Hayyoota M/B/Shankoor Sad. 1ffaa ksaa Bahaan

Hayyoota M/B/Shankoor Sad. 1ffaa ksaa Bahaan የሸንኮር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ይሰራል

15/11/2025
28/08/2024
የመደመር ትውልድ ባህሪዎች ፦➨አንድነትን የሚወድና ለአንድነት የሚሰራ፦➨ብልጽግናን የሚሻ፣ ለመለወጥና ለማደግ የሚጓጓ፦➨በሃሳብ ልዕልና የሚያምን፦➨መስጠትንና በነጻ ማገልገልን እንደ ክብር የሚ...
19/06/2023

የመደመር ትውልድ ባህሪዎች ፦
➨አንድነትን የሚወድና ለአንድነት የሚሰራ፦

➨ብልጽግናን የሚሻ፣ ለመለወጥና ለማደግ የሚጓጓ፦

➨በሃሳብ ልዕልና የሚያምን፦

➨መስጠትንና በነጻ ማገልገልን እንደ ክብር የሚያይ፦

➨ድህነትንና ቆሻሻን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።

ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል - አቶ ኦርዲን በድሪየሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተ...
16/06/2023

ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል - አቶ ኦርዲን በድሪ

የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ አሳሰቡ።

በአቶ ኦርዲን በድሪና ሌሎች አመራሮች መሪነት ሲካሄድ የቆየው የጋምቤላ ክልል የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ አመራሮቹ የክረምት በጎ ፈቃድና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ከተማ አካሂደዋል።

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶች በማስቀጠልና ፈተናዎችን በድል በመሻገር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል ብለዋል።

ፓርቲው የሚመራው መንግስት ባለፉት ዓመታት የገጠሙትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በድል በመሻገር በማህበራዊ ሆነ በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በቀጣይም ፈተናዎችን በድል በመሻገር የተገኙትን የልማት ድሎች ፍጥነትና መፍጠርን በመጨመር አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም አሁን ላይ ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም ለተጀመረው የልማት ጉዞ መሰናክል የሆኑትን ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት አብሮ መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው፤ እንደ ብልጽግና ፓርቲ ግብርናንና ኢንዱስትሪን ጨምሮ እየተገበራቸው በሚገኙት አምስት የብዝሃ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ስራዎች በርካታ ስኬቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም የተገኙትን ስኬቶችና ጥንካሬዎች በማስፋት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በጅምር የቀሩ የልማት ፕሮጀክቶችና የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት የማስቀጠሉ ሂደትም ሌላው በፓርቲው የተመላከቱ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑም አመላክተዋል።

ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል አቶ ቲቶ ሐዋሪያት በሰጡት አስተያየት፤ በስልጠናው የተቀመጡ አቅጣጫዎች በከፍተኛ ተነሳሽነት ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ለህዝቡ ቃል የተገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን መፍጠርና መፍጠን በሚለው መርህ ለመፈጸም እንደሚሰሩ የገለጹት ሌላው ተሳታፊ አቶ ጆዶ ኡሞድ ናቸው።

በዕለቱ አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በጋምቤላ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት ስራ አስጀምረዋል።

"በሀገሪቱ የሕግ የበላይነትን የማስፈን እና ሰላም የማረጋገጥ እርምጃ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር ነው" - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትበሀገሪቱ የህግ የበላይነትን የማስፈን እና ሰላም የማ...
10/06/2023

"በሀገሪቱ የሕግ የበላይነትን የማስፈን እና ሰላም የማረጋገጥ እርምጃ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር ነው" - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በሀገሪቱ የህግ የበላይነትን የማስፈን እና ሰላም የማረጋገጥ እርምጃ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ሰላምን ማረጋገጥና ህግ የማስከበር እርምጃ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ግጭትና ጦርነት የዜጎችን ደህንነትና ነጻነት አደጋ ላይ በመጣልና ዴሞክራሲን በማወክ የሰው ህይወትና ንብረት ያጠፋሉም ነው ያሉት።

