Konta Special Woreda Edu.Office

Konta Special Woreda Edu.Office This page created only to promote educational values, success.... in woreda office and schools. It i

በኮንታ ልዩ ወረዳ በ2012 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የአመያ 2ኛ ደረጃና በመሠናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፦     ...
26/04/2021

በኮንታ ልዩ ወረዳ በ2012 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የአመያ 2ኛ ደረጃና በመሠናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፦
1. ተማሪ አዲሱ አስራት አደለ 533
2. ተማሪ ሁሉምያልፋል በለጠ ወ/ማሪያም 476
3. ተማሪ ገብሬ ገዛኸኝ ዳሮታ 476
የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የማበረታቻ ሽልማት ለእያንዳንዳቸው Corei 7 8th generation laptop ተሰጥቷል። ይህ ሽልማት ለተማሪዎችና ለመምህራን ከፍተኛ መነሳሳትን የሚፈጥርና በትምህርት ስራ የተሻለ ፉክክር የሚፈጥር ነው። ተሸላሚ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ተማሪዎችንን በመደገፍ፣ በማስተማር እገዛ ያደረጋችሁ የአመያ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት አመራርና መምህራን ላደረጋችሁት ተሳትፎ የልዩ ወረዳው መንግስትና ትምህርት ጽ/ቤት ልባዊ ምስጋና ያቀርባል። የተመዘገበው ውጤት የእናንተም፣ የተማሪዎችም የእኛም በአጠቃላይ የልዩ ወረዳው ስለሆነ ቀጣይ ከዚህ የሚበልጥ ውጤት በማስመዝገብ ብቁና ተወዳዳሪ በራሱ የሚተማመን ዜጋ ለመፍጠር ለምታደርጉት ጥረት የልዩ ወረዳው መንግስትም ሆነ ትም/ጽ/ቤት ከጎናችሁ በመሆን የማበረታታት ስራ የሚሰራና በሚያስፈልጋችሁ ጉዳይ ሁሉ ከጎናችሁ የሚቆም መሆኑን እናረጋግጣለን። ሌሎችም ቀን ከሌሊት እየሰራችሁ፣ ሙያዊ ግዴታችሁንና ኃላፊነታችሁን እየተወጣችሁ ግን ያሰባችሁት ያህል ውጤት ባለመምጣቱ በቁጭት ውስጥ ያላችሁ የዘርፉ የትምህርት አመራርና መምህራን ምንም ዓይነት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሳትገቡ ስራችሁን እንድትሰሩ እያሳሰብን ከተጋገዝን፣ ከልብ ከሰራን የወደቀውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ እንደምንችል ሙሉ እምነት አለን። በዚህ ጊዜ ከእውነታ የራቀ በጥናት ያልተረጋገጠ ወቀሳና ትችት እንዲሁም በየማህበራዊ ሚዲያ የሚጻፍና የሚተነተን ከሙያዊና ምሁራዊ ንግግር ያፈነገጠ ወሬ ሰምታችሁ ትጥቅ መፍታት አያስፈልግም። መፍትሄው በእጃችን ነው። ያለፈው ውድቀታችን መቼም ምንጊዜም የወደፊት ተስፋችንን ሊያጨልም አይችል። በብዙ ውጣውረድ ተምራችሁ ውጤት ባለመምጣቱ ያዘናችሁ ተማሪዎቻችን እንዲሁም ለልጆቻችሁ ውጤት ማማር ዋጋ የከፈላችሁ የተማሪ ወላጆች የውጤት ድርቀት ምንም እንኳን ቢያሳዝነንም አሁንም ዕድል በእጃችሁ እና በእጃችን መሆኑን ተገንዝበን ከፊት ያለውን ተስፋ በማየት እንደገና ለማሻሻል እንድትሞክሩ እኛም ቀን ከሌሊት በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ከጎናችሁ በመቆም የምናግዛችሁ መሆኑን እንገልጻለን። ውድ የትምህርት አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች ኮንታ ላይ የሚዋዥቅ ውጤት ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ውጤት ለማስመዝገብ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ጥናት በማድረግ ዘላቂነት ያለው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት ሁሉ ከጎናችን እንድትቆሙ እንጠይቃለን። ወሬ ሳንሰማ ትክክለኛና ምሁራዊ እንዲሁም ሙያዊ ግምገማዎችንና ትችቶችን የአቅም መገንቢያ መሳሪያና ግብዓት አድርገን እየተቀበልን የዘርፉን እድገት ለመደገፍ ከልብ ለምትቀርቡ ባለድርሻዎች በራችን ምንጊዜም ክፍት ነው። ከሰራን፣ ከተጋገዝን ከተደማመጥን፣ አንዳችን ለአንዳችን አቅም ከሆንን በእርግጠኝነት ውጤት እናመጣለን።
የኮንታ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
ሚያዝያ 2013/ ኮንታ-አመያ

Address

SNNPR
Adiya

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konta Special Woreda Edu.Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Konta Special Woreda Edu.Office:

Share