድማችሁ አብራችሁን ስላከበራችሁ እናመሰግናለን" ሲሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አጋርተዋል።

Celebrating Excellence: From DTU to the Global Stage!We are excited to share some monumental news! We proudly congratula...
23/03/2026

Celebrating Excellence:

From DTU to the Global Stage!

We are excited to share some monumental news! We proudly congratulate our esteemed alumni, Dr. Saron and Dr. Betenas, on successfully matching into residency programs in the United States. 🇺🇸🩺

As former students of the Debre Tabor University College of Health Sciences, their achievements reflect the world-class education provided at our institution. This milestone is a testament to their relentless hard work, unwavering dedication, and perseverance.

Please join us in wishing them continued success as they embark on this prestigious new chapter in their medical careers.

You have made the DTU family incredibly proud!

Congratulations on your promotion!Your dedication, hard work, and passion for teaching andresearch have truly paid off. ...
20/03/2026

Congratulations on your promotion!

Your dedication, hard work, and passion for teaching andresearch have truly paid off.

This achievement is a testament to yourcommitment to academic excellence and your impact on students and colleaguesalike.

Wishing you continued success in your career and many moremilestones ahead!

Best regards,

Tabor University

14/03/2026
በታሪክ ማህደር የማይደበዝዙት የፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ አሻራዎች!"ሃገር የሚለወጠው በትምህርት ነው" በሚለው ጽኑ እምነታቸው፣ ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (መካነ-አዕምሮ) እድገትና ለሃገራችን ...
10/03/2026

በታሪክ ማህደር የማይደበዝዙት የፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ አሻራዎች!

"ሃገር የሚለወጠው በትምህርት ነው" በሚለው ጽኑ እምነታቸው፣ ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (መካነ-አዕምሮ) እድገትና ለሃገራችን የጤና ትምህርት ስርአት መዘመን ህይወታቸውን ሙሉ የከፈሉ ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ ካረፉ ዛሬ 7ኛ ዓመታቸውን ደፍነዋል።

ይሁን እንጂ የፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ በተለይ ክዚህ በታች በተጠቀሱት አበርክቷዋቸው ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡

ፕሮፌሰሩ ጉና ተራራ ስር ከምትገኝ ሣህርና ማርያም ቀበሌ ተነስተው፣ በከፍተኛ ጽናት እስከ እንግሊዝ ሊድስ ዩኒቨርሲቲ በመዝለቅ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን የተቀዳጁ ጽኑና ብርቱ ባልሞያ ነበሩ።

በሃገራችን የትምህርት ስርዓት በተለይም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ሳይንስና ሞያ (Public Health Science and Profession)ና ማህበርሰብ አቀፍ (Community based Education) የትምህርት ካሪኩለምን ለመጀመሪያ ጊዜ በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። በዚህም አስተዋጽዖቸውም በቀድሞ የሞያ ጉዋደኞቻችውና ተማሪዋቻችውና "የኢትዮጵያ የየህብረተሰብ ጤና ሞያ" አባት ይባላሉ፡፡

🎓 የትምህርት ጉዞ
ፕሮፌሰሩ ለዘመናዊ ትምህርት በነበራቸው ልዩ ፍቅር ርቀቱ ሳይበግራቸው በእግር እየተጓዙ ተምረዋል። የትምህርት ታሪካቸውም የሚከተለውን ይመስላል፦
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን፦ በደብረ ታቦር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ፦ ወደ ጎንደር ከተማ በመጓዝ በቀደሞው በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ወይም ባሁኑ አጠራር አጼ ፋሲለደስ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ፦ በቀድሞው በጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአሁኑ የጎንደር ዩኒቨርስቲ በሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ትምህርት ተመርቀዋል።
ከፍተኛ ትምህርት፦ በሀገረ አሜሪካ ከሚገኘው "ቱሌን" (Tulane) ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን፣ማስተርስ ኦፍ ፐበሊክ ሄልዝ (Masters of Public Health)፣ በመቀጠልም ወደ በእንግሊዝ አገር በመዝጓ እዛ ከሚገኘው "ሊድስ" (Leeds) ዩኒቨርሲቲ በኤፒዲሚዮሎጂ የዶክትሬት (PhD) ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውንም የተቀበሉት ከዚሁ ከሊድስ ዩኒቨርሲቲ ነው።

ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ በጅማ ዩኒቨርሲቲ
የትምህርት ህልዮት መተግበር፦

