Wachemo University -WCU

Wachemo University -WCU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wachemo University -WCU, College & University, Hossana.
(1)

Vision: "To be a premier comprehensive university in Ethiopia, distinguished for its academic excellence, innovative research and community engagement by 2030"

Join WCU telegram page
https://t.me/WACHEMOPR

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የማጠናከሪያ ትምህርት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀመረ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ 60 ሁለተኛ ደረጃ ትም...
27/04/2026

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የማጠናከሪያ ትምህርት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀመረ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ 60 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የማጠናከሪያ ትምህርት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።

በዚህ መርሃ-ግብር ከ60ዎቹ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ 456 ተማሪዎች ለ45 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤

ስልጠናው ተማሪዎች በቀጣዩ ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዝግጅት ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ እንዲያደርጉና የዩኒቨርሲቲውን ሀብቶች በአግባቡ እንዲንከባከቡ አሳስበዋል።

መምህራንም የተመደበውን አጭር ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ተማሪዎቹን ለፈተና ዝግጁ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ማልደዮ በበኩላቸው፤

በክልሉ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆን አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ 60 ትምህርት ቤቶች መኖራቸው፣ ይህን ልዩ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ እንዳደረገው ገልጸዋል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ ለተማሪዎቹ የምግብ፣ የመኝታና የህክምና አገልግሎቶችን በማመቻቸት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑንም ኃላፊው አክለዋል።

ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች ድልድል በባለሙያ መደብ ላይ ተወዳድረው ያለፉ ቋሚ አስተዳደር ሠራተኞች የሥራ ኦሬንቴሽን ተሰጠ************በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች...
27/04/2026

በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች ድልድል በባለሙያ መደብ ላይ ተወዳድረው ያለፉ ቋሚ አስተዳደር ሠራተኞች የሥራ ኦሬንቴሽን ተሰጠ

************

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች ድልድል በባለሙያ መደብ ላይ ተወዳድረው ያለፉ ቋሚ አስተዳደር ሠራተኞች የሥራ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።

በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች ድልድል ለሥራ አስፈፃሚዎችና ቡድን መሪዎች የሥራ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ እንደገለፁት፣

በአዲሱ የአስተዳደር ሠራተኞች ድልድል መሠረት አዲስ በባለሙያ መደብ ላይ ተወዳድረው ያለፉ ቋሚ አስተዳደር ሠራተኞች በየደረጃ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ሠራተኞች ስሜታዊ ብልሃት፣ አድልኦ አለማድረግ፣ አገልግሎት ተኮር ስራ መስራት፣ ተቋሙን በብቃትና በጥራት ማገልገል፣ በትብብር መንፈስ መተጋገዝ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ለለውጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የተነገሩት ፕሬዝዳንት የግለሰብ ተነሳሽነት እና የጋራ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተገቢ መረጃዎችን መያዝና ውጤት ለመምጣት በመልካም ስነምግባር መታነጽ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ምስጥራዊነት መጠበቅ፣ የሥራ ሰዓት መክበር፣ ችግር ፈቺ መሆን፣ ከሌብነትና ከስርቆት እራስን ማረቅ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

27/04/2026

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲደረግ የቆየው ተቋማዊ ጥራት ኦዲት መውጫ መርሃ ግብር ተካሄደ።በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲደረግ የቆየው ተቋማዊ ጥራት ኦዲት መውጫ መርሃ ግብር ተካሂዷል።የኦዲት ዓላማ በዋናነት ...
25/04/2026

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲደረግ የቆየው ተቋማዊ ጥራት ኦዲት መውጫ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲደረግ የቆየው ተቋማዊ ጥራት ኦዲት መውጫ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የኦዲት ዓላማ በዋናነት ተቋማዊ ስርዓትን መገንባት እና ማሻሸል እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ከተቋሙ ጥሩና ልምድ መውሰድ የሚያስችል እድል የተገኘበት እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ እንደገለፁት፥

ተቋማዊ ጥራት ኦዲት መደረግ ለተቋማት ጥንካሬና ማሻሻል ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

አክለውም ዶ/ር ዳዊት በተቋማዊ ኦዲት መነሻ መንግታዊ ድጋፍ ለመግኘት እና ስራዎችን በዕቅድ በቅንጅት ለመምራት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የተደራጀ አይሲቲ መሠረተ ልማት በመጠቀም የመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲሠራ ያስችላል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣

በኦዲት መነሻ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እና በታዩ ደካማ ጎኖች ክፍታቶችን ለማረምና ለማሻሻል እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በአቶ ዳኝነት አምሳሉ የተመራ ልዑካን ተገኝተዋል።

ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

24/04/2026
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ************የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የዩኒቨ...
24/04/2026

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ

************

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የዩኒቨርሲቲው የ2018 ዓ.ም 9 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገምግሟል።

የየዘርፉ ቁልፍ አፈጻጸም እና የከፍተኛ ትምህርት የሪፎርም አጀንዳዎች ተገምግሟል።

በጨረሻም ለመጣው ውጤት አስተዋጽኦ ያደረጉትን አካላት በማመስገን የተግባራት አፈጻጸም ተጠናክሮ እንድቀጥልና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

ከሀዲያ ዞን ለተወጣጡ ፖሊስ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ለፖሊስ አባላት የአቅም ግንባታ ስል...
24/04/2026

