Dire dawa university ethiopia

Dire dawa university ethiopia COME AND LEARN FOR KNOWLEDGE

ማስታወቂያበድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
06/05/2022

ማስታወቂያ
በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ የፕሮግራም ጥቆማ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ፊልም ...
05/05/2022

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ
የፕሮግራም ጥቆማ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ፊልም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዛሬ ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ከዜና ሰዓት በኃላ የሚቀርብ ስለሆነ እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል!!!ኢድ ሙባረክድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
02/05/2022

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል!!!

ኢድ ሙባረክ
ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ

Dire-Dawa UniversityStrategic Partnership & Internationalization DirectorateCICOPS SCHOLARSHIPS 2023 (ITALY)
27/03/2022

Dire-Dawa University
Strategic Partnership & Internationalization Directorate
CICOPS SCHOLARSHIPS 2023 (ITALY)

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን "እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። "እኔ የእህቴ ጠባ...
09/03/2022

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን "እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል የዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (MARCH 8) ዛሬ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተከበረ ሲሆን በዚሁ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት ሴቶች ለዘመናት በተዛቡ አስተሳሰቦች ሳቢያ ለተለያዩ ወስብስብ ችግሮች ተጋልጠው ቆይተዋል፡፡
ምንም እነኳን ይህን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ በርካታ ጥረቶች መደረጋቸው ባይካድም እነዚህ ጥረቶች ትርጉም ባለው መልኩ የሴቶችን ችግር ቀርፈዋል ብሎ ለመናገር ያስቸግራል ብለዋል፡፡
ሴቶች ያሉባቸው ችግሮች በዘላቂነት ተቀርፈው በሁሉም መስክ ተጣቃሚነታቸውን እና ተሳታፊነታቸውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ራሳቸው ሴቶች ችግሮቻቸው እንዲፈቱ በፊትአውራሪነት ተሰልፈው የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸዋለ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሴቶችን ችግር ከመፍታ አንፃርም በአሁኑ ሰዓት ልጅን ተንከባክቦ ለማሳደግ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቅርቡ የህፃናት ማቆያ መዕከል ግንባታ መጀመሩን ዶ/ር ኡባህ ጠቁመው ይህ የህፃናት ማቆያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር ድረስም በጊዜያዊነት በዩኒቨርሲቲው የተወሰኑ ክፍት የህንፃ ክፍሎችን ምቹ በማድረግ አገልግሎቱን በማስጀመር የሴቶችን ውጤታማነት ለማሳደግ ጥረት አንደሚደረግ ገልፀው ለዙሁ ስኬትም ሁሉም አካል የበኩሉን ይወጣ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የድሬደዋ ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ኢፍቱ አባስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት እኛ ሴቶች የሚደርስብንን ጫና እና ተፅእኖ ተቋቁመን በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ መሆን ይጠበቅብናል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ወጣቶች፣ ኤች.አይ.ቪ /ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ይታገሱ ፍቃዱ በበኩላቸው ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ ከራሳቸው ከሴቶች ብዙ ይጠበቃል ሴቶች በትምህርት እና በእውቀት አቅማቸውን በየጊዜው በማጎልበት ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (MARCH 8) በማስመልከት በተከበረው በዓል ላይ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ያሉ ተስፋዎችና ሊያጋጥም የሚችሉ ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ በመምህር ቅድስና ሰብስቤ ጥናታዊ ጽኁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም በበዓሉ ላይ የተገኘውን ታዳሚ የሚያዝናኑ የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉና በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ለቻሉ ሴት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የእግር ኳስ ጤና ቡድን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እግር ኳስ ጤና ቡድን ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ አደረገ፡፡ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
09/03/2022

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የእግር ኳስ ጤና ቡድን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እግር ኳስ ጤና ቡድን ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ አደረገ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የጤና ቡድኑ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ቡድን በቀረበለት ጥሪ ሀዋሳ በመገኘት ባደረገው ጨዋታ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ጤና ቡድን ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት ግዜ (1999 ዓ.ም) ጀምሮ ተቋሙን በመወከል ከተለያዩ ተቋማት ጤና ቡድን ጋር ውድድሮችን እያከናወነ ያለ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ በየዓመቱ በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በተቋማት መካከል በሚደረገው ውድድር ላይ በቋሚነት ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

የዓለም የምህንድስና ቀን "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የ...
09/03/2022

