MWU GRH Public Relation Office

MWU GRH Public Relation Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MWU GRH Public Relation Office, College & University, Bale Goba, Goba.

10/09/2020

The National Academic Digital Library of Ethiopia (NADLE) is a project under Ministry of Science and Higher Education, Ethiopia. The objective is to collect and collate metadata and provide full text index from several national and international digital libraries, as well as other relevant sources.....

09/09/2020

ማስታወቂያ
ለመላው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰብ:

።።።
በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ብለን መግለጻችንም ይታወቃል።

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እያሳወቅን እስከዛው ድረስ የቫይረሱን ስርጭት ለመከለካል የሚያስችል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ከክፍያ ነጻ በሆነው የዲጂታል ላይበራሪያችን http://ndl.ethernet.edu.et በመግባት አጋዥ መጻህፍትን እያነበባችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

።።።።።
https://t.me/MinistryoSHE
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ነው።
ይቀላቀሉና በሌላ አማራጭ ትክክለኛ መረጃ ያግኙ።

08/09/2020

ሞትን አይቼ ተመለስኩ

የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮ-ሜዳ አካባቢ ነው የምኖረው፡፡ አስታውሳለሁ ቀኑ ሰኔ 16 ሐሙስ ዕለት ነው፤ ካለወትሮዬ ምቾት የሚነሳ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ስረበሽ ነበር የዋልኩት፡፡ ማታ ላይ ምግብ ባያሰኘኝም በግድ ቀምሼ ተኛሁ፡፡

እኩለ ሌሊት ብን ብን የሚል ደረቅ ሳል ድንገት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፤ ሰውነቴም በሚነድ እሳት ውስጥ እንዳለ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ባኞ ቤት ገባሁና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጠብኩ ሊበርድ አልቻለም፡፡ አፌ ስለደረቀና ስለመረረኝ በውሃ ተጉመጠመጥኩት፤ እንደማቅለሽለሽ አለኝ፡፡

ተከራይቼ ስለምኖር በወቅቱ አጠገቤ የሚረዳኝ ሰው አልነበረምና እማደርገው አጣሁ፡፡ ቆይቼ ለጓደኛዬ ደውዬ እንደታመመኩ ነገርኩት፡፡ መኪና ይዞ መጣና ወደ አቅራቢያዬ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወሰደኝ፤ እነሱም ሁኔታውን አይተው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላኩኝ፡፡ የሆስፒታሉ ሃኪሞችና ነርሶች ተረባረቡና አስገቡኝ፡፡ ወዲውኑ ምርመራ ታዞልኝ ናሙና እንድሰጥ ተደረገ፡፡ ትኩሳቱ እየጨመረ መጣ፤ አጠገቤ የሚረዱኝን የጤና ባለሙያዎች ጭምር የሰውነቴ ግለት ይታወቃቸው ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እየደከመኝ እየደከመኝ መጣ፡፡

የምርመራ ውጤቴ ደረሰ፤ ውጤቱም የኮሮና ቫይረስ በሽታ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከዚያ በኋላ የሆንኩትን ሁሉ በውል አላቀውቅም ነበር፡፡
ከ7 ቀናት በኋላ ከሰመመን ስሜቴ ወጥቼ ራሴን ሳውቅ በአፍንጫዬ ቱቦ እና በእጄ ላይ ደግሞ ግሉኮስ ተተክሎልኛል፤ በዙሪያዬ ደግሞ መላ አካላቸውን በተሸፈኑ ጤና ባለሙያዎች ተከብቤ አገኘሁት፡፡ ድንጋጤ አይሉት የመረበሽ ሰሜት ተሰማኝ፤ ከአጠገቤ የነበረ ሃኪም ሊያረጋጋኝ ሞከረ፡፡ አይኖቼ በእምባ ተሞሉ፡፡

ቀስ በቀስም ራሴን እያወቅሁ ስሄድ ወደኋላ እንደህልም ያየሁትን ማስታወስ ጀመርኩ፤ ነጭ የለበሱ የለበሱ ሰዎች አጅበውኝ ይዘውኝ ሲሄዱ ያየሁት ታወሰኝ፡፡ ሰፊ አዳራሽ ያለው ዙሪያ ገባው በአበቦች ያጌጠ ውብ ቦታም ይታወሰኛል፡፡ እንዲህ አይነት ስፍራ በምድር ላይ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ምንድን ነው ነገሩ ብዬም ራሴን ጠየኩ፡፡

በተደረገልኝ ህክምናና እንክብካቤ ራሴን በደንብ እያወኩኝ ስመጣ ያ ያየሁት ነገር በሞትና በህይወት መካከል የነበርኩበትን ወቅት በማስታወስ ላይ እንደነበርኩ ተረዳሁ፡፡ ሳልሞት ሞትን አይቼ እንድመለስ የረዳኝን ፈጣሪ እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ፡፡
እኛ የምናውቀው በሽታ ሲያመን ሰው እንዳያስታምመንና እንዳይጠይቀን እስከ መከልከል የሚያደርስ አልነበረም፡፡ ኮሮና ግን የተለየ ነው፤ ቤተሰብ እንኳ ከጎኔ ሆኖ እንዲያስታምመኝ ያለፈቀደልኝ ጨካኝ በሽታ ነው፡፡

ከምንም በላይ ግን የህክም እርዳታና እንክብካቤ ያደረጉልኝን የጤና ባለሙያዎች በእጅጉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፤ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ክፉ አይንካቸው፡፡

ቀድሞ ያልታዬኝ ስህተቴ አሁን ላይ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል፤ ለበሽታው የነበረኝ ግዴለሽነት ዋጋ አስከፍሎኛል፡፡ እኔ እድሉን አግኝቼ ታክሜ መዳኔ ቢያስደስተኝም አሁን ላይ ጤና ተቋማት ወደ መጨናነቅ ደረጃ እየደረሱ መሆኑን ስሰማ በእጅጉ አሳዝኖኛል፤ ችግሩን ቀምሸዋለሁና፡፡ እናም ወገኖቼ ከእኔ ተማሩ፤ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ በማድረግ ከኮሮና በሽታ ራሳችንና ቤተሰባችንን እንጠብቅ መልዕክቴ ነው፡፡

(ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያገገመ ግለሰብ ታሪክ፤ ስሙ በግል ጉዳዩ ምክንያት ያልተጠቀሰ)

https://youtu.be/8c_UJwLq8PI
02/09/2020

https://youtu.be/8c_UJwLq8PI

The formal declaration of a does not change the fact that you can - and should - take these simple steps to protect yourself and your love...

01/09/2020
MWU Goba Referral Hospital Library
01/09/2020

MWU Goba Referral Hospital Library

Congratulations to all our Madda Walabu University  PGs.
22/08/2020

Congratulations to all our Madda Walabu University PGs.

09/08/2020

በቀን እስከ 400 ናሙና መመርመር የሚችለው የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከል ስራ ጀመረ፡፡

09/08/2020

የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ከፍቶ ስራ አስጀመረ 4 Share Email Facebook Twitter Google+ Viber Linkedin Telegram Pinterest WhatsApp ReddIt Tumblr StumbleUpon VK Digg LINE ጎባ፣  ነሃሴ 3/2012 (ኢዜአ) የመዳ ወ....

Address

Bale Goba
Goba
302

Telephone

+251929381738

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MWU GRH Public Relation Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to MWU GRH Public Relation Office:

Share