Psychology department- Bahir Dar University

Psychology department- Bahir Dar University Psychology is a diverse field of study that will prepare you for a wide variety of career options.

01/10/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Yakoral Animaw, Abay Ayana, Mulugeta Tesema, Jamaal Yuusuf

12/11/2024

ፍልስፍና በእጓለ ገ/ዮሐንስ፤

ፍልስፍና ሲባል ሰፊ ነገር ነው። ሁለት ቅርጫፎች ባሉት ዛፍ ይመሰላል። አንድኛው ተራርቆ የሚገኘው የሥነ ፍጥረት ዓለም ነው። ሁለትኛው ከሰው መንፈስ የሚገኘው የታሪክ ወይም የሥልጣኔ ዓለም ነው።ሁለቱም ዓለማት የሚገናኙበት አንድ ቦታ አላቸው። ሰው ይባላል።

ሰው በሁለት ዓለማት መካከል የሚገኝ አማካኝ ፍጥረት ነው። በአካሉ የጉልሁ ዓለም ተካፋይ ነው።በመንፈሱ የረቂቁ የዘላቂው ዓለም ተሳታፊ ነው። በሥነ ፍጥረት የሚጸናው የግዴታ ህግ በእሱም ላይ ይጸናል። በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ የሚጸናው የነፃነት ህግ በእሱም ላይ ይጸናል።

የልፋት መልካም ውጤት!
16/07/2023

የልፋት መልካም ውጤት!

የትምህርት ኮሌጅ ለመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 95% ቱን አሳልፏል።
የዮኒቨርስቲያችንን አጠቃላይ የማሳለፍ ምጣኔ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሐምሌ 09/2015ዓ/ም(የውስጥ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን-BDU) እንደዘገበው፥

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች 84.7% የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል

ፈተና ከተሰጠባቸው 79 ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% ማሳለፍ ችለዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ79 ፕሮግራሞች 3229 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በማስፈተን 84.7 በመቶ የማለፊያ በቂ ውጤት አስመገቡ።

በመደበኛው መርሐ ግብር ብቻ ፈተናውን ከወሰዱ 2843 ተማሪዎች ውስጥ 89.5 ከ50 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ሲሆን ፈተና ከተሰጠባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% ሁሉም ተማሪዎች፣ በ14 ፕሮግራሞች ደግሞ በእያንዳንዱ ፕሮግራሞት 1ተማሪ ብቻ ሲቀር ሁሉም አልፈዋል።

በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር 45ተማሪዎች ተፈትነው 55.3% ፣ በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር 305 ተተማሪዎት ተፈትነው 43.9 ፣ በክረምት መርሐ ግብር 34 ተማሪዎች ተፈትነው 85.3% ያሳለፈ ሲሆን በሁሉም መርሐ ግብሮች 84.7 የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ጥራት ላለው ትምህርትና ምርምር አበክሮ የሚሰራው የ60ዓመት ባለፀጋው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዚሁ አጋጣሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

14/06/2023
Call for Invitation
29/05/2023

Call for Invitation

Call for invitation
23/05/2023

Call for invitation

19/05/2023

ግለኝነት ...!
የሰው ልጅ ባህርይ የግነኝት መንፈስ የነገሰበት ይመስላል።የሰው ፍላጎት ገደብ አልባ የሆነበት ምክንያትም በግለኝነቱ ሳይሆን አይቀርም። ግለኝነት፤ ከልክ ያለፈ ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ የመፈለግ ባህርይ ነው።

"ግለኝነት፤ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ የግጭት መንስኤ ነው" ቢባል ስህተት አይሆንም። በዚህ ዓለም የተከሰቱ የሰው ልጆች ግጭቶች፤"የእኔ ካልሆነ ወይም የእኔው ካልሆነ" በሚል ሰጣ-ገባና ውዝግብ የተጀመሩ ናቸው።የግለኝነት ግጭቶች በሂደት አድገው መጠነ-ሰፊ ጦርነቶች ይሆናሉ። ሁነዋልም።

በዓለም ላይ የተፈጸሙ ጦርነቶች፤ የሃብት በሆኑ ጉዳዮችና በሴት መንስኤ የተከሰቱ ናቸው። በሰው ልጆች መካከል የተደረጉ ጦርነቶች መንስኤ ከዚህ ውጭ ይሆናል ተብሎ የሚታመን አይደለም።

በሴት መንስኤ ከተከሰቱ ጦርነትች፤ ለምሳሌ "የትሮይ ፈረስ" በመባል የሚታወቀውን ታሪካዊ ሁነትን መጥቀስ ይቻላል። የሃብት ምንጭ በሆኑ ጉዳዮች የተከሰቱ ጦርነቶች በርካታና መጠነ-ሰፊ ናቸው። ሥልጣን፣ መሬት፣ንግድና የመሳሰሉት፤ ሃብት የሚገኝባቸው ጉዳዮች ናቸው።አንድኛውና ሁለትኛው የዓለም ጦርነቶች በነዚህ መንስኤዎች የተከሰቱ መሆኑን በርካታ የታርክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