የዓለም የምህንድስና ቀን "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ደርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የምህንድስና ቀን በየዓመቱ የካቲት 25 ቀን እንዲከበር ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የዘንድሮው የምህንድስና ቀንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃም ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ቀኑን በማስመልከት በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት መድረክ ላይ በምህንድስናው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቅና ያላቸው ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡
የበዓሉን አከባበር በይፋ የከፈቱት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ክብርት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዳሉት ምህንድስና የሰው ልጅን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላትና የአኗኗር ስርዓትን ለማሻሻል እንዲሁም ዘላቂ የሆኑ የልማት እድሎችን በመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ታውቆ በተባበሩት መንግስታት የልማት ግቦች ላይ በሰፊው በመስራት በዜጎች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣትና ግቦቹን ለማሳካት የተለያዩ አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የምህንድስናውን ዘርፍ በማሳደግ በሀገራች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የራሱን ድርሻ ወስዶ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን ላይ መሆኑን በመግለፅ፤ ለሀገራችንና ለአካባቢው አገሮች የምስራቁ ክፍል የኢንዱስትሪ ኮሪደር እንድትሆን የተመረጠችው ድሬደዋ የሰነቀቸውን ርዕይ ማሳካት እንድትችል የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስናው ዘርፍ የሰለጠነና ብቁ የሰውኃይል በማፍራት እንዲሁም በድሬደዋና በአካባቢዋ ከሚገኙ ኢንድስትሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ በብቃት ለመወጣት እየሰራ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዘዳንተር ዶ/ር ኡባህ አደም አስታውቀዋል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የድሬደዋ ቴክኖሎጂ ኢነስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ገደፋየ በዚሁ በዓል ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የምህንድስና ቀን ሲከበር የዛሬው የመጀመሪያ መሆኑን ጠቁመው ምህንድስና ዓለም በየዘመኑ ሲያጋጥማት ለነበረው ቀውስ መፍትሄ ከመስጥ እንፃር የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በመግለፅ ዘርፉ ችግር ፈቺነቱ እንዳለ ሆኖ ግን በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት የሚታዩ ውስንነቶች ስፋት ያላቸው በመሆኑ እነዚህን ክፍተቶች ለማጥበብም እንደ ዛሬው አይነት በምህንድስናው ዘርፍ የሚገኙ ባለሙያዎችን በእንድነት የሚያሰባስብ መድረክ መዘጋጀቱ ወሳኝ በመሆኑ ይሄው ተግባር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የምህንድሳ ቀን በማስመልከት ለአንድ ቀን በቆየው መድረክ ላይ በምህንድስናው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቀት ያላቸው የዘርፉ ምሁራን ዘላቂ ልማት እና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና በተሰኙ ርዕሶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ኃይል ልማት፣ በመማር ማስተማር እና ጥናትና ምርምር ላይ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የብዝኃነት ፎረም  "ብዝኃነታችን ለብልጽግናችን"  በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ይገኛል፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የድሬደዋ ዩኒ...
09/03/2022

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የብዝኃነት ፎረም "ብዝኃነታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ይገኛል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ "ብዝኃነታችን ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያውን የብዝኃነት ፎረም በዛሬው እለት በቢፍቱ ሞል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ሲሆን በፎረሙ ላይ በመገኘት የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ እንደተናገሩት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ከሚያከናውነው ሀገራዊ ተልዕኮው ጎን ለጎን እንደ ሀገር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን የጋራ የምክከር መድረኮችን በማሰናዳት ትልቅ ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ሀርቢ አክለውም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ድሬደዋ ከቅርብ ዓመት ወዲህ ልዩነትን ባልተገባ መንገድ በመጠቀም በህዝቦች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ጠንካራ ትስስርን ለማላላት የሞከሩ እኩይ ተግባራት ተፈፅመዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ከፋፋይና እጥፊ የሆነ እኩይ ድርጊት ዳግም ተመልሶ የህዝባች ስጋትና የልማታችን ማነቆ እንዳይሆን በግልፅ የመወያየት ባህላችንን በማዳበር በሀገራችን ሰለምና ደህንነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ቤተ እምነቶች፣ የትምህርት ተቋማት እና የሚዲያ አካላት የሚኖራቸው ሚና የጎላ በመሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳነት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ሀገራችን የበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ከመሆኗም ባሻገር የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት እና የተለያዩ ሀይማኖትች የሚገኙባት ሀገር እንደመሆኗ ብዝኃነት ማስተናገድ ይኖርባታል ብለዋል።

ዶ/ር ኡባህ አክለው ከ70 በላይ ብሔር ፣ ብሔረሰብና ህዝቦች የሚኖሩባት የትንሻ ኢትዮጵያ ተምሳሌት ተብላ የምትጠራው ድሬደዋም ያላትን ተከባብሮ በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር እሴቷን በአግባቡ መጠቀም እንዲቻልና ለተቀረው የሀገራችን ክፍልም ለማስተዋወቅ የዚህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸው ያላቸው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በመሆኑ የድሬደዋ ከተማ ከብዝኃነት አንፃር ያሏትን ፀጋዎች ተጠቅመን ለዲሞክራሲ ግንባታ፣ ለህዝቦች እኩልነት ፣ ለፍትሀዊ ተጠቃሚነት መዋል እንዲቻል ታስቦ ፎረሙ መዘጋጀቱን የገለፁት ዶ/ር ኡባህ እንደዚህ አይነት መድረኮች ቀጣይነት ይኖረዋል ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በበኩላቸው በብዝኃነት ፎረሙ መድረክ እስካሁን ያለፈበትን ሂደትና በቀጣይ ሚኖረውን ገፅታ የሚያሳይ ጥናት አቅርበዋል፡፡

