University of Gondar

University of Gondar The University of Gondar is an esteemed institution of higher learning in Ethiopia, founded in 1954.
(4)

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዕድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል (CEED) ለ2018 ዓ.ም ዕጩ ምሩቃን በሥራ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ዙሪያ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡********************...
21/06/2026

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዕድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል (CEED) ለ2018 ዓ.ም ዕጩ ምሩቃን በሥራ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ዙሪያ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡
*************************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዕድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል (CEED) ለ2018 ዓ.ም ዕጩ ምሩቃን ስልጠናውን ከሰኔ 13-14/2018 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች የሰጠ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል።

የሥራ ዕድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ገብሬ ሙሉዓለም ስልጠናውን አስመልክተው እንደተናገሩት “ይህ የምሩቃን ሥልጠና በዓላማ-መር ሕይወት (Purpose-Driven Life)፣ ራስን ማወቅና ግላዊ ክህሎትን ማሳደግ ፣ በሥራ ዝግጁነት ክህሎት (Employability Skills) እና በሥራ ፈጣሪነት (Entrepreneurship) ዙሪያ ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር ገብሬ አክለውም “ይህ ሥልጠና ተማሪዎቻችን ከተለመደው የአካዳሚክ ዕውቀት ባሻገር ወደ ሥራው ዓለም ሲቀላቀሉ ተወዳዳሪና ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ትልቅ ድልድይ ነው" ሲሉ ገልፀዋል። ምሩቃን ወደፊት በቅጥር ላይ ብቻ ሳይወሰኑ በሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ የታነጹና በሀገር ኢኮኖሚ የራሳቸውን አወንታዊ አሻራ የሚያሳርፉ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሥልጠናውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተሰጠው የዋና አሰልጣኞች ሥልጠና (Master Trainers) የሰለጠኑ 38 አሰልጣኝ መምህራን እየመሩት ይገኛል። የሥልጠናው ይዘትና ዝግጅት ከተማሪዎቹ ፍላጎት ጋር እጅግ በጣም የተናበበ በመሆኑ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች አስቀድመው እንዲረዱና በራስ መተማመን እንዲገነቡ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ያነጋገርናቸው አስልጣኞች ገልፀዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ ዕጩ ምሩቃን በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በተለይ በተግባር ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች (የበዙበት በመሆኑ ክህሎታችን በተጨባጭ ለመፈተሽ እንደረዳንና ወደ ሥራው ዓለም ለመግባት ትልቅ ስንቅና መነሳሳት ፈጥሮብናል፤ ወደፊትም ይህ አይነቱ ሥልጠና በተቋሙ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” በማለት ገልፀዋል፡፡

የገበያውን ዓለም መሠረት ያደረገው ይህ ሥልጠና ዛሬ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም በስኬት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ምሩቃኑ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም “ከትምህርት ወደ ሥራ ዓለም” በሚል መሪ ቃል የአሠሪ ድርጅቶችና አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚሳተፉበትና በልዩ ሁኔታ በተቋሙ በድምቀት በሚከበረው ዓመታዊ የሥራ ትስስር መድረክ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ዶ/ር ገብሬ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።
********
ለልህቀት እንተጋለን.
የዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ
ሰኔ 14/2018 ዓ.ም.

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ከነርቸር ፕሮጀክት (NURTURE Project) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተመራቂ ተማሪዎች የፋይናል ፕሮጀክት የውድድር መድረክ (Graduate Fin...
20/06/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ከነርቸር ፕሮጀክት (NURTURE Project) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተመራቂ ተማሪዎች የፋይናል ፕሮጀክት የውድድር መድረክ (Graduate Final Project - Competition Challenge) ላይ እንዲገኙ ጋብዞዎታል!

