06/06/2026
ተሳታፊዎች የሰርቲፊኬትና የዕውቅና መርሃ ግብር እና #የምርምር እና #ቴክኖሎጂ ውድድር ማጠቃለያ ተካሄደ
ካምባ፣ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም. (ካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
በካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮምፒውተር የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች እና በአክሽን ሪሰርች (Action Research) ሥራዎች የተሳተፉ ባለሙያዎች የሰርቲፊኬትና የዕውቅና ሽልማት መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የካምባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ለተመራቂዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል። በንግግራቸውም እንደ ካምባ ምርጫ ክልል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ የሁሉም አካላት ትብብር ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰልጣኞቹም ከዕለታዊ ኃላፊነቶቻቸው ጋር በማስተባበር ለስልጠናው ቅድሚያ በመስጠት ወደ ስኬት መድረሳቸው የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ “ #ተቋማትንና #ማኅበረሰቡን #ለማገልገል #ያስችላል። ዛሬ ለሰርቲፊኬት በመብቃታችሁ ።” ብለዋል።
በሌላ በኩል አቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኮሌጁ በማታ መርሃ ግብር ለሦስት ወራት የቆየ የኮምፒውተር ስልጠና መስጠቱን ገልጸው፣ ከመደበኛ ትምህርቱ በተጨማሪም አሰልጣኞች በሥራ ቦታቸው ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙ የአክሽን ሪሰርች ጥናቶችን በማካሄድ ለዕውቅና መብቃታቸውን አስረድተዋል።
የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ #ተበጀ #ተለማ በበኩላቸው፣ ይህ ስልጠና ቀጣይነት ያለው መሆኑን በመግለጽ፤ ስልጠናውን ያልወሰዱ አካላት የኮሌጁ በር ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል። አክለውም ፤ “ዘመኑ የሚጠይቀው #ዲጂታል መሆንን ነው፤ ስለዚህ እንላመድ፣ #እንሰልጥን፣ ፣ ” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ኢንዱስትሪ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በሰጡት አስተያየት፣ የተሰራው ቴክኖሎጂ የማህበረሰብ ችግር ከመፍታት አኳያ ላቅ ያለ ድርሻ ያለው በመሆኑ ባለሙያዎች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንዳለባቸው ሀሳብ ሰጥተዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በዘመናዊ የኮምፒውተር ክህሎቶች፣ በመረጃ አያያዝ እና በቢሮ አፕሊኬሽኖች ላይ ተግባራዊ እውቀት ማግኘታቸው ተገልጿል። በስልጠናው በድምሩ 98 ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመርሃ ግብሩ ላይ አስተያየት የሰጡ ሰልጣኞች ስልጠናው በሙያቸውና በዕለታዊ የሥራ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጣላቸው ገልጸዋል። “ከዚህ በፊት ብዙ የቢሮ ሥራዎችን በእጅ እንሠራ ነበር። አሁን ግን ኮምፒውተርን በብቃት በመጠቀም ሥራዎቻችንን በፍጥነትና በጥራት ማከናወን ችለናል። ስልጠናው የነበረው ተግባራዊ አቀራረብ ለሥራ ቦታችን በቀጥታ የሚጠቅም እውቀት እንድናገኝ አስችሎናል። ወደፊትም ተጨማሪ ስልጠናዎች ቢዘጋጁ በደስታ እንሳተፋለን።” ብለዋል።
በመጨረሻም ኮሌጁ የጀመረውን የአጭር ጊዜ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ፕሮግራም በስፋት እንደምቀጥል ያስታወቀ ሲሆን፣ ፣ እንደዚህ ዓይነት ስልጠናዎች የሰው ኃይል ብቃትን በማሳደግ ለተቋማት ውጤታማነትና ለአካባቢው ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የካምባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ይስሐቅ ዮሐንስ፣ አቶ ግዳጀ ግምቴ የካምባ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን፣ አቶ ተበጀ ተለማ የኮሌጁ ምክትል ዲንና የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ማርቆስ ምልፆ የኮሌጁ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ፣ እንዲሁም የኮሌጁ ኢንስትራክተሮችና ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
#ካምባ
Bezabih Gebeyehu
Yisahak Yohannes
Teka Wude
Tsehay Bekele
Lissanework Kassaye Eka
Enku Yohannes
Tebeje Telema
Markos Milko Mitsa