04/06/2026
አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ሚሊዮን ዶላሮችን በመስረቅ ወንጀል ተከስሶ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ቅጣቱን ከተቀበለ ከአንድ ዓመት በኋላ አባቱ ደብዳቤ ይልክለታል፦«ውድ ልጄ በእርጅናዬና በሕመሜ ጊዜ ለምን ብቻዬን ተዉከኝ፤ ታውቃለህ የእርሻ ወቅት ደርሷል መሬቱን ለመቆፈርና ድንች ለመተከል የሚረዳኝ ሰው ከአጠገቤ የለም። ድንች መትከል ቀላል ነው ነገር ግን በዚህ አቅሜ መቆፈር አልችልም። ዛሬ ላይ አንተ ታስረሃል እና እንደምንም መሞከሬ የማይቀር ነው። በፈጣሪ ፈቃድ እንደገና እንገናኛለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።»
ልጅም ከእስር ቤት እንዳለ ለአባቱ መልሶ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፈለት፦«የእኔ ውድ አባት እባክህን አሁን ላይ መሬቱን መቆፈር የለብህም። የሰረቅኩትን ገንዘብ በጠቅላላ የእርሻ መሬቱ ላይ ስለቀበርኩት አንተ ላይ አደጋ ያመጣብሃል። ስለዚህ እስከምፈታ ድረስ ጠብቅ።»
በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ውስጥ ሆነ ወደውጭ የሚተላለፍ የእስረኞች ደብዳቤ ስለሚነበብ ምስጥሩ ወዲያው ተደረሰበት። በማግስቱ ጠዋትም ከመቶ በላይ ፖሊሶች ወደ አባቱ ቤት በመሄድ አንድም ሳይቀር የእርሻውን መሬት ቆፋፈሩት። ቢሆንም ግን ለሰዓታት ቢቆፍሩ ምንም አላገኙም ነበር።
ከሦስት ቀን በኋላ ልጁ ለአባቱ ድጋሚ ደብዳቤ ጻፈለት፦«ውድ አባቴ የላኩልህን የሰው ኃይሎች እንደተጠቀምክ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ድንች መትከል ትችላለህ።» 🤗