በፎረሙ ላይ ተዋቂው ምሁር፣ ደራሲ ገጣሚ እና ተመራማሪ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የመድረኩን ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ብዝኃነትን የሚያስተናግድ ትውልድ ለመፍጠር ከእንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ መሰራት ይኖርበታል ለዚህ ስኬትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በፎረሙ ላይ ተገኝተው ብዝኃነት በኢትዮጵያ ትናት፣ ዛሬ እና ነገ በሚለ ዶ/ር ንጉሱ አክሊሉ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

የድሬዳዋን ባህልና እሴት ለሌሎች የማስተዋወቅ እንዲሁም ሀገር አቀፍ የብዝሀነት ጉዳዮች ላይ መሰረት በማድረግ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የመጀመሪያው "የብዝሃነት ፎረም" እየተካሄደ ይገኛ...
09/03/2022

የድሬዳዋን ባህልና እሴት ለሌሎች የማስተዋወቅ እንዲሁም ሀገር አቀፍ የብዝሀነት ጉዳዮች ላይ መሰረት በማድረግ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የመጀመሪያው "የብዝሃነት ፎረም" እየተካሄደ ይገኛል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

የዓለም የምህንድሳ ቀን "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ ነው፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የተባበሩት መንግስታት የትም...
09/03/2022

የዓለም የምህንድሳ ቀን "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ ነው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ደርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የምህንድስና ቀን ሁሌም የካቲት 25 ቀን እንዲከበር ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የዘንድሮው የምህንድስና ቀንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃም ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ "ምህንድስና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ሲሆን ቀኑን በማስመልከት በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ በምህንድስናው ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድና እውቅና ያላቸው ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

World Engineering Day
09/03/2022

World Engineering Day

126 ኛው የአደዋ የድል በዓል "ዓድዋ የኢትዮጵያ እና የጥቁር ህዝቦች የሉአላዊነት መገለጫ" በሚል ርዕስ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
01/03/2022

126 ኛው የአደዋ የድል በዓል "ዓድዋ የኢትዮጵያ እና የጥቁር ህዝቦች የሉአላዊነት መገለጫ" በሚል ርዕስ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደገለጹት የአደዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።
ይህን የትናንት ገድላችን ወኔ ሆኖን ዛሬ ላይ የተሻለ ስራ መስራት እንድንችል ታሪክን መማርና ማወቅ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የፓናል ውይይቱ ሊዘጋጅ መቻሉን ዶ/ር ሰለሞን ገልፀው የዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ባለቤትነት የዚህ አይነቱን ትልቅ ዝግጅት ማሰናዳት መቻሉ የሚበረታታና በዩኒቨርሲቲው የሚገኙት ሌሎች የትምህርት ክፍሎችም በአርያነት ሊከተሉት የሚገባ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አባቶቻችን በእብሪት ተነስቶ ሃገራችንን ለመውረር የመጣውን ቀኝ ገዢ ኃይል ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለው የዓለምን ታሪክ መቀየር እንደቻሉት ሁሉ እኛ ልጆቻቸውም ልዩነቶቻችንን አቻችለን በአንድነት ከፊታችን የተጋረጠብንን ችግር በድል መወጣት ይገባናል ያሉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በተለይም በዘመናችን የሀገራችን ቀንድኛ ጠላት የሆኑትን ድህነትና ኋላቀርነት ላይ የተባበረ ክንዳችን በማሳረፍ የህዝባችን ኑሮ እንዲሻሻል ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ ስራ በመስራት የሚጠበቅብንን እንወጣ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

126 ኛውን የአደዋ ድል በአል ምክንያት በማድረግ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር የትምህርት ክፍል ከማህበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ " ሥነ-ጽሁፋዊ ምሰላና ድምፅ አልባዎቹ የዓድዋ ድል ባለቤቶች" እና "የአድዋ ጦርነትና ለቱሪዝም ሃብትነት ያለው አቅም " የሚል ርዕስ ያላቸው ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የአደዋን ድልን የሚዘክር የኪነ- ጥበብ ዝግጅት በድሬደዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በሚሊንየም የባህልና የኪነጥበብ ቡድን ቀርቧል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw

Address

Dire Dawa

Telephone

+251251111501

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire dawa university ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share