ማህደረ ግጥም

ማህደረ ግጥም ይህ የግጥም ስራዎቼን የማቀርብበት ፔጅ ነው። ታዳጊ እንደመሆኔ መጠን join በማለት እያያችሁ ገንቢ አስተያየት እንድትሰጡኝ ስል በአክብሮት እጠይቃለው!!

11/02/2026

መጥኖ የሰራሽ ጥበቡን አብዝቶ
ሁለመናሽ መሳጭ እንከን የለሽ ከቶ
የአጋጣሚ ጉዳይ የዘመን ስልጠና
የእግዚአብሔር ፍቃድ አንቺን አመጣና
የውበትሽ ሳያንስ ትህትናሽ በልጦ
ልቤ አንቺን ይላል ከኔ አንቺን መርጦ
ለበረሃው ልቤ እንደ ሰማይ መና
ለተጎዳው ጎኔ ጠጋኙ ሆንሽና
የግራዬ ጉድለት መጠኑ ሲለካ
የጎደለው አጥንት አንቺ ነበርሽ ለካ
በጣም ነው ምወድሽ የኔ ወገብ ችቦ
ዕጣ ያገናኘኝ ካለሁበት ስቦ
በሰላም በፍቅር ኑሪልኝ በደና
አጊኝቼ እስካቅፍሽ እናፍቃለሁ ገና

18/04/2024

ለመድረስ

23/03/2022

እንኳን ወደዚህ ግሩፕ በደህና መጣችሁ እያልኩ አበረታች ድጋፍና ምክራችሁን እነሆ እላለው!!

21/03/2022

ገና ከጅምሩ፣
ተዋት ተዋት ሲሉኝ፣ሁላቸውንም ትቼ፣
እሷም እኔን ትታኝ፣
እሷን አስባለው፣ብቻየን ተኝቼ።

17/03/2022

የሆንኩትን ነገር፥ለማን አዋያለው፣
አፌን ተለጉሜ፣ሰማዩን አያለው

23/02/2022

ዝምታ
ዝምታ ወርቅ ነው፣ሰው ሲለኝ ሰምቼ፣
ዝም ማለት ጀመርኩ፣መናገሬን ትቼ።
ሲከፋኝም ዝም፣ሲደላኝም ዝም፣
መናገሬን ትቼ፣ሳበዛ መቆዘም፣
ትልቁም ትንሹም፣በኔ ላይ በረታ፣
ሲቅበዘበዝ ያዝኩት፣
የኪሴን ጨርሶ፣ሱሪዬን ሲፈታ፣
ጭራሽ ያለቦታው፣ዝም አትበል ወገኔ፣
አለም ዝብርቅርቅ ናት፣ማትፈታ ቅኔ።
ፍፁም ያለቦታው፣እንዲሁ ዝም ማለት፣
ይቆይ ይሆን እንጂ፣
ማምጣቱ አይቀርም፣የአየር ጋንኤልነት።

የአመለኛ ውሻዬ፣የሰሞኑ ፀባይ፣አስገረመኝ በጣም፣ተናካሽ ሰዎችን፣መንደር ላይ ፈርቷቸው፣ከቤት ውስጥ አይወጣም፣
21/02/2022

የአመለኛ ውሻዬ፣
የሰሞኑ ፀባይ፣አስገረመኝ በጣም፣
ተናካሽ ሰዎችን፣
መንደር ላይ ፈርቷቸው፣ከቤት ውስጥ አይወጣም፣

Address

Chemendefer
Dire Dawa
DIRE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማህደረ ግጥም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to ማህደረ ግጥም:

Share