19/12/2025
“ ዩናይትድ ሊጉን ለማሸነፍ ሌላ 10 አመት ሊያስፈልገው ይችላል “ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን
| የቀድሞ ታሪካዊ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ማንችስተር ዩናይትድ ሊጉን ለማሸነፍ ተጨማሪ 10 አመት ሊያስፈልገው እንደሚችል ገምተዋል።
“ ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ያለበት ሁኔታ የእኔን ገጠመኝ አስታውሶኛል ሊቨርፑል ሀያል የነበረበትን ወቅት “ ሲሉ ፈርጉሰን አስታውሰዋል።
" ሊቨርፑል አራት ሻምፒየንስ ሊግ ያሸነፈ አስደናቂ ቡድን ነበር " ያሉት አሰልጣኙ “ ነገርግን ሊጉን ለማሸነፍ 30 አመት ጠብቀዋል “ ብለዋል።
“ ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ነው ፤ ፕሪሚየር ሊጉን ለማሸነፍ ሌላ አስር ወይም አስራ አንድ አመት ሊወስድ ይችላል " ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።