በመግለጫው፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን አፍሪካዊ የሰላም ተምሳሌት ልትሆን ይገባታል፤ ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ ዕድገቷ የተረጋገጠ ይሆናልም፤ በቀጠናው እና በአፍሪካም ተጽእኖ ፈጣሪ ትሆናለች ብለዋል።

በመሆኑም አሁን እየተረጋጠ ያለውን አንጻራዊ ሰላም ቀጣይነቱን ማረጋገጥ አመራሩ በተለያየ ጊዜያት መክሮ አስምሮበታል ብለዋል።

የሰላም በሮቻችንን ለሁሉም ኃይሎች ክፍት ማድረጋችን በመላ ሃገሪቱ እየሰፈነ ላለው ሰላም መሰረት ሆኗል ያለው መግለጫው፣ የሰሜኑ ግጭት በተቀመጠለት አቅጣጫ በስኬታማነት እየተተገበረ እንደሚገኘም ጠቁሟል።

በመግለጫው፣ ከሸኔ ጋር የተጀመረው ሰላም የማስፈን ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን በቤንሻንጉል እና በጋምቤላ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችም በተከፈተው የሰላም በር መጠቀም በመቻላቸው አካባቢዎቹ የተረጋጉ እና ሰላማቸው የተረጋገጠ መሆን ችሏል ተብሏል።

መንግስት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን፣ የግዛት አንድነትን እና ህብረ ብሔራዊነትን ለሚያረጋግጥ ሰላም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ አያስቀምጥም ያለው መግለጫው፣ ሰላም ለማጽናት እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ አንድ ሀገራዊ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ የመገንባት የተሳካ ስራም ተጠንክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በክልሎችም እንዲሁ የተቀናጀ ወንጀሎችን መከላከል የሚችል የተጠናከረ መደበኛ ፖሊስ የመገንባት ስራም በተሳካ መልኩ እየቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።

በመግለጫው ሰላማችንን የማይፈልጉ ኃይሎች ዛሬም እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን ከውስጥ የነጠላ እውነትን በኃይል በሌሎች ላይ ገዢ ለማድረግ የሚጥሩ ኃይሎች፤ ከውጭ ደግሞ ታሪካዊ ጠላቶቻችን መሞከራቸው አልቀረም ነው የተባለው።

ስለሆነም፣ የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ የተጀመረው ጠንካራ የጸጥታ እና የደህንነት ተቋም የመገንባት ስራም መንግስት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ሰላምችንን የተሻለ ለማድረግ ቂምን መሻር እና ከሂሳብ ማወራረድ እሳቤ በመውጣት የሽግግር ፍትህን ለማስፈን የተጀመረው ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ማህበረሰቡም የሰላም ማስፈኑን ሂደት እንዲደግፍ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተገኙ አመርቂ ውጤቶችን በሁለተኛው ምዕራፍ ለመድገም በተለይ በጥምር ግብርና ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተናገ...
09/06/2023

በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተገኙ አመርቂ ውጤቶችን በሁለተኛው ምዕራፍ ለመድገም በተለይ በጥምር ግብርና ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተናገሩ።

በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው አሻራቸውን ያሳረፉ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በሰጡት አስተያየት ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በየክልሎቹ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ በየአካባቢው ያለው የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለማሳካት ይሰራል ብለዋል።

በምግብ ተክሎች ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም የአቦካዶ፣ የኮክ፣ የጊሽጣና መንደሪን ፍራፍሬዎችን በመትከል በምግብ ራስን ለመቻል የሚከናወኑ ተግባራትን በሚያግዝ መልኩ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ዝግጁነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው በመጀመሪያው ምዕራፍ የተገኙ ስኬቶችን ለመድገም በቂ ዝግጅት መደረጉን ነው የጠቀሱት።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ክልሉ የደን፣ የቡና እና የፍራፍሬ ወይም ጥምር ግብርና ስርዓትን በመከተል እንደሚያለማ ጠቁመው በክልሉ ከሚተከሉ አጠቃላይ ችግኞች መካከል 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን የቡና፣ 50 ሚሊዮን ደግሞ የፍራፍሬ ዝርያዎች ተከላ ቀደም ብሎ መጀመሩን አረጋግጠዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው ከዕቅድ በላይ ማሳካት በተቻለበት በመጀመሪያው ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች አምጥቷል ብለዋል።

