Bonga University

Bonga University Bonga University is one of the Public Higher Educational Institution in Ethiopia.
(1)

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገለፁ።          :::::::::::::::::::ጳጉሜ 05/2019 ዓ.ም:::::::::::::::::የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝ...
10/09/2026

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገለፁ።

:::::::::::::::::::ጳጉሜ 05/2019 ዓ.ም:::::::::::::::::

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ለመላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው መላው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል።

በተለይ የዘንድሮው 2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ለኛ ለኢትዮጵያውያን በብዙ መልኩ የተለየ መሆኑን ገልፀዋል።

ለዚህም ማሳያው ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ እና የሀገራዊ ምክክርን ባሳካንበት ማግስት መሆኑ አዲሱን ዓመት የተለየ ያደርገዋል።

ይሄም የዴሞክራሲ ባህላችንና እኛ ኢትዮጵያውን ምን ያህል ቁጭ ብሎ የመነጋገር የቆየ ባህል እንዳለን ማሳያ እንደሆነ በአድናቆት ገልፀዋል።

መጪው አዲስ ዓመትም እንደ ዩኒቨርሲቲም እንደ ሀገርም የጀመርናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን የምናሳካበት እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት የበለጠ የምናረጋግጥበት እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለጽ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !!

መልካም አዲስ ዓመት!!

በጋራ እንችላለን!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለሴት አቅመ ደካማ ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።:::::::::: ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም:::::::::::::::ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተ...
09/09/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለሴት አቅመ ደካማ ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

:::::::::: ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም:::::::::::::::

ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተከበረ ያለውን " የህብር ቀን " ምክንያት በማድረግ ለሴት ዓቅመ ደካማ ተማሪዎች ድጋፍ ተደርጓል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ(ዶ/ር) ሲሆኑ በመልዕክታቸውም ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በተለይ በክረምት በጎ ፈቃድ ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንደዚህ አይነት ድጋፍ ሲያደርግ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልፀው በተለይ ሴት ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከት/ት ገበታ መቋረጥ የለባቸውም በሚል ከት/ት ቁሳቁስ በተጨማሪም የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍም ተደርጓል።

ከቦንጋ ከተማ አስ/ር ት/ት ጽ/ቤት ተወክለው የመጡት ወ/ሮ ፍሬህይወት ገሠሠ በበኩላቸው ስለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንደ መሪ ቃሉ ሁሌም ቃል በተግባር የሆነ ተቋም እንደሆነ አውስተዋል።

በጋራ እንችላለን!

08/09/2026
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም ሀገር ዓቀፉን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል። በዚህ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመ...
01/09/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም ሀገር ዓቀፉን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

በዚህ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በመጪው 2019 ዓ.ም. ት/ት ዘመን ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ እንድታደርጉ ግብዣችንን ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው።

በአረንጓዴው ወርቅ መፍለቂያ የሚገኘው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በጉምቱ መምህራኖቹ እና በተደራጀ የቤተ-ሙከራ እና ቤተ-መጽሐፍቱ ያላቸውን ብቃት በመግለጽ ነው።

ከምንም በላይ ከጽንሰ ሀሳብ ባሻገር ለተግባራዊ ትምህርት ቅድሚያ የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲያችን በጤና ሳይንስ ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ በህግ ፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጆቹ የተለያዩ ት/ት ዘርፎች እንዳሉን በመግለጽ ነው።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም በሰላም ተምሳሌነቱ ከመጠቀሱም ባሻገር ተማሪዎች ሁሌም ለደህንነታቸው ሳይሰጉ ዩኒቨርሲቲያችንን መርጠው ሲመጡ የምናደርገው ልዩ አቀባበል ለየት ያደርገናል።

ሌላው እና ተቋማችን ከሚወደስበት ተግባር አንዱ ማራኪው ጊቢያችን ባሻገር ስማርት ክፍሎቻችንና ዲጂታል ቤተ-መጽሀፍታችን ከዓይን ያውጣችሁ ያስባለን የደረስንበት ከፍታ ነው።

ውድ የተማሪ ወላጆች ልጆችዎ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ሲመርጡ ወደ ሌላኛው ቤታቸው እንደመጡ እንድታስቡ እንወዳለን።

ውድ ተማሪዎችም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ በማድረግ የወደፊቷን የበለፀገች ኢትዮጵያን እንገንባ።

ምርጫችሁ አድርጋችሁን ስለምትመጡ በባህላችን ቡና አፍልተን "ቡኖ ኡዮቴ" ብለን እንጠብቃችኋለን።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ !!!

በጋራ እንችላለን!

20/08/2026
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 92.1 ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህል እና ሳይንስ...
18/08/2026

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 92.1 ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህል እና ሳይንስ ተቋም /ዩኔስኮ/ያወጣውን Expression Of Interest /EOI/ For Community Radio Partnership የፕሮግራም ይዘት ውድድር ማሸነፍ ችለናል።

በመሆኑም በቀጣይ በወጣቶች ፣ በሴቶች እንዲሁም በጤና ላይ መስራት የሚያስችለንን መርሀ-ግብር የምናጠናክርበትን አቅም ይፈጥርልናል።

በመሆኑም ለፕሮግራም አዘጋጅ ፣ አቅራቢ እና የሬድዮ ዝግጅት አስተባባሪ የመሳሰሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በቀጣይ የምናገኝ ይሆናል።

ከዚህም ባሻገር የበለጠ ፕሮግራሞቻችን ጥራት እና ይዘት ጨምረው መጓዝ የሚያስችል አቅምም ይፈጥርልናል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሁሌም የተሰጠውን የመንግስት ተልዕኮ ከማሳካት ባሻገር የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ችግሮችን በጥናት እና ምርምር ለመፍታት እየሰራ ያለ የመንግስት ከፍተኛ የት/ት ተቋም ነው።

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!