ከሀዲያ ዞን ለተወጣጡ ፖሊስ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ለፖሊስ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።

በስልጠና መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎትና ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ እንደተናገሩት፥

ለዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት እንደሆነ አብራርተዋል።

አክለውም ዶ/ር አበበ ዩኒቨርሲቲው በጥናት ላይ ተመስርቶ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለይም በትራፊክ አደጋ መከላከልና የመንገድ ደህንነት ዙርያ የዘመቻ ስራዎችንና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በስፋት እየተሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሀዲያ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ተሾመ ባቲሶ በበኩላቸው፥

ሀገር የሚገነባው በእውቀትና በቴክኖሎጂ ውጤት በመሆኑ የሠራዊት አባላት የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በእውቀትና በዲስፕሊን ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ስልጠናውን ሰመንያ አራት የትራፊክና ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ለሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት እንደሚከታተሉ ገልፀው፤

መምህራንና አሰልጣኞች የሚሰጡትን ትምህርት በአግባቡ በመውሰድ ለተጨማሪ ተልዕኮ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለትራፊክ ፖሊስ የሚሰጠውን ስልጠና በማመቻቸቱ ልባዊ ምስጋና ያቀረቡ ዋና አዛዥ ሰልጠኞች በፍጹም ዲሲፕሊን ስልጠናውን እንዲከታተሉ አሳሰበዋል።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

24/04/2026

24/04/2026

አዲስ የሕግ ትርጉም፦ የሥራ ውል ማቋረጥ እና የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
*****************************

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት፣ አንድ ሠራተኛ ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ ሲቀር ስለሚወሰድ እርምጃ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን የሕግ ትርጉም በመለወጥ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል።

ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ይህ ችሎት ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የሕግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት አንድ ሠራተኛ ለተከታታይ አምስት የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ ገበታው ላይ ከቀረ፣ አሠሪው ምንም ዓይነት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳይጠበቅበት የሥራ ውሉን ወዲያውኑ ማቋረጥ ይችላል።

ይህ አዲስ ውሳኔ "አሠሪው ለእያንዳንዱ ለቀረበት ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት" በሚል ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሻረ ነው።

አዲሱ የሕግ ትርጉም የሥራ ዲሲፕሊንን ለማስከበርና የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ግልጽ በሆነ መንገድ ለመምራት ታቅዶ የተሰጠ በመሆኑ፣ በማንኛውም የፍትሕ አካል ዘንድ እንደ አስገዳጅ ሕግ ሆኖ ያገለግላል።

ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞው አሠራር ቀሪ ሆኖ በአዲሱ ትርጉም መሠረት ውሳኔዎች የሚሰጡ ይሆናል።

በብርቱካን አስናቀ

የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የአስተዳደርና ል/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዘርፍ የ9 ወር  ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ።በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/...
23/04/2026

የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የአስተዳደርና ል/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዘርፍ የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የአስተዳደርና ል/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም 9 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል።

የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳራ ሽኩር እና የአስተዳደርና ል/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤርምያስ ሞሊቶ እንደገለፁት፤

በዘርፉ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠልና በቀሩት ወራት የታዩ ክፍታቶችን ለመሙላት አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አሳሰበዋል።

ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

የ5 Million Ethiocoders ኢኒቬቲቭ የሥራ አቅጣጫ መስጫ መድረክ ተካሄደ።በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ5 Million Ethiocoders ኢኒቬቲቭ የሥራ አቅጣጫ መስጫ መድረክ ተካሂዷል።በመር...
23/04/2026

የ5 Million Ethiocoders ኢኒቬቲቭ የሥራ አቅጣጫ መስጫ መድረክ ተካሄደ።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ5 Million Ethiocoders ኢኒቬቲቭ የሥራ አቅጣጫ መስጫ መድረክ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ እንደገለፁት፥

የ 5 Million Ethiocoders ኢኒቬቲቭ ዓላማ በዋናነት ተለዋዋጭ አለም ላይ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመቀበል ተጠቃሚ መሆን ነው ብለዋል።

ጊዜው የቴክኖሎጂ በመሆኑ አለም ያለበትን ሁኔታ መገንዘብ እና ለተግባራዊነቱ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለመጠቀም በምታደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አንዱ የትምህርት መስክ በመሆኑ፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መንግስት የሚያመጣው ኢኒሼቲቭ መቀበልና ተግባራዊ በማድረግ ጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው አንስተዋል።

አክለውም ዶ/ር ዳዊት የዩኒቨርሲቲውን የአገልግሎት መስጫ ዘርፎችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሠራ በመሆኑ የሁሉም የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የቴክኖሎጂን መዘመን ጠቃሜታ መረዳትና ተጠቃሚ ለመሆን ማሰልጠንና የእውቅና ሰርተፍኬት መውሰድ እንደሚያስፈልግ የተነገሩት ደግሞ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳራ ሽኩር ናቸው።

በመጨረሻም የ 5 Million Ethiocoders የሥራ አቅጣጫ መድረክ አስመልክቶ የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀጋነሽ ሞገስ እና የአይሲቲ ዳይሬክተር አቶ ደገለ ደስታ ግንዛቤ ሰጥተዋል።

ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

በፈጠራ ስራ ለተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ**********በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ስራ ለተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷል።በኢትዮጵያ አእምሯአዊ ንብረት ባለስልጣን...
22/04/2026

