19/11/2024
ለበጎ ስራ ተመልሻለሁ 🙏🙏🙏
ወንድማችን ፍፁም ግርማ (ፍፄ) በጠና ታሟል። በእርግጥ ካመመው ወራቶት ተቆጠሩ። በሽታውን የሰው ፊት ሳያይ "እርዳታ እናሰባስብ" ብንለው እንኳን "ቆይ!"ብሎ ብቻውን ለመታገል ሞከረ ሞከረ ሞከረ ግን አሁን ከአቅሙ በላይ ሆነበት። "አቃተኝ አግዙኝ" ሲል እንዴት ልብ ይሰብራል። ከራሱ አልፎ ለሰዎች፣ ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ ልጅ በድንገት በበሽታ ወድቆ እጅ አጠረው። በሽታ ክፉ ነው። ተሯሩጦ እንዳይበላ አስሮ ያስቀምጣል። በህመም ምክንያት በተቋረጠ ገቢ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል። ፍፄ ይህን ተቋቁሞ ህመሙን በሆዱ ሸሽጎ ነበር። ዛሬ ግን እስከ 2 ሚሊየን ብር የሚፈጅ የውጭ ሀገር ህክምና እንደሚያስፈልገው ሲሰማ "አሁን ተራው የእናንተ ነው" አለን። ከፈጣሪ በታች ለሰው መድኃኒት ሰው ነው። እናም ፍፄ እኛን ላለማስቸገር ብዙ ታግሎ አቃተኝ ካለ እኛ አለንልህ ልምለው ይገባል።
ነገ እኛም ተረኞች ነን እናም የአቅማችንን በማውጣት ፍፄን እንታደገው።
ይሄንን የእርዳታ መስጫ አማራጮች ተጠቅመን እናግዘው የላካችሁበትን ፎቶውን ብትልኩልን ሌሎችን ያበረታታል።
👉ንግድ ባንክ 1000222130143
👉አቢስንያ 36211725
👉ቴሌብር 0911395229/0913246683
ፍፁም ግርማ አሸብር
ሼር አድርጉት🙏