20/04/2026
ከኢቶሪካ አልበም ጥቂት የቃላት ትርጉሞች‼️
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ የማዕረግ ጥግ(አብራ ኗሪዬ)
"መሳይ ሱላማጢስ የውበት ሩቅ ዳርቻ
አንድ አድርጎ ፈጠረሽ እስካይኖርሽ አቻ"
➡️ ሱላማጢስ፦ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ላይ የምትገኝ ወጣት ሴት ስም፥ 'የሰላም ሴት' የሚል ትርጉም ያላት፥ የሙሽራው (የንጉስ ሰሎሞን) ፍቅረኛ፥ ቆንጆ፣ ትሁትና ታማኝ ሴት
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ ዝ ፀዳል
"ከወንዙ ዳር ከአባይ ግዮን
የተገኘች ቶጳዝዮን"
➡️ ቶጳዝዮን፦ በኢትዮጵያ የሚገኝ፥ አረንጓዴ ቀለም ያለው፥ የሚያብረቀርቅ፥ የሚያበራ፥ ለአልባሳት ጌጥና ለነገስታት ዘውድ የሚያገለግል የከበረ እንቁ
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ ጀምበር
"ሀለዎቴ የልቤ ትርታ
አመላክቺኝ ሀቅ ያለው ቦታ"
➡️ ሀለዎቴ፦ 'መኖሬ' ወይም 'ህልውናዬ'፥ ሀለወ፦ ኖረ ወይም አለ ከሚለው ግሥ የወጣ
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ ፅዮን ሙሽራዬ
"የካባዋ ሙካሽ፥ ቀዩ ጥብጣብ ሲያምርባት"
➡️ ሙካሽ፦ በሀበሻ የባህል ልብሶች (ካባ፥ ቀሚስ) ላይ በወርቅ ወይም በብር ክር የሚሰራ ጥበባዊ የጥልፍ ስራ ወይም ማስዋቢያ
🎼የዘፈኑ ርዕስ፦ መሬማ
"እንደ አፋር አፍሌታ የጠየመው ፊቴን
ሌላው ቢቀር እንኳን እይው ማንነቴን"
➡️ አፍሌታ፦ አፋር ውስጥ ለውሃ መያዣነት የሚጠቀሙበት፥ ከፍየል ቆዳ የሚሰራ
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ ሳምነው
"እመምነቴ፥ እማማ"
➡️ እመምነት፦ የመነኮሳት እናት፥ የገዳም መሪ መንፈሳዊ እናት፥ አስተዳዳሪ
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ በመስኮቱ
"ልክ እንደ ፀባርቅ የአይኖችሽ ውጋጋን
አንድ አድርጎ ዘለቀው ክረምትና በጋን"
➡️ ፀባርቅ፦ ማንፀባረቅ፥ መታየት/መገለጥ
🎼የዘፈኑ ርዕስ፦ ቲንታጎ(ፒንታጎ)
"ባላምባራስ ባልሆን እኔ ቲንታጎ
ማን ክብሬን ሊነካ እንዴት ተደርጎ"
➡️ ቲንታጎ፦ ቆራጥ ጀግና፣ ፅኑ፣ የእርጋታና የጥንካሬ ማሳያ
🎼 የዘፈኑ ርዕስ፦ መርከብ
"ከየት ልዋስ ያኔ ከየት ፅናት
ሲመሌዲዴ አላኖር ሲለኝ ስጋት"
➡️ ሲመሌዲዴ፦ በግዕዝ ጨለማ ሲነግስ ወይም ሌሊቱ ሲሾም፥ በኦሮምኛ ደግሞ ካንቺ ውጪ እምቢ
እናንተም ጨምሩበት፤ ለማንኛውም ቴዲ አፍሮ በስሜት ሳይሆን በእውቀት፥ በግልብ ሃሳብ ሳይሆን በጥልቅ ንባብ ጥበብን የሚቀኝ ግዙፍ አርአያ ሰብ ነው!!!
(ታምሩ ዓለሙ)