20/06/2026
ሲዳማ ቡና የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!
****************
ሲዳማ ቡና ሁለት ጨዋታ እየቀረው የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
በ36ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያይቷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብርሀኑ በቀለ ለሲዳማ ቡና፣ በረከት ወልዴ በፍጹም ቅጣት ምት ለነገሌ አርሲ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከጨዋታው አንድ ነጥብ ያገኘው ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳክቷል።
በሊጉ ታሪክም ይሄንን ክብር የወሰደ 11ኛው ክለብ ሆኗል።
በ2002 ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው እና ባለፉት አስራ ሰባት አመታት በሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ ዕርከን ላይ ሲወዳደር የቆየው ሲዳማ ቡና አስረኛ የክለቡ አሰልጣኝ በሆነው ያሬድ ገመቹ እየመራ ዋንጫውን ወስዷል።
ክለቡ በቀጣይ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክልም ይሆናል።