የዕለቱ ዋና ዋና ሁነቶች፦
የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን፦ የወደፊት ዲጂታል መፍትሄዎችን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይመለከታሉ፤ ለተቋምዎ የሚሆኑ አዋጭ የዲጂታል መፍትሄዎችንም ይመርጣሉ።

የሽልማት ሥነ-ስርዓት፦ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት (15,000 ETB፣ 10,000 ETB እና 7,000 ETB) እንዲሁም የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከታል።

የትስስር መድረክ (Networking)፦ ከተመራቂ ወጣቶችና ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር ትስስር የሚፈጠርበት ምቹ አጋጣሚ እንደሚሆንም ይታመናል።

ሁነቱ የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ፦
ቦታ፦ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ፣ PG አዳራሽ (College of Informatics PG Hall)
ቀን፦ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. (June 24, 2026)

ሰዓት፦ ጠዋት 2:30

የነገዎቹን የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል በመገኘት እንዲያበረታቱ እና ለተቋምዎ የሚሆኑ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያበረታቱ በአክብሮት ተጋብዘዋል!

Graduate Final Project – Competition Challenge

The College of Informatics, in collaboration with the NURTURE Project, cordially invites you to the Graduate Final Project Competition Challenge. Join us to support our graduating students and discover cutting-edge digital solutions tailored for your institution!

Key Highlights of the Event

👉Innovation Exhibition: Explore future-ready digital solutions and technological advancements. A prime opportunity to scout viable digital products for your organization.

👉 Award Ceremony: Celebrating excellence with attractive cash prizes for top performers—1st Place (15,000 ETB), 2nd Place (10,000 ETB), and 3rd Place (7,000 ETB)—along with Certificates of Achievement.

🤝 Industry-Academia Linkage: A dynamic networking platform to connect talent with potential industries and sector experts.

Event Details@

👉 Venue: College of Informatics, PG Hall

👉 Date: June 24, 2026

👉 Time: 2:30 Local Time (8:30 AM)

Be there to empower tomorrow's tech leaders in person and explore innovative breakthroughs ready for institutional adoption. Your presence is highly valued!

20/06/2026
ለቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቀቀ************በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 4 -12/2018 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች  የመውጫ ...
19/06/2026

ለቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቀቀ
************

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 4 -12/2018 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

ከሰኔ 4 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወቁት ምክትል ፕሬዝዳንቱ የፈተና ግብረ ሀይሉን ጨምሮ የፀጥታ ዘርፍ አባላት፣ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የስራ ሀላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አመስግነዋል።

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ግቢ የፈተና ማዕከል ሀላፊ የሆኑት አቶ ጋዲሳ ወንዶ በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው የፈተናው ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተፈተኛ ተማሪዎች በቂ ገለፃ በመስጠት እና ከአመራሩ ጋር በቅርበት በመነጋገር ያለፉትን ሰባት የፈተና ቀናት ካለምንም የዲሲፒሊን ችግር ፈተናውን በሰላም ማጠናቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው ቆይታ ከአቀባበል ጀምሮ ለተደረገላቸው መልካም መስተንግዶ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በፈተናው ወቅት የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ አካላትን አመስግነዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት በዩኒቨርሲቲው ከሰኔ 4 -12/2018 ዓ.ም በተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከ6759 በላይ እጩ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ሦስት ግቢዎች (ማራኪ፣ ቴዎድሮስና ፋሲል) የመውጫ ፈተናውን ወስደዋል።
************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ 60 ሚሊዮን ብር  የሚገመትና በቀዶ ሕክምና ዘርፍ  የላቀ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ማይክሮስኮፕ  ድጋፍ ተደረገ*****ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና...
19/06/2026

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመትና በቀዶ ሕክምና ዘርፍ የላቀ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ማይክሮስኮፕ ድጋፍ ተደረገ
*****
ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለውና የአንጎልና ህብለ ሰረሰር (Neurosurgery) ቀዶ ህክምና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ዘመናዊ የኒውሮሰርጂካል ማይክሮስኮፕ ሰኔ 12/2018 ዓ. ም በሆስፒታሉ ግቢ በእርዳታ ተበርክቷል።

በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታው ብርሃን፣ ደምስ ሙላቱ የህ.ጤ.ሳ.ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆስ የጤና ትምህርትና የህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር፣
ዶ/ር ምናርጓቸው አጣናው የህ.ጤ.ሳ.ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆስ የህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ምክትል ዳይሬክተር፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአንጎልና ህብለ ሰረሰር (Neurosurgery) ሀኪምና ድጋፍ አፈላላጊ ዶ/ር ኢሳያስ አደፍርስ፣ እንዲሁም በሪች አናዘር'' (Reach Another) በኩል ዶ/ር ቢኒያም ባህሩና ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ተገኝተዋል።

ይህ ዘመናዊ መሣሪያ ''ሪች አናዘር'' (Reach Another) ከተሰኘ በጎ አድራጎት ድርጅት የተገኘ ሲሆን የመጨረሻ ደረጃ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ክህሎት የተገጠመለትና አደገኛና በጣም ጥቃቅን በሆኑ የአንጎልና ህብለ ሰረሰር ክፍሎች ውስጥ የሚከሰቱ እጢዎችን በቀዶ ህክምና ለማከም ወደር የለሽ ነው ተብሏል ።

ይህ መሳሪያ በኮሌጁ የኒውሮ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ጥራትን በእጅጉ የሚያሻሽል ሲሆን፣ በተለይም የአንጎል፣ የነርቭና የህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና በከፍተኛ ጥራት አገልግሎት ለመስጠትና ብዙ ታካሚዎችን ለማስተናገድ አዲስ አቅም የሚፈጥር ነው።

በተጨማሪም ለዚሁ ቀዶ ህክምና የሚውል ጭንቅላትን ለህክምናው በሚፈለገው አቀማመጥ ለማስቀመጥ የሚያግዝ (Mayfield Head Fixation system) የተባለ መሳሪያም እገዛ ተደርጓል።

ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ጋር ከ10 ዓመታት በላይ የቆየ ጠንካራና ዘላቂ አጋርነት ያለው ''ሪች አናዘር'' (Reach Another) ግብረ ሰናይ ድርጅት ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ጊዜያት ''አልትራ ሳውንድ''' ( Ultrasound) መሳሪያ በማቅረብ፣ የህጻናት ፊዚዮ ቴራፒ አገልግሎት መስጫን በማደስና ሌሎች የህክምና ድጋፎችን በማበርከት አጋርነቱን አሳይቷል።

ዛሬ የተገጠመውና ለአግልግሎት ዝግጁ የሆነው የኒውሮሰርጂካል ማይክሮስኮፕ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰጠውን የኒውሮ ሰርጀሪ ህክምና አቅምና ጥራት ከመሰረታዊ ኒዩሮ ሰርጀሪ ወደ Micro-Neurosurgery በማሸጋገር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይህም በአካባቢው ከዚህ በፊት ለመስጠት አስቸጋሪ የነበሩ ውስብስብ የአንጎል፣ የነርቭ እና የህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምናዎች በተሻለ ደረጃ እንዲፈጸሙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ታካሚዎች ለህክምና ከጎንደር ሆስፒታል ውጭ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ የላቀ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚረዳ ነው።
************
ለልህቀት እንተጋለን !
የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

የተቋምን ታሪክ መሰነድ ተቋሙ የመጣበትን መንገድ ለመረዳትና ጠንካራ ጎኑን ለማሳደግ እንዲሁም ሊስተካከል የሚገባውን ለይቶ ለማረም በአጠቃላይ ተቋማዊ እድገትን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና አለው:...
19/06/2026

የተቋምን ታሪክ መሰነድ ተቋሙ የመጣበትን መንገድ ለመረዳትና ጠንካራ ጎኑን ለማሳደግ እንዲሁም ሊስተካከል የሚገባውን ለይቶ ለማረም በአጠቃላይ ተቋማዊ እድገትን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና አለው:: በተለይም ተቋሙን ሊደግፉ የሚችሉ አካላት ስለተቋሙ የተሟላ መረጃና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማስቻሉም በተጨማሪ በየተቋማቱ በኃላፊነትም ሆነ በሁሉም የአገልግሎት ዘርፎች ለትውልድ አሻራቸውን እያኖሩ ያሉ ባለታሪኮችን እንደየ ተሳትፏቸው የሚያነሳ በመሆኑ በማስተማሪያ ሰነድነት የመዋል አቅምም አለው። ከዚያም ባሻገር የተቋማትን እና የማኅበረሰቡን አበርክቶ በአግባቡ በማደራጀት ተገቢውን ክብርና ትኩረት እንዲያገኙ በማሳለጥ ለሀገር ግንባታ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ማሳያ የሚሆንና ልምድ ሊወሰድበት የሚችል ታሪክ ተቋሙን ማዕከል ባደረገ መንገድ “የትውልድ አሻራ” በሚል ርዕስ መጽሐፍ አሰናድቷል፡፡ ይህን ተሞክሮ ሊያሰፋ የሚችል ዝግጅት ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ መጽሐፉን በማስመረቅ ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም በዚህ ደማቅ ዝግጅት ትሳተፉ ዘንድ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

