Me n me

Me n me Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Me n me, College & University, Dessie, Dese.

13/10/2021

ጥቅምት 5 በረከቱ ይደርብን ሼር
ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!
አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።
አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።
አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ
ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።
ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።
በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።
በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።
ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።
ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።
ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል። የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ምልጃ በረከት አይለየን..
የድንግል ወዳጆች ከ50ሺ በላይ አባል ያለውን ቴሌግራም ተቀላቀሉ
t.me//JOIN_maryam_amalajinet_TELEGRAM

12/10/2021
03/10/2021

DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2023 Program: Online Registration
DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2023 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም
መልካም እድል ይመኝላቹሀል
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

23/09/2021

Skeleton system of Human body
For more information like Biotech Scholar

19/09/2021

Exploring the future of aerospace, science, and technology. Trusted stories from every angle.

Managed by the National Institute of Aerospace.

18/09/2021

✍ #በተደጋጋሚ #ሽንቶ #እየመጣ #ተቸግረዋል?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለዉ ከሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሲኖር ማለት ነዉ፡፡በተድጋጋሚ ሽንት መሽናት ስራዎን እንቅልፍዎን እና አጠቃላይ ሰላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህም የዚህን ችግር መነሻ እና ህክምናዉን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡

👉 #መንስኤ

📌 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
📌 የስኳር ህመም
📌 እርግዝና
📌 የፕሮስቴት እጢ ችግር
📌 ሽንት የሚያሸኑ መድሀኒቶች መጠቀም
📌 የነርቨ ችግር
📌 የኩላሊት በሽታ
📌 አንዳንድ ለካንሰር የሚሰጡ ህክምናዎች
📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እና መጠጦች

👉 #መፍትሄ

📌 በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት
📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ እንደ ካፌን እና አልኮል ያሉ ንጥረ ነገሮችን መቀነስ
📌 ሽንቶዎን አለመቋጠር
📌 ወደ መኝታ በሚሄዱ ጊዜ ፈሳሽ ነገሮችን አለመጠቀም
📌 ለዳሌ አጥንት የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን መስራት

👉👉 #በተደጋጋሚ ሽንቶ እየመጣ ተቸግረዋል!! ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ 👉
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

( #በጤና # ባለሙያ # ስጦታ )

18/09/2021
18/09/2021
18/09/2021
18/09/2021

14 ሺህ የክላሽ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ደሴ በማድረግ ባህርዳር ከተማ ላይ 14 ሺህ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ዋለ።

በዛሬው ዕለት ከምሽቱ 3:30 ሰዓት መነሻውን ደሴ በማድረግ በመካነሰላም መርጦ ለማሪያም ሞጣ ባ/ዳር መስመር የታርጋ ቁጥር ኮድ3 አአ 59582 የሆነ ሲንግል ካፕ መኪና ሻግ በማሰራት 14 ሺህ የክላሽ ጥይት በደብቅ ሲጓጓዝ ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ሁሴን አህመድ እና መሃመድ አደም ከተባሉ ተጠርጣሪዎች ጋር እጅ ከፍንጅ ከክልሉ ፓሊስ አባላት ጋር በጋራ በመሆን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከመነሻዉ ደሴ ጀምሮ እሰከ መዳረሻዉ ባ/ህርዳር ከተማ ሚስጥራዊ ክትትል በማድረግ ለክልሉ ፖሊስ ጥቆማና መረጃ በመስጠት ተጠርጣሪዎች እንዲያዙና ህገወጥ የግንኙነት መረቡ እንዲበጣጠስ ያደረገዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ነዉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

18/09/2021

የተፈናቃይ ተማሪዎችን ወጪ ሸፍኖ ለማስተማር የተዘጋጀው ወረዳ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) ከሰሜን ወሎ የተፈናቀሉ ተማሪዎችን የአንድ ዓመት ሙሉ ወጪ ሸፍኖ ለማስተማር መወሰኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

አስተዳደሩ ለሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ በጻፈው ደብዳቤ ከዞኑ የተፈናቀሉና በችግር ውስጥ የሚገኙ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎና ተንከባክቦ ለማስተማር ዝግጁ ነኝ ብሏል።

በመሆኑም በአሸባሪው ሕወሓት ወረራና ጥቃት የተፈናቀሉ፣ ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁ፣ ንብረትና ትምህርት ቤት የወደመባቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በግንባር ዘመቻ ላይ ያሉ ተማሪዎች ተለይተው እንዲላኩለት ነው የጠየቀው።

ተማሪዎቹን ተቀብሎና ተንከባክቦ ለማስተማር ደግሞ 57 ትምህርት ቤቶችና የወረዳው ነዋሪዎች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!

Address

Dessie
Dese

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Me n me posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share