20/06/2026
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ እውቅና እና ሽልማት ተበርከተለት
👇👇👇👇👇👇
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተቋማትን አሰራር የሚያዘምኑ እንዲሁም አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ ለተለያዩ ተቋማት በማበርከት ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለአስተዳደሩ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ላበረከተው ዘመናዊ ሶፍትዌሮች ከፍተኛ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በዚሁ የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት ‘’የድሬዳዋ ፓሊስ መምሪያ የጀመራቸውን የሪፎርም ስራዎች በማገዝ እንዲሁም ለአስተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መስፈን ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችን በማበርከት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ጉልህ ድርሻ አለው’’ ብለዋል፡፡
ከንቲባው አክለውም በአሰራር ክፍተቶች ሳቢያ ወቀሳ ይሰነዘርበት የነበረውን ተቋም የተሸለ ተቋማዊ ቁመና እንዲኖረው፣ በሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት እና ጥራት የተመሰገነ ተቋም መሆን ችሏል ያሉ ሲሆን አክለውም " ይህንን ምስጉን ተቋም ለመገንባት በቁርጠኝነት የተሳተፉ የአመራር አካላት እና የሪፎርሙ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና አመራሮች ሊመሰገኑ ይገባል" ብለዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው፤ የፖሊስን አደረጃጀት፣ አሠራር እና የሰው ኃይል ለማዘመን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተፈጠረው ጠንካራ ትብብር ስድስት ሶፍትዌሮችን ማበልጸግ መቻሉን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ "ሃያ አራት ሰባት" (24/7) የተባለውን የዳታ አያያዝ ሥርዓት በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ ወጣቶችን ማፍራት መቻሉን ጠቁመዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እውቅናውን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት "የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካባቢያዊ እና ሀገራዊ እንድምታቸው የጎላ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም ለዲጂታል ኢትዮጲያ 2030 ስኬት ጉልህ አበርክቶ የሚኖራቸውን ቴክኖሎጂዎች ከተለያዩ የፌደራል እና ክልል ተቋማት ጋር በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ኡባህ አያይዘውም የዛሬውን እውቅና ላበረከተው የድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ በዩኒቨርሲቲው እና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድሬዳዋ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)
ለበለጠ መረጃ
👉 ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
?Dire-Dawa University/DDUniv/
?? ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
👉 ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/”