"የአንድ ሀገር ወይም ተቋም ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው በተፈጥሮ ሀብት መኖር ሳይሆን በተቋማት ጥራትና ጥንካሬ እንዲሁም በመሪዎች ስልታዊ እይታ ነው" — ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን********...
19/06/2026

"የአንድ ሀገር ወይም ተቋም ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው በተፈጥሮ ሀብት መኖር ሳይሆን በተቋማት ጥራትና ጥንካሬ እንዲሁም በመሪዎች ስልታዊ እይታ ነው" — ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን
***************************
​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ተቋማዊ ሽግግር፣ ለስትራቴጂካዊ አስተዳደር እና ለአካዳሚክ ፈጠራ የሚበቃ የላቀ አመራር” በሚል መሪ ቃል ለከፍተኛ፣ ለመካከለኛ እና ለመሰረታዊ አመራር ያዘጋጀውን የሶስት ቀናት ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ከሰኔ 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ በዘርአያቆብ አዳራሽ (ታወር 59 ህንፃ ) እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ላይ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ፕሮፌሰሮችና አስተባባሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም ከጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ የሥራ ኃላፊዎችና እንግዶች በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል።

​ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ ናቸው።

​የመድረኩን መከፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን፣ የአንድ ሀገር ወይም ተቋም ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው በተፈጥሮ ሀብት መኖር ሳይሆን በተቋማት ጥራትና ጥንካሬ (Institutional Quality) እንዲሁም በመሪዎች ስልታዊ እይታ (Strategic Governance) መሆኑን በተለያዩ ዋቢ መጻሕፍት አስደግፈው አብራርተዋል።

​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የነገ የሀገር መሪዎችንና ከፍተኛ ምሁራንን የሚያፈራ ተቋም በመሆኑ ይህንን እውነት ወደ ተግባር የመቀየር ቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለበት ፕሬዚደንቱ አስገንዝበዋል።

አክለውም "እውነተኛ ተቋማዊ ሽግግር (Institutional Transformation) ለማምጣት መዋቅርና አሰራርን መቀየር ብቻ አይበቃም፤ ከሁሉ አስቀድሞ የአመራሩን የአስተሳሰብ አድማስ (Mindset) ማደስና ማሳደግ ግድ ይላል" በማለት የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ አብራርተዋል።

​ይህ ስልጠና አመራሩ ቀጣይ ስራዎቹን በላቀ እይታ፣ በአዲስ ስትራቴጂካዊ መነቃቃትና በሙሉ ጉልበት ለመምራት ትልቅ የእውቀትና የክህሎት አቅም እንደሚፈጥር ሙሉ እምነታቸውን የገለጹት ዶ/ር አሥራት፤ ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት በመከታተል ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ያገናዘበ ውጤታማ ውይይት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

​ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ ለዩኒቨርሲቲው ላሳዩት ልዩ አጋርነትና ወንድማዊ እገዛ በራሳቸውና በተቋሙ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

​የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ በአመራርነትና ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ያተኮረውን ይሄንን ስልጠና መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናትም በተከታታይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።
********
ለልህቀትእንተጋለን!
የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ
ሰኔ 12/2018 ዓ/ም

Address

Maraki Street
Gondar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00
Sunday 08:00 - 17:00

Telephone

+251581141232

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when University of Gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to University of Gondar:

Share