ዘርማና አርዴ በብልጽግና

ዘርማና አርዴ በብልጽግና ለለውጥ መትጋት!!!

09/07/2021
16/06/2021
15/06/2021

ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ፦ ምርጫ ቦርድ

ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ የሚሰጥበት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል (ከሐረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ቦርዱ አሳስቧል።

ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዝግ እንዲያደርጉም አሳውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት…) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም ተብሏል።

የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አበረታትቷል።

Address

Seba Kuteba
Wolkite

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዘርማና አርዴ በብልጽግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share