20/05/2026
።
===============================
ግንቦት 12/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከኢትዩ-ቴሌኮም በገዛውና ወደ ትግበራ ባስገባው Educational Management System (EMS) አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ስልጠና ለአሰልጣኞች መስጠት ጀመረ።
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ም/ዲን አቶ አጅመል መሐመድ እንዳሉት ሲስተሙ በከፍተኛ ወጪ ከኢትዮ-ቴሌኮም የተገዛ እንደሆነና በኮሌጁ ውስጥ እየተተገበረ ለሚገኘው የዲጂታላይዜሽን አሰራር ስርዓትን ለመዘርጋትና ቀልጣፋ የአስተዳደር ስርዓት ለመፍጠር ታስቦ የመጣ መሆኑን አብራርተው፤ ሲስተሙ በአጠቃላይ በኮሌጁ የስልጠና ስርዓት ላይ ከፍተኛ ፋይዳና ሚና ያለው በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም በትጋት እንዲሰሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ስልጠና በዋናነት ትኩረት ያደረገው የሲስተሙ አጠቃቀም ለሁሉም አሰልጣኞች ማሳወቅና ማስገንዘብና በቀጣይ አጠቃላይ አሰራራቸው በዚህ ዘመናዊ ሲስተም መሠረት እንዲከውኑ ለማስቻል ያለመ ነው።
በዚህ ስልጠና ላይ ከሁሉም የት/ት ክፍሎች የተውጣጡ አሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይነት ተደራሽነቱን በማስፋት አሁን የሰለጠኑትን አሰልጣኞች በመጠቀም ለቀሪዎቹ አሰልጣኞች በሙሉ የሚሰጥ ይሆናል።
-----------------------------
!
!
------------------------------
Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!