በሀገራችንም፤ሥልጣንና መሬት የግጭት መንስኤዎች ሰለመሆናቸው በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።በሀገራችን፤ ከጥንት እሰከዚህ ጊዜ ድረስ በርካታና መጠነ-ሰፊ ጦርነቶች ተከስተዋል። "ግለኝነት፤የወለዳቸው ጦርነቶች ናቸው" ማለት ይቻላል።"ሥልጣኑም፣ መሬቱም፣ ንግዱም የእኔ ብቻ ይሁንና ይድላኝ" ከሚል የግለኝነት መንፈስ የመነጩ ግጭቶች ናቸው።

በሀገራችን፤በሴት ምክንያት የተከሰቱ ግጭቶች፤ መጠነ-ሰፊ አይባሉም እንጅ በርካታ መሆናቸው ግን አይካድም። ግጭቶች፤ በጦርነት ደረጃ ባይገለጹም ብዙ ህይወትን የቀጠፉ መሆናቸው ማንም የሚረዳው ነባራዊ ሀቅ ነው።

19/05/2023

...ሰዎች እንደተቆለለ ድጋይ ናቸው። የላይኛው የታችኛውን መቼም ይጫነዋል። የታችኛውም እንደዚሁ ከበታቹ ላለው የባሰ ሸክም ይሆንበታል። እንደዚህ ክብደቱ ያልተመዛዘነ በመሆኑ ቁልሉ መፍረሱ አይቀርም። በቁልሉ ውስጥ የሚገኙትን ድንጋዮች ሁሉንም የምትሸከም ምድር ናት። ህዝብም እንደ ምድር ነው። ዘመናዮችን፤ ከነባለሟሎቻቸው፣ ከነሎሌዎቻቸው፣ ከነባሮቻቸው ተሽክሞ ችሎ ይኖራል...የተክለ ሐዋርያት ሃሳብ ነው።

ምድር ለሰው ልጆች ህልውና እና ፍላጎት አሰፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ይዛ ተፈጥራለች።መሬት ለሰው ልጆች መገልገያ ነገሮችን በሙሉ ይዛለች።ሁሉም ነገር ከምድር የተገኘ ነው።ይህ ሁነት፤ የሰው ልጅ የማግኘት እንጅ የመፍጠር ችሎታ የለውም ለማት የሚያስችል ይመስላል። የሰው ልጅ በተፈጥሮ በታደለው የማስብ ችሎታን ተጠቅሞ፤በምርምር ከምድር ያገኘውን ቁስ ቅርጹን በመቀየር ይገለግልበታል።ማርክስ እንዳለው፤ ስራ ተስራ የሚባለው፤ የተፈጥሮን ቁስ ቅርጹን ቀይሮ ለአገልግሎት ማዋል ሲቻል ነው።

"ዓለም ለሰው ልጆች ፍላጎት በበቂ ይዛለች ነገር ግን ሰው ሰግብግብ ስለሆነ፤ እርስ በእርስ ይጫረሳል"ሲል ጋንዲ በአጭሩ ገልጾታለ።

ምድር የሰው ልጆችን ከእነ ችግሮቻቸው ተሸክማ ትኖራለች።ምድርን፤ተፈጥሮ ቻይ አድርጎ ፈጥሯታል።ሰዎች፤ በመሬት ላይ የማይፈጽሙት ድርጊት የለም ማለት ይቻላል።መሬት ሁሉንም ሰው ታስተናግዳለች።አትመርጥም።ምድር፤ ሰዎች ከሞቱ በኋላም ከእነ ጉዳቸው በውስጧ ደብቃ ለዘላለም ታኖራለች።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤በሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል፤የትምህርት ክፍላችን ምርጡ መምህር (ዶ/ር ዮሃንስ አስማረ) ከተማሪዎቹ ጋር በደሰታ ደምቀው ይታያሉ።ይናገራል ፎቶ! ከዚህ የቡድን ፎቶ ውስጥ ...
18/03/2023

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤
በሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል፤የትምህርት ክፍላችን ምርጡ መምህር (ዶ/ር ዮሃንስ አስማረ) ከተማሪዎቹ ጋር በደሰታ ደምቀው ይታያሉ።ይናገራል ፎቶ!

ከዚህ የቡድን ፎቶ ውስጥ ያላችሁ፤ የቀድሞ የትምህርት ክፍላችን ተማሪዎች "አለሁ" በሉን እና ደስ ይበለን !

18/03/2023

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤
በሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል፤ተመርቀው የወጡ ተማሪዎች የቡድን ፎቶ ያላችሁ ቤተሰቦች፤ የቡድን ፎቶዎችን በውስጥ መስመር ብትልኩልን፤ ምስሉን በዚሁ ገጽ የምንለጥፍ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Psychology department- Bahir Dar University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Psychology department- Bahir Dar University:

Share