25/04/2026
የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ለሶስት ዓመታት በደረጃ አራት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አሰመረቀ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
የአጋርፋ ኮሌጅ በሰብል ልማት፣ በመሬት አስተዳደር እና ተፈጥሮ ሀብት ያሰለጠናቸውን በመደበኛ 514 በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም 78 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመረቀ።
በምረቃው መግቢያ ላይ የክሌጁ ዲን አቶ ፊራኦል ኤደኦ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ ለዛሬ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለው። በሀገራችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአንበሳውን ድርሻ የምትይዙት እናንተ ስለሆናችሁ የተጣለባችሁን ከፍተኛ ሀላፊነት እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል ።
በምረቃ ስነስረዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት ዓባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ብረሀነመስቀል ጠና ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የዘንድሮ ተመራቂዎች ለየት የሚያደርጋችሁ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዋዜማ ላይ የተመረቃችሁ መሆኑ ነው ብለዋል።
የተከበሩ ፕሬዝዳንቱ አክለውም እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች ለሀገራችሁ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላችሁ በመሆኑ ተግታችሁ እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበዋል።
በስራና ክህሎት ሚንስቴር የቴክኒክና ሙያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት የተከበሩ አቶ ጌታቸው ደምሴ በበኩላቸው ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የወደፊት የስራ አቅጣጫ በመስጠት አጠቃለዋል።
ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት