09/03/2023
# ተጨማሪ ማሻሻያ ለ10ኛ ክፍል አጠናቃቂዎች
================================= በቀድሞው ማለትም በ12+1 /ሰርተፍኬት/ 12+2/ዲፕሎማ/ እና ከዚያ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው በቴክኒክና ሙያ የስልጠና ዘርፍ መሰልጠን ለሚፈልጉ እስከ ደረጃ 5 ድረስ ስልጠናቸውን መቀጠል ይችላሉ፡፡ ሆኖም ስልጠናቸውን የሚጀምሩት ከደረጃ አንድይሆናል፡፡
• ስልጠናቸውን በተለያየ ደረጃ አጠናቀው የተመረቁ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ማሻሻል ቢፈልጉ ስልጠናቸውን ባጠናቀቁበት ሙያ ብሄራዊ የሙያ ብቃት ምዘና እና የአንድ አመት የስራ ልምድ ካቀረቡ ቀጣዩን እስከ ደረጃ አራት በተከታታይ መሰልጠን ይችላሉ፡፡
• በደረጃ 4 ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ባጠናቀቁበት ሙያ ብሄራዊ የሙያ ብቃት ምዘና እና አንድ ዓመት በሰለጠኑበት ሙያ አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ካመጡ ወደ ደረጃ አምስት በመግባት ስልጠናቸውን መከታተል ይችላሉ፡፡
• በ10+1፤ በ10+2 እና በ10+3 የስልጠና ደረጃ ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ብሄራዊ የሙያ ብቃት ምዘና እና የአንድ አመት የስራ ልምድ ካቀረቡ ቀጣዩን እስከ ደረጃ አራት በተከታታይ መሰልጠን ይችላሉ፡፡
• በታችኞቹ የሙያ ደረጃዎች ላይ በመሰልጠን ላይ እያሉ ወደ ላይኛው ደረጃ ከፍ ለማለት የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናን በድጋሜ ወስዶ /ዳ/ ውጤቱ የዘመኑን የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያገኘ/ች;የመቁረጫ ነጥቡ በሚጋብዛቸው ደረጃ ስልጠናቸውን መቀጠል ይችላሉ
• የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀው በመደበኛው የስልጠና ፕሮግራም ወደ ቴ/ሙ/ስ/ተቋማት በመግባት መሰልጠን ያልቻሉ ተማሪዎች ቢሮው በቁጥር ሙ/ኢ/ል/ቢ-2/37/2014 በቀን 11/01/2014 በወጣው የ10ኛ ክፍል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ለ10ኛ ክፍሎች ብቻ እንዲስተናገዱ ይደረጋልይ፡፡
• ከአንድ ሙያ ወደ ሌላ ሙያ ለመቀየር የሚፈልግ ሰልጣኛ ወይም አመልካች በተቋሙ ተገምግሞ ተቀባይነት ያገኘ መሆን አለበት
• በተፈጥሮ ሳይንስም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና የመቁረጫ ነጥቡን የሚያሟሉ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ ሁሉም ሙያዎች ላይ እኩል የመወዳደርም ሆነ የመሰልጠን መብት ይኖራቸዋል፤፤