30/12/2023
🗣️የፉልሀም አሠልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ከነገው የፉልሃም እና አርሰናል ጨዋታ በፊት ይህንን ተናግረዋል
🗣 " አርሰናል ምንም ጥርጥር የለውም በሊጉ ጥሩ ብቃት ላይ ነው ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም ነገ በሜዳችን የምንገጥመው የሊጉን ምርጥ ቡድን ነው።"
🗣"ቡድኑ የሜዳ ላይ እንቅሥቃሴያቸው እጅግ የሚያሥገርም ነው የፊት መሥመራቸው ኳሡን የሚቆጣጠሩበት እንዲሁም የኋላ መሥመር ላይ የተደራጀ መከላከል ድንቅ ብቃት አላቸው ለየትኛውም ቡድን ምቾት የማይሠጥ ኳሥን እንደፈለጉ የሚቆጣጠሩ እና አጥቂዎቻቸው ለተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ምቾት የማይሠጥ ከፍተኛ የማጥቃት በሀሪ የተላበሰ ቡድን ነው።"
🗣 " አርሠናል በሁሉም መሥፈርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቡድን ነው ማለት።"
🗣 "የሚጫወቱበት መንገድ ተጋጣሚ ቡድንን ወደ ኋላ የመግፋት አቅም አላቸው። እናም እነሱን ተጭኖ ለመጫወት ለማጥቃት እና ለመጫን በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም እነሡ የሚጫወቱበት መንገድ ተጋጣሚን በመጫን እና ኳሥ በመቆጣጠር የሚጫወቱ በመሆኑ እነሡን ተጭነን ለመግጠም ከእነሡ ጋር በዚህ መንገድ ለመጋፈጥ አስቸጋሪ ቡድን ናቸው።"
🗣" ተመልከት የዚንቼንኮን ፖዚሽናል ቦታ ዚንቼንኮ ምንም እንኳን በተመለላሽ ቦታ ላይ የሚሠለፍ ቢሆንም ወደ መሀል ሜዳ እየተሳበ በመሃል ክፍሉ ላይ ከአንድ ተጨማሪ ሃይል ይፈጥራል ለመሀል ክፍላቸውም ጥራትን ይሰጣቸዋል።"
🗣 " ቡድናቸው ውሥጥ ለተቃራኒ ቡድን አሥቸጋሪ ፈጣን ተጫዋቾች አሏቸው እንደ ማርቲኔሊ ሳካ Ødegaard እና Havertz የመሳሰሉ ድንቅ ብቃት የላቸው ተጫዋቾች ሁሌም ለተጋጣሚ ቡድን አስጊ ናቸው።"
🗣 " አርሠናል እጅግ የላቀ ብቃት ባላቸው ተጫዋቾች የተዋቀረ እጅግ ጥራት ያላቸውን ተጫዋቾች የያዘ ቡድን ነው እነሡ በዚህ ሀገር ውስጥ የሚገኝ የትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን በሚገባ ማሸነፍ ይችላሉ በዚህ ሊግ የሚገኝ የትኛውም ቡድን መግጥም የማይፈልገው ቡድን አርሠናል ነው ብል ምንም ማጋናነን አይሆንብኝም እነሱን ለማቆም እንደ ቡድን በደንብ መደራጀት ከመጀመሪያ እሥከ ጨዋታው ፍጻሜ ትኩረት ሳይለይህ እንደ ቡድን አንድ ላይ እነሡን መጣበቅ አለብን እኑሡ እኛን በመጫንና እኛን በቅጽበት ጫና ውስጥ እንድንገባ ኳሥ እንድንይዝ አይፈቅዱልንም ነገር ግን ኳሱን ሥናገኝ እኛም በተደራጀ ጨዋታ የምናገኛቸውን እድሎች በመጠቀም ራሳችንን መግለጽ ያለብን እና እንደ አርሠናል ካለ ከፍተኛ ብቃት ይዞ ከሚገኝ ቡድን ጋር ተጋፍጠህ ለማሸነፍ ቁርጠኛ መሆን አለብህ ለዚህ ደሞ ዝግጁ ነን።"
🔜በማለት የፉልሃሙ አለቃ ማርኮ ሲልቫ ከጫወታው በፊት ተናግረዋል🖐