Alpha University College,College of Distance Studies

Alpha University College,College of Distance Studies Alpha Education and Training Company

ለርቀት መርሐግብር  የፈተና ዝግጅት ለባለሙያዎች የተደረገ ጥሪ
29/09/2022

ለርቀት መርሐግብር የፈተና ዝግጅት ለባለሙያዎች የተደረገ ጥሪ

21/09/2022
21/09/2022
አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመደበኛና በርቀት ትምህርት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ*******************(ኢ.ፕ.ድ)አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በድህረ ምረቃ 210 እንዲሁም በቅድመ-ምረ...
19/09/2022

አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመደበኛና በርቀት ትምህርት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በድህረ ምረቃ 210 እንዲሁም በቅድመ-ምረቃ 1850 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዚደንት አቶ ዘሪሁን መስፍን፥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብት በመጠቀም ወቅቱ የሚጠይቀውን ችግር የሚፈታላት የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልጋታልና ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት በመጠቀም የአገራቸውን ችግር እንዲፈቱ አሳስበዋል።

"ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ በስራ ዕድሜ የሚገኝ የሠው ኃይል፣ አኩሪ ታሪክና ባህል ያላት ውብ ሀገር ናት፡፡ እነዚህን ገፀ በረከቶች ወደ ውጤት በመቀየር የሀገራችን ህዝቦች ካሉባቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች መታደግ ወቅቱ የሚጠይቀው የተማሩ ዜጎች የዕለት ተዕለት ተግባር እንደሚሆን ይጠበቃል በመሆኑም በቀጣይ እናንተ በዩኒቨርስቲ ኮሌጃችን በዛሬው ዕለት ትምህርታችሁን በሚገባ ተከታትላችሁ ያጠናቀቃችሁ የዕለቱ ተመራቂዎቻችን ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት በምትሠማሩበት የስራ መስክ በአግባቡና
ኃላፊነት በተሞላበት ጭምር ለሀገራችሁና ለሕዝቦቿ እንደምታበረክቱ የፀና ዕምነት አለኝ" ብለዋል።

ቀጣይ ዘመናችሁ የፍቅር፣ የመከባበርና የአንድነት ጉዞ እንዲሆን በመመኘት በሄዳች ሁበት ሁሉ ዩኒቨርስቲ ኮሌጃችንን በአግባቡ በመወከል አምባሳደሮቻችን እንድትሆኑ ሲሉም አደራ አስተላልፈዋል።

የአልፋ ዩኒቨርስቲ የቦርድ አባል ዶክተር ብርሃኔ አስፋው፥ ለተመራቂ ተማሪዎች በባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ፍላጎታችሁን ለማሳካትና የሚፈለገው ርቀት ላይ ለመድረስ አሁንም አልረፈደም ሲሉ የትምህርት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።

በየጊዜው ራስን በማሳደግ ሁልጊዜ በማንበብ ለቀጣይ ከፍተኛ ትምህርት ተግታችሁ ተገኙ ሲሉ ለተመራቂ ተማሪዎች አሳስበዋል።

Messages from Associate Vice Persident for College of Distance Studies
14/09/2022

Messages from Associate Vice Persident for College of Distance Studies

Registration for 2015 E.C. is On !!!
17/08/2022

Registration for 2015 E.C. is On !!!

Address

Addis Ababa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alpha University College,College of Distance Studies posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Alpha University College,College of Distance Studies:

Share