10/10/2016
በትምህርት ሚኒስቴር በ2009 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና ነባር መደበኛ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ፤
መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ጥቅምት 9-10/2009 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትገቡ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
1) ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ
2) የ10ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ውጤት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ
3) አንሶላ፣ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
4) ፓስፖርት መጠን ያለው 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውጭ ለሆናችሁ ሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ጥቅምት 18-19/2009ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