"በትምህርት ረሃብን ማጥፋት ይቻላል" የሚለውን ጽኑ እምነታቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ዓመታት በተግባር አሳይተዋል።በቆየታቸውም አያሌ ተማሪዎችን በማስተማር፤ ችግር ፈቺ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን የቀረጹ፤ ጥናትና ምረምር ያከናወኑና ከፍተኛ በሆነ ወኔ፤ ትጋትና ስነ ምግባር የአካባቢውን ማህበረሰብ አገለግለዋል፡፡ አሻራቸው ዛሬም በዩኒቨረሲቲው ነፍስ ዘርቶ ይታያል፡፡

ስርአተ-ትምህርት ቀረጻ፦ የማህበረሰብ ተኮር ትምህርት ስርአት (Community-based education) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ ስርአተ-ትምህርት እንዲቀረጽ አድርገዋል።በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲጀመርና እንዲሰፋፋ አድርገዋል፡፡ ይሄ ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቁማት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

የተቋም እና የህብረተሰብ ትስስር፦

ዩኒቨርሲቲው ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራና የህዝቡን ችግር እንዲፈታ ብርሃን የፈነጠቁ መሪ ነበሩ።

ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

በተመሳሳይም ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ብዙ የማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ተማሪዎችን በማስተማርና በማማከር አገልግለዋል፡፡

ፕሮፌሰር በተለይም የጤና ትምህርት አሰጣጥ ትምህርትን [pedagogy] በማስተማር ይታወቃሉ ፤ ይታወሳሉ፡፡ ለዚህም አገልግሎታቸው እኤአ በ2018 ከ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልመዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ

ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከተሉትን አምስት የትምህርት ካሪኩለሞች ላይ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ተሳትፈዋል፤ አነዚህም
👉አንደኛ ማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ (MPH)
👉ሁለተኛ ማስተርስ ኦፍ ሳይንስ (MSc)
👉ሶስተኛ ዶክተር ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ፤ ይሄ በቅርቡ በኢትዮጵያ ትምህርትና ጤና ሚኒሰቴር ጸድቆ በሀረማያ ዩኒቨረሲቲ ለመጀመርያ ጊዜ በ2018 ዓ.ም ተጀምረዋል፡፡ እና አራተኛ የፐብሊክ ሄልዝ ፒ.ኤች.ዲ (PhD in Public Health) አዘጋጅተው በማቅረባቸው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የወርቅ ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በምጭረሻም የጤና ባለሞያዎች ትምህርት የማሰተረስ ትምህርት [Masters of Health Professionals Education] ካሪኩለምን ቀርጸው፤ በሃገራችን ለመጀመርያ ጊዜ በጂማ ዩኒቨርሲቲ እነዲጀመር አድርገዋል፡፡ በዚህም ብዙ ባለሞያዎችን በማስመረቅ እንደ ሃገር ማፍራት ችለዋል፡፡ አነዚህም ባለሞያዎች የጤና ባለሞያዎች ትምህርት አንዲሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ ለደብረ ታቦር
ዩኒቨርሲቲ እና ለአካባቢው ተፈጥሮ የነበራቸው ራዕይ

"አረንጓዴ ዩኒቨርሲቲ" (Green University) በሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ይገለጻል። የዚህ አሻራቸውም
አረንጓዴ ዩኒቨርሲቲ (Green University)
ህልዮት፦ ፕሮፌሰሩ ተቋሙ ንጹህ፣ ኃይል ቆጣቢ እና ለም እንዲሆን "ለምለም መካነ-አዕምሮ" የሚለውን መርህ አንግበው ሰርተዋል ከግብም አድረሰዋል።ይህ አሰራር የትምህርት ጥራትን ቀጣይ በሆነ መልኩ ለማስጠበቅ የሚያስችል "ህያው የስነ-ምህዳር ቤተ-ሙከራ" ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።ፕሮፌሰሩ የተቋሙን የስነ-ምህዳር ህያውነት ለመጠበቅ በመሪነት ተሳትፈዋል፤ አሳትፈዋል።
ፕሮፌሰር መኮንን አሰፋ ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ ያደረጉት አስተዋጽዖ ብዙ ቢሆንም ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መመስረትና መስፋፋት ያደረጉት አስተዋጽዖ ለሰማይ ለምድር የከበደ ግዙፍ ስራ ነው፡፡ መምሀራንን ሜንቶር [Mentor] ማድረግ፡ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት፤ የማብቃት ስልጠና በመስጠትና [ Capacity Building] በማማከር፤የተለያዩ መመሪያዎች እንዲዘጋጁ በማገዝ አንዲሁም የትምህርት ክፍሎች አንዲሰፋፋ በብርቱ ሰርተዋል፡፡ ከዚህም በላይ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አማካሪ ኮሚቴ [ College of Health Sciences Advisory Committee] በማቋቋም እጅግ የላቀ አስተዋጽዖ አበርክተዋል፡፡

