Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology

Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology In Ethiopia, EiTEX is a premier higher education institute under Bahir Dar University for more than

In Ethiopia, EiTEX is a premier higher education institute under Bahir Dar University for more than 50 years. It is a pioneer institute in offering programs in Textile, Leather, Apparel and Fashion technology. The institute continues to strive to strengthen research, community service and technology transfer activities in order to contribute to economic development of the country as per Growth and

Transformation Plan (GTP). The EiTEX is one of the limbs of the Bahir Dar University whose objectives perfectly fit the strategy of agriculture-led and export-oriented industrialization and the effort to combat the problem of textile & garment manufacturing and trade of the country. The institute aims to support and develop Ethiopian Textile, Garment, Leather and Fashion industries. Furthermore, the institute regularly organizes international conferences in the cotton, textile, apparel and leather sectors. Generally, the vision of EiTEX has been to support and enhance the capability and the competitiveness to Ethiopian Textile, Garment, Leather and Fashion industries including the small and medium enterprises.

BDU-EiTEX Announces the 2026/2027 Scholarship and Admission Opportunity for International Students. Apply now by complet...
10/06/2026

BDU-EiTEX Announces the 2026/2027 Scholarship and Admission Opportunity for International Students. Apply now by completing the online application form through the following portal::
https://forms.gle/Xijiy56NEKZMj9Ty6

08/06/2026
07/06/2026

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ የፋሽን ትርኢት

የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) የጎብኘዎች ቡድን የአማጋ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካን ጎበኘ============================================...
05/06/2026

የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) የጎብኘዎች ቡድን የአማጋ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካን ጎበኘ
========================================================================

(ባሕር ዳር-ግንቦት 27/2018 ዓ.ም) – በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) በተደረገለት የጉብኝት ጥያቄ መሠረት በሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ የተመራ የጎብኝዎች ቡድን በ“አማጋ” የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር በመገኘት የሥራ ልምድ ልውውጥ አድርጓል።

በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቡድን የፋብሪካውን የምርት ሂደት፣ የማሽነሪ አጠቃቀም፣ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት እንዲሁም የሰው ኃይል አስተዳደር ልምዶችን በተግባር ተመልክቷል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ የምርት ብቃት ማሻሻያ ዘዴዎች እና የገበያ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ አሠራሮች ላይ ገለጻ ተደርጓል።

ጉብኝቱ በፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አስጎብኝነት የተካሄደ ሲሆን፣ የምርት ሂደቶች፣ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓቶች፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የፋብሪካው የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ለጎብኚዎቹ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በኢንስቲትዩቱ እና በኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ ተግባራዊ የሥራ ልምዶችን መቀመር እና በትምህርት፣ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች የጋራ ትብብርን ማሳደግን መሆኑን ተመልክቷል።

በውይይቱም የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የአማጋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ወደፊት በተማሪዎች የተግባር ስልጠና፣ በምርምር ሥራዎች እና በቴክኖሎጂ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ያላችውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ጉብኝቱ በአካዳሚና በኢንዱስትሪ መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር እና የቴክስታይል ዘርፉን ለማዘመን የሚያግዙ ልምዶችን ለመጋራት ጠቃሚ አጋጣሚ እንደነበር ተገልጿል።

ልጆችም በፋሽን ትርኢቱ እንዲህ ተሳትፈዋል
18/05/2026

ልጆችም በፋሽን ትርኢቱ እንዲህ ተሳትፈዋል

ይህ የፋሽን ትርኢት የ14ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት አካል የሆነው  በባሕር ዳር ጊዮን ሆቴል በድምቀት እንዲህ በሚያምር ሁኔታ ተካሂዷል።
17/05/2026

ይህ የፋሽን ትርኢት የ14ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት አካል የሆነው በባሕር ዳር ጊዮን ሆቴል በድምቀት እንዲህ በሚያምር ሁኔታ ተካሂዷል።

የ14ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት አካል የሆነው የፋሽን ትዕይንት በባሕር ዳር ጊዮን ሆቴል በድምቀት ተካሄደ(ባሕር ዳር/ግንቦት 9፣ 2018 ዓ.ም.) በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትክስታ...
17/05/2026

የ14ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት አካል የሆነው የፋሽን ትዕይንት በባሕር ዳር ጊዮን ሆቴል በድምቀት ተካሄደ

(ባሕር ዳር/ግንቦት 9፣ 2018 ዓ.ም.) በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) የ14ኛው ዓለም አቀፍ የጥጥ፣ ቴክስታይል እና አልባሳት የእሴት ሰንሰለት በአፍሪካ (CTA-2026) አውደ ጥናት አካል የሆነውን የፋሽን ትዕይንት በባሕር ዳር ፈለገ ጊዮን ሆቴል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።

በኢትዮጵያ የቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) አዘጋጅነት የተካሄደው ይህ የፋሽን ትዕይንት የተማሪዎችና ታዋቂ ዲዛይነሮች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን የፋሽን ትዕይንቱ ባሕር ዳር የቱሪዝም፣ የባህል እና የትምህርት አቅሟ ከፋሽን ኢንዱስትሪ ጋር በመጣመር የአፍሪካ የፋሽን ከተማ የመሆን እድል እንዳላት ገልጸዋል። እንዲሁም በቴክስታይል እና በአልባሳት ዘርፍ ፈጠራ፣ ባህልና የቴክኖሎጂ እድገት የሚገልጽ መድረክ ሆኖ ታይቷል ሲሉ የትእይንቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። በፋሽን ትዕይንቱ ላይ ባህላዊና ዘመናዊ የአልባሳት ዲዛይኖች ቀርበው ከተሳታፊዎች ከፍተኛ አድናቆትን አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ትክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ በመዝጊያ ንግግራቸው ባሕር ዳርን የፋሽን ከተማ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች እየተጠናከሩ መሆናቸው ተገለጸ። በከተማዋ የፋሽን ትዕይንቶች እና የፈጠራ መድረኮች በማዘጋጀት ባሕር ዳርን በዘርፉ ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው። በተለይም በኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በሚዘጋጁ መርሃ ግብሮች ተማሪዎችን፣ ባለሙያዎችን እና የኢንዱስትሪ ተዋናዮችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የፋሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በ14ኛው ዓለም አቀፍ የጥጥ፣ ቴክስታይል እና አልባሳት የእሴት ሰንሰለት አውደ ጥናት በአፍሪካ (CTA-2026) የኢትዮጵያ ትክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX)ከኢትዮጰያ ንግድ ባንክ፣ ማዶት ቴክስታይል፣ ኢትዮ ላብ፣ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አቫንቲ ብሉ ናይል ሪዞርት ናኪ ሆቴል እና አዲስ አምባ ሆቴል ድጋፍና ትብብር አድርገዋል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንስቲትዩት (ALLPI) እንደ ቁልፍ አጋር ሁኖ በመሳተፍ ለኮንፈረንሱ ስኬት አስተዋፅኦ አድርጓል።

የCTA-2026 አውደ ጥናት በይፋ ተጠናቀቀ=====================(ባሕር ዳር/ግንቦት 9፣ 2018 ዓ.ም.) በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲ...
17/05/2026

የCTA-2026 አውደ ጥናት በይፋ ተጠናቀቀ
=====================

(ባሕር ዳር/ግንቦት 9፣ 2018 ዓ.ም.) በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 14ኛው ዓለም አቀፍ የጥጥ፣ ቴክስታይል እና አልባሳት የእሴት ሰንሰለት በአፍሪካ (CTA-2026) አውደ ጥናት በይፋ ተጠናቋል።

በዊዝደም አዳራሽ የተካሄደው አውደ ጥናት ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎች እና የግል ዘርፍ ተወካዮችን በማሳተፍ በዘርፉ ያሉ ዕድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የEiTEX ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ የመዝጊያ ንግግር በማድረግ አውደ ጥናቱ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ ትስስር እና በአፍሪካ አገራት መካከል የትብብር ግንኙነት ማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገበ ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር ታምራት በንግግራቸው የጥጥ፣ የቴክስታይልና የአልባሳት ዘርፍ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት ያለውን ሚና በማስታወስ በቀጣይም በምርምርና በኢንዱስትሪ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ አገራት በጋራ በመስራት በዘርፉ የተሻለ የእሴት ሰንሰለት ለመፍጠር እንደሚችሉ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ በበኩላቸው፤ በዘርፉ የሚደረጉ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎች ከኢንዱስትሪው ትስስር ጋር ይበልጥ ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው በጥብቅ አሳስበዋል።

ፕሮፌሰር ተከተል እንደ ገለፁት፤ የምርምር ውጤቶች በሸልፎች ላይ ብቻ ተወስነው ሳይቀሩ ወደ ምርት፣ ወደ ቴክኖሎጂ እና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲቀየሩ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው ቅርብ ትብብር ወሳኝ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ፈጣሪዎች እና ሀሳቦች በተግባር እንዲውሉ መንግሥት፣ የግል ዘርፍና የምርምር ተቋማት በጋራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በአውደ ጥናቱ ወቅት ከተለያዩ አገራት የመጡ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችና የፖሊሲ አውጪዎች በጥጥ፣ በቴክስታይልና በፋሽን ዘርፍ ያሉ የልማት እድሎችና ተግዳሮቶች ላይ የጥናት ጽሑፎችን አቅርበው ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
እንዲሁም በኮንፈረንሱ ጎን ለጎን የተካሄደው የፋሽን ትዕይንት መርሃ ግብር የEiTEX ተማሪዎችና ሙያዊ ዲዛይነሮች የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ ታዳሚዎችን አስደምሙዋል።

በመጨረሻም የEiTEX ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ለአውደ ጥናቱ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ ተሳታፊዎች፣ አጋር ተቋማት፣ ተመራማሪዎች፣ አዘጋጆችና ደጋፊዎች ምስጋና በማቅረብ የሰርትፊኬት አሰጣጥ ስነስርዓት አከናውነዋል።

በዊዝደም አዳራሽ እየተካሄደ ያለው 14ኛው ዓለም አቀፍ የጥጥ፣ የቴክስታይል እና የአልባሳት እሴት ሰንሰለት አውደ ጥናት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።በዓውደ ጥናቱ ሁለተኛ ቀን በአፍሪካ የጥጥ፣ የቴክስ...
16/05/2026

በዊዝደም አዳራሽ እየተካሄደ ያለው 14ኛው ዓለም አቀፍ የጥጥ፣ የቴክስታይል እና የአልባሳት እሴት ሰንሰለት አውደ ጥናት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

በዓውደ ጥናቱ ሁለተኛ ቀን በአፍሪካ የጥጥ፣ የቴክስታይል እና የአልባሳት ዘርፍ ላይ ያተኮሩ የምርምር ጽሑፎች ቀርበው ውይይቶች እየተካሄደ ይገኛል። በተለይም ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የእሴት ሰንሰለት ማጠናከር፣ ፈጠራና ኢኖቬሽን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት የትብብር አጋጣሚዎች በስፋት ይነሳሉ።
በመድረኩ ላይ የተገኙ ምሁራንና ባለሙያዎች የአፍሪካን የቴክስታይል እና አልባሳት ዘርፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የምርምር ትስስር፣ የኢንዱስትሪ ትብብርና የሰው ኃይል ልማት ወሳኝ መሆናቸውን አፅኖኦት ሰጠው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology:

Share