30/12/2025
አንዲት የጽዳት ሰራተኛ አንድ ቦርሳ ይዛ ወደ አለቃዋ ቢሮ ገባችና "ጌታዬ፣ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ እያጸዳሁ ሳለ ይህንን ቦርሳ አገኘሁት" አለች።
አለቃውም "እሺ፣ እዚህ አስቀምጪው" አለ።
ሰራተኛዋም በመቀጠል "ቦርሳው በከፊል ክፍት ስለነበር፣ 3,000 ዶላር አየሁ። አንዳንድ ዕቃዎችም ወድቀው ስለነበር በጥንቃቄ መልሼ አስቀምጬዋለሁ" አለች::
አለቃው አመስግኖ አሰናበታት:: ወዲያውም ትልቅ ደንበኛቸው ለሆነውና ለቦርሳው ባለቤት ለሚስተር ዊልሰን ደውሎ "ሄሎ፣ ቦርሳዎን እኛ ጋር ረስተውት ሄደዋል" አላቸው::
ሚስተር ዊልሰንም፣ "ኦ! እግዚአብሔር ይመስገን! የት ጣልኩት ብዬ ተጨንቄ ነበር። ውስጥ 5,000 ዶላር አለበት" አሉ።
ስልኩ ሲዘጋ አለቃው ግራ ተጋባ። የጽዳት ሰራተኛዋ ያለችው 3,000 ነው፤ ባለቤቱ ግን 5,000 ነው ያለው።
ጸሃፊዋ ጣልቃ ገባችና "ጌታዬ፣ የጎደለውን 2,000 ዶላር በእርግጠኝነት እሷ ነች የወሰደችው" አለች::
አለቃውም "ለምን እንደዚያ አሰብሽ?" ሲል ጠየቃት።
"ምክንያቱም እሷ የሁለት ልጆች እናት የሆነች፣ ያለ ባል የምትኖር ችግረኛ ናት። ባለፈው ሳምንት ደሞዝ እንዲጨመርላት ስትለምን አይቻታለሁ። እንዳይገርምህ ጌታዬ፣ እንዲህ አይነት ሰዎች በጣም አጭበርባሪ ናቸው፤ እመነኝ እሷ ናት የሰረቀችው" አለች።
ከስራ በኃላ ወደ ቤት ሲሄዱ፣ አለቃው የጽዳት ሰራተኛዋን ጠጋ ብሎ "እሜቴ፣ በኑሮ እየተቸገርሽ ነው?" ሲል ጠየቃት።
"አዎ ጌታዬ፣ ትንሽ ከበድ ብሎኛል። ልጄ ሆስፒታል ታማብኝ ለህክምናዋ 2,000 ዶላር አስፈልጎኛል" አለች።
ወዲው ጸሃፊዋ ጮኸች! "አየህ ጌታዬ! ልክ የጎደለው ገንዘብ መጠን ነው! እሷ ሌባ ናት!" አለች::
የጽዳት ሰራተኛዋም ደነገጠች:: መልሳም "ሌባ? ኧረ እኔ ምንም አልሰረቅኩም፤ ለምን ትዋሺለሽ?" አለች።
አለቃውም "በቃ ይበቃል፣ ሂጂ" ብሎ ተሰናበታት።
በሚቀጥለው ቀን ሚስተር ዊልሰን ቦርሳቸውን ሊቀበሉ መጡ። ቦርሳውን ሲከፍቱ ግን 3,000 ዶላር ብቻ አገኙ።
አለቃውና ፀሐፊዋም ምን ይፈጠር ይሆን ብለው ይጠብቁ ጀመር::
ነገር ግን ሚስተር ዊልሰን አልተቆጡም፣ እንዲያውም ተገረሙና "ኦ! ይቅርታ በጣም ትላንትና ረስቼው ነበር። ለካ 2,000 ዶላሩን ለጓደኛዬ ለመስጠት ቀንሼ ነበር። ቦርሳው ውስጥ ትቼ የሄድኩት 3,000 ዶላር ብቻ ነው። ስለ ስህተቴ ይቅርታ" አሉ።
በዚህ ጊዜ ጸሃፊዋ በአፍረት ደርቃ ቀረች። በስህተት ጽዳት ሰራተኛዋን በመወንጀሏ ምክንያት::
አለቃው ግን ፈገግ አለና የጽዳት ሰራተኛዋን አስጠራት። ለደንበኛው እያሳየ፣ "ቦርሳዎን ያገኘችው ይህች ሴት ናት። ምንም እንኳን የራሷ ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ቢኖርባትም፣ እምነቷን ጠብቃ ቦርሳውን መልሳለች። ከዛሬ ጀምሮ እሷ አዲሷ ምክትል ረዳቴ ናት። ደሞዟም ይጨምራል፣ የልጇም ህክምና ይሸፈናል" አለ።
-------------- ------------- -------------
በችግር ውስጥም ሆኖ ታማኝ መሆን ትልቅ ዋጋ ያስገኛል።
ሰውን በሁኔታው አይተን መፍረድ ስህተት ነው።
እውነት ትዘገይ ይሆናል እንጂ፣ የልፋት እና የታማኝነት ዋጋ መከፈሉ አይቀርም።
ታማኝነት መሸለም አለበት ብላችሁ ካመናችሁ፣ እስቲ የልብ ምልክት (❤️) ኮሜንት ላይ አስቀምጡ።
🛑ላይክ ሼርና ፎሎ ማድረግ እንዳይረሳ!!!