ክልሉ የአየር ንብረት መዛባት ተጽዕኖን የሚቋቋሙ ብቻ ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ነው የተናገሩት።

በተያዘው የክረምት ወቅት ከሚተከሉ ችግኞች ባሻገር ለቀጣይ ዓመት የሚሆኑ ችግኞችን የማፍላት ስራዎች እንደሚከናወኑም ገልፀው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የህብረተሰቡ ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ባህል መዳበሩን ጠቅሰዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ትግራይ ክልል በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች አርዓያነት እንደነበረው አስታውሰው፣ ሆኖም በጦርነቱ የተፈጥሮ ሀብት ስራው መስተጓጎሉን አንስተዋል።

በዚህም የተስተጓጎለውን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ለማካካስ በሁለተኛው ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በስፋት ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ሁለተኛው ምዕራፍ በይፋ በተጀመረበት አፋር ክልል የተመለከቱት እምርታ ያመጣ የፍራፍሬ ልማት፤ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ አቅም የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

በተለይም በቆላማ አካባቢዎች ላይ የአመራር ቁርጠኝነት ከተጨመረበት የአየር ንብረት መዛባት ተጽዕኖን መቀነስ ብቻ ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚቻል ጉልህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

Naannichatti nageenyi akka lafa qabatuuf dargaggoonni shoora gumaachaa jiran cimsuu qabu- Obbo Abdujabbaar Mahammad Naan...
08/06/2023

Naannichatti nageenyi akka lafa qabatuuf dargaggoonni shoora gumaachaa jiran cimsuu qabu- Obbo Abdujabbaar Mahammad

Naannichatti nageenyi akka lafa qabatuuf dargaggoonni shoora gumaachaa jiran cimsuu qabu jechuun Itti gaafatamaan waajjira paartii badhaadhinaa damee Naannoo Hararii Obbo Abdujabbaar Mahammad dubbatan.

Waajjirri Paartii badhaadhinaa damee Naannoo Hararii Dargaggoota Naannichaa waliin mari'ateera.

Waltajjicha irratti Itti gaafatamaan waajjirichaa Obbo Abdujabbaar Mahammad akka jedhanitti yeroo ammaa kanatti Naannichatti nageenyaa fi tokkummaan uummataa akka cimuuf yoomiyyuu caalaa ciminaan hojjatamuu qaba.

Magaalaan Harar magaalaa lammiileen hundi nagayaan, tokkummaa fi waldanda'umsaan keessa jiraatan ta'uu yaadachiisanii, duudhaa kun akka cimuuf hunduu gahee isaa bahuun barbaachisaadha jedhaniiru.

Keessumattuu dargaggoonni aadaa wal dhageeffachuu fi waliin mari'achuu gabbifachuun nageenyi akka lafa qabatuuf hojjachuun murteessaa ta'uu kaasanii, qaamolee nageenyi akka boora'uu fi tokkummaa ummataa akka diigamuuf hojjatan dammaqinaan hordofuun ittisuu qabna jedhaniiru.

Dargaggoonni ergama diigumsaa miidiyaalee hawaasaatiin daddarban moggatti dhiisuun nageenyaaf waardiyaa dhaabbachuu akka qaban ibsaniiru.

Itti gaafatamaan Biiroo Bulchiinsaa fi Nageenyaa Naannichaa Obbo Xilaahun Waadaraa gama isaaniitiin nageenyi akka cimuuf dargaggoonni gahee isaanii bahaa turan.

Gara fuula duraattis nageenyi naannicha keessatti mullatu akka cimsuuf gaheen dargaggootaa olaanaa waan ta'eef akka cimsan gaafataniiru.

Dargaggoonni waltajjicha irratti argaman gama isaaniitiin akkuma kanaan duraa tokkummaa keenya cimsuun nageenyaaf waardiyaa ni dhabbanna jechuun dubbataniiru.

