24/03/2026
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነገ በዋናው ግቢ በሚገኘው የምረቃ አዳራሽ ደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ያካሂዳል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ድረስ ያሰለጠናቸውን ዕጩ ተመራቂዎች ለምርቃት ያበቃል።
ወድ ተመራቂዎቻችን ለዓመታት በለፋችሁበት የትምህርት ዘርፍ ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ነገ የምትቀበሉት ዲግሪ የድካማችሁ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገራችን ብሩህ ተስፋና ዕውቀት የምታበረክቱበት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው። የወደፊት ጉዟችሁ የጥበብና የውጤት ይሁንላችሁ!
እንኳን ደስ ያላችሁ!
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ/Spring of Wisdom
Arba Minch University will host a grand graduation ceremony tomorrow at the Graduation Hall located on the Main Campus. The university is proud to graduate candidates who have completed their studies across various programs, ranging from Undergraduate degrees to PhDs.
To Our Dear Graduates: Congratulations on reaching this prestigious milestone through years of hard work in your respective fields! The degree you receive tomorrow is not only the fruit of your labor but also the beginning of a new chapter where you will contribute knowledge and hope to our country's bright future.
May your future journey be filled with wisdom and success! Congratulations once again!
Arba Minch University "Spring of Wisdom"