ፕሮፌሰር በተለይ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተው ወደ አዲሰ አበባ ከተመለሱ በሁዋላ ሚልኩት የትምህረት ጉብኝት ሪፖርት [ My Report of Educational Visit] እጅግ ተናፋቂ ነበር፡፡

🏔️ የጉና ተራራ

ፕሮፌሰሩ ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ በነበራቸው ልዩ እምነት ለጉና ተራራ ህልውና የሚከተሉትን ተግባራት አከናውነዋል፦

የጉና ተራራ ለአገርና ለአለም ያለው ፋይዳ በተይ የውሃ ማማ ነቱ ጉልህ መሆኑን በማመን፣ ከተለያዩ አካላት ጋር በመወያየትና አውደ ጥናቶችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረዋል።አሳምነዋል በውጤቱም ለተራራው እና ለአካባቢው የመተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀት፣ ጉና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ "ጥብቅ ስፍራ" ሆኖ እንዲከለል ዘወትር የማይዘነጋ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የጉና ተራራ (ከባህር ወለል በላይ 4231 ሜትር ከፍታ ያለው) እና የጣና ሐይቅን በማስተሳሰር የተለያየ መልክዓ ምድርን ያቀፈ የምርምር ማዕከል ጉና ጣና የተቀናጀ የጥናትና ምርምር ማዕከል [GUna Tana
Integrated Field Development and Research Center] እንዲቋቋም አድርገዋል።

📝 የፕሮፌሰር የመጨረሻ ቃል

ፕሮፌሰር እስከ መጨረሻው የህይወት እስትንፋሳቸው ድረስ ከንባብና ከጽሕፈት ሳይለዩ ለተማሪዎቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ያስተላልፉት የነበረው ምክር እንዲህ የሚል ነበር፦

"ሁሌም አንድ ነገር አትርሱ፤ እኔ በሙያዬ ለማህበረሰቡ ምን መስራት አለብኝ? ስትሉ ራሳችሁን ጠይቁ"።

ፕሮፌሰሩ ትምህርት የፍትሃዊነትና የእኩልነት [Justice and Equality] እርካብ መሆኑን፣ ለትምህርት መድከም ደግሞ ለህዝብ መድከም እንደሆነ በጽኑ ያምኑ ነበር።
📖ታሪክ እና ዕውቀት (Quest for Knowledge)
የቴዎድሮስ መንፈስ፦ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ መንደር በሆነው ጋፋት አቅራቢያ መገኘቱ፣ የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥማት የመመለስ ታሪካዊ አደራ እንዳለበት ያምኑ ነበር።

የ"ይቻላል" ተምሳሌት፦ አፄ ቴዎድሮስ በጋፋት "ሴቫስቶፖልን" የሰሩበትን የ"ይቻላል" መንፈስ፣ ዩኒቨርሲቲው ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ እንደ ማዕዘን ድንጋይ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ያስተምሩ ነበር።

የጋፋት ኢንጅነሪንግ ዩኒቨርሲቲ፦ ፕሮፌሰሩ "Gafat University of Engineering (GUE)" የተባለ ተቋም እንዲመሰረት ትልቅ የሞራል እና የታሪክ ግዴታ እንዳለበት አምነው ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ፕሮፌሰሩ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለምንም ክፍያ (በነፃ) ሲያገለግሉ የቆዩ የዩኒቨርሲቲው "አባት" ተብለው የሚጠሩ ሰው ነበሩ።

ፕሮፌሰሩ የዛሬ 7 ዓመት በተወለዱ በ75 ዓመታቸው መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ፕሮፌሰር ዛሬ በህይወት ከኛ ጋራ ቢኖሩ ኖሮ ዛሬ 82 ዓምታቸው ይሆን ነበር ማልት ነው፡፡
ፕሮፌሰር ሞትን በስራቸው ቀድመውት ነበር፡፡

Address

Technique Road
Debre Tabor
272

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DTU College of Health sciences. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share