Qaamolee nageenyaa waliin qindaa'uun hojiiwwan Naannichatti nageenya lafa qabsiisuuf hojjatamaa jiran cimsanii kan itti fufan mirkaneessaniiru.

Waltajjicha irrattis Itti gaafatamaa Waajjira paartii badhaadhinaa damee Naannoo Hararii Obbo Abdujabbaar Mahammad dabalatee gaggeessitoonni ol

ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊ ክልላዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ። በሀረሪ ክልል በነገው እለት ምንም አይነት የተፈቀደ የአደባባይ ...
08/06/2023

ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ

ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊ ክልላዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ።

በሀረሪ ክልል በነገው እለት ምንም አይነት የተፈቀደ የአደባባይ ሰልፍ እንዲሁም ፖሊስም ሆነ የክልሉ መንግሥት አካላት የሚያውቁት ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታውሳል።

በሌሎች አካባቢዎች መስጂዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ባለፈው ሳምንት የአርብ (የጁምዓ) ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ ሕገወጥ ሰልፍ በማድረግ በፈጠሩት ሁከት፣ ረብሻና ግርግር ህግ በማስከበር ስራ ላይ በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላል የአካል ጉዳትና እና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በትዕግስት የክልሉን ሰላም ማረጋጋታቸው የሚታወቅ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ አካላት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም በነገው እለት ጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኃላ ሕገወጥ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ማረጋገጥ ችሏል።

ለዘመናት በፍቅርና በመቻቻል አብሮ የኖረውን ህዝብን በሀይማኖት ለመከፋፈል አጀንዳ ቀርፀው የክልሉን ሰላም ለማደፍረስና ብጥብጥ ለመፍጠር እየሰሩ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ፖሊስ ደርሶበታል።

በመሆኑም በነገው እለት አርብ በክልሉ በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍ ራሱን እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ ያስጠነቅቃል።

ሆኖም ይሄንን ማሳሰቢያ ተላልፈው የሚገኙ አካላትን የማይታገስና ህግን የማስከበር ሀላፊነቱን የሚወጣ መሆኑን ያሳስባል።

በመጨረሻም ህዝበ ሙስሊሙ የሚያነሳውን ማንኛውንም ጥያቄ በህግ አግባብ በሰላማዊ መንገድ ማስተናገድ የሚቻልበት ሥርዓት መኖሩን በመገንዘብ ለፀረ-ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሳይሆን የፀጥታ አካላት የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ህዝበ ሙስሊሙ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል።

የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም
ሐረር፣ ኢትዮጵያ

ህግ ይኖራል ተከብሮ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ! ህግ ይኖራል ተከብሮ  #ስርአት ይኖራል ተዛውሮ! ስርአት ይዛወራል ህግ ግን ይፀናል! ህግ ሊሻሻል ይችላል  #መፅናት ግን አለበት!ይህን ማድረግ ...
06/06/2023

ህግ ይኖራል ተከብሮ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ!

ህግ ይኖራል ተከብሮ #ስርአት ይኖራል ተዛውሮ! ስርአት ይዛወራል ህግ ግን ይፀናል! ህግ ሊሻሻል ይችላል #መፅናት ግን አለበት!ይህን ማድረግ ስንችል ነው ተቋም መፍጠር የምንችለው!ተቋም ኖሮን የፀና ህግ ኖሮን በስርአት መዛወር ውስጥ የማይናድ የወል ፍላጎት እና እውነት ያላት ሀገር ከፈጠርን #ኢትዮጵያን ማበልፀግ ይቻላል፡፡

24/08/2022
24/08/2022

ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ የነበረ አውሮፕላን በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወደቀ
**************************

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያ አየር ክልል ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ኃይል ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ፡፡

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም አንስተዋል።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀብል የነበረ አውፕላንም በጀግናው አየር ኃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ኃይሎች ቢኖሩም የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያነ ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ ምህናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል አሁን የመከላከል ርምጃ እየተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የማጥቃት ርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው ጠቁመዋል።

Address

Harar

Telephone

+251915404143

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hayyoota M/B/Shankoor Sad. 1ffaa ksaa Bahaan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Hayyoota M/B/Shankoor Sad. 1ffaa ksaa Bahaan:

Share