Tzu dire

Tzu dire Tizu love

13/03/2020
29/08/2019
09/06/2019
04/06/2019
31/05/2019

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን ስልሣኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘውን የሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ጎበኙ። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በፊስቱላ ሕመም የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ክብር ለመመለስ ለሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ዶ/ር ካትሪን ሐምሊንን አመስግነዋል። ዶ/ር ሐምሊን የተገለሉና የተረሱትን ለመንከባከብ የሚጫወቱትን ሚና ከልብ እንደሚያደንቁም ጠ/ሚሩ ተናግረዋል። በማስከተልም ለዚሁ አገልግሎታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት የዕውቅና ሽልማት ያበረከቱላቸው ሲሆን ከቀዳማዊት አመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆንም በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ የዛፍ ችግኝ ተክለዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed and First Lady Zinash Tayachew visited the Hamlin Fistula Hospital in celebration of the hospital’s 60th anniversary of service. Prime Minister Abiy commended Dr Catherine Hamlin for her tremendous work of restoring the dignity of Ethiopian women affected by obstetric fistula. He expressed his heartfelt appreciation for the care-taking role she took of the most marginalized in their time of grave need. Prime Minister Abiy Ahmed also bestowed an award upon Dr Catherine Hamlin on behalf of the Government of Ethiopia for her tireless contribution and together with First Lady Zinash Tayachew planted seedlings in the compound of the hospital.

24/05/2019

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የ2011 ትምህርት ዘመን የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ማስፈፀሚያ የንቅናቄ ዕቅድ ረቂቅ ሠነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የመፈተኛ ጊዜውን የወሰነ መሆኑ ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

ሆኖም በዛሬው ዕለት የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት ባደረገው ስብሰባ ከኢድ በዓል ጋር በተያያዘ በጥልቀት ተወያይቶ፦

1ኛ .የ10ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 3፣ 4 እና 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፤

2ኛ.የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣ 7፣ 10 እና 11 ቀን 2011ዓ.ም ሲሆን፥

3ኛ. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 12፣ 13 እና 14 ቀን 2011ዓ.ም. ለአስተዳደራዊ አመቺነት ሲባል የተቀየረ መሆኑን አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከህብረተሰቡ ጥያቄ በተጨማሪም ፈተና ተፈታኞችና ፈታኞች ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ከቦታ ቦታ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠርና የፈተናውን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቋል፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251917118286

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tzu dire posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share