በጋራ እንችላለን!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለቦንጋ ከተማ  ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።       :::::::::::::: ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም::::::::::::::::ስልጠናው በህይወት ክህሎ...
13/08/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለቦንጋ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

:::::::::::::: ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም::::::::::::::::

ስልጠናው በህይወት ክህሎት ፣ ውጤታማ አመራርነት እና የአደዛዥ ዕፅ ተጠቂነት የሚሉ ርዕሶች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መማ/ማስ/ምር/ቴክ/ማህ/አገ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ልዩ ረዳት መ/ር ጌትነት ገ/ሚካኤል የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ከፍተዋል።

መ/ር ጌትነት በመልዕክታቸው እንደገለፁት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው የክረምት በጎ ተግባራት ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በዝርዝር ገልፀዋል።

የዛሬውም ስልጠና በተለይ ወጣቶችን መሠረት ባደረገ መልኩ ሲያዘጋጅ በምክንያት መሆኑን አውስተዋል።

ተሳታፊ ወጣቶችም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ተገቢውን ክህሎት እንድትጨብጡ በማለት ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል።

ስልጠናውን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መ/ራን የሆኑት ጌትነት ገዛኸኝ (ዶ/ር) እና መ/ር ፍሬው አስረስ በተለያዩ ርዕሶች ላይ እንደሚሰጡ ከወጣው መርሀ-ግብር መረዳት ይቻላል።

ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

በጋራ እንችላለን!

የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር የሁለተኛው ክፍል እና የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ።          ::::::::::::::ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም::::::::::::::ቦንጋ...
12/08/2026

የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር የሁለተኛው ክፍል እና የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ።

::::::::::::::ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም::::::::::::::

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር ከሐምሌ 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል።

በዛሬው የመጨረሻ ቀን መርሀ-ግብር የአንዲት በጥልቅ ድህነት ውስጥ ያለች ሴት የስምንት ልጆች እናት በቦንጋ ከተማ ልዩ ስሙ በሚሽን ሰፈር አካባቢ የቤት እድሳት መርሀ-ግብር በማስጀመር ነበር።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በመርሀ -ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ እንደነዚህ አይነት የማህበረሰብ አገልግሎት እና ሰብዓዊ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ቤት የምናድስላት ሴት ደግሞ እጅግ በጣም ችግረኛ በመሆኗ እኛም የአቅማችንን በማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን ለመወጣት ያስችለናል ብለዋል በዚህም ደስተኞች ነን ብለዋል።

በክቡር ፕሬዝዳንቱ መሪነትም የቤት እድሳቱ የግንባታውን ሂደት በይፋ በማስጀመር ወደ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አረጋውያን ማዕከል ችግኝ ተከላ ፕሮግራም መካሄድ ችሏል።

በአረጋውያን ማዕከል በተከናወነው ፕሮግራም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አልማዝ ሀ/ወልድ የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል።

በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ-ግብር ማጠቃለያ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ቀርቧል።

በመልዕክታቸውም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞችን ለማዕከሉ ለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነው እንደዚህ አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ለማዕከሉ አረጋውያን ረጅምን ዕድሜ ተመኝተዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ የተለያዩ የመንግስት መዋቅሮችን ያመሠገኑ ሲሆን በማጠቃለያው ለአረጋውያኑ ድጋፍ የአልባሳት ፣ የገንዘብ እና የቴምር ድጋፍ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የተላኩትን ስጦታዎች ለአረጋውያኑ በማበርከት የፕሮግራም ፍፃሜ ሆኗል።

በጋራ እንችላለን!

Call for Graduate Program Applications (MSc, MA & PhD)Academic Year: 2019 E.C. (2026/2027 G.C.) Bonga University is plea...
12/08/2026

Call for Graduate Program Applications (MSc, MA & PhD)

Academic Year: 2019 E.C. (2026/2027 G.C.)

Bonga University is pleased to invite applications from qualified candidates for admission to its Master's and Doctor of Philosophy (PhD) degree programs across colleges for government-sponsored and self-sponsored candidates using https://www.bongau.edu.et/pg.php

Application Period
From: 11 August 2026 G.C. (05 Nehase 2018 E.C.)
To: 20 September 2026 G.C. (10 Meskerem 2019 E.C.)

Application Fee Notice

Non-refundable fee of ETB 150.00 payable via Commercial Bank of Ethiopia (CBE) Account No: 1000245740402 ('D' Account).

Important Notice: This online application is for preliminary admission screening only. Shortlisted applicants must present original documents, hard copies, and the original CBE bank deposit slip to the Office of the Registrar during registration for verification. Additionally, uploaded files must be under 2MB.

Applicants residing in or near Bonga may submit their applications in person at the Office of the Registrar, Bonga University.

Together We Can!

Address

Bonga
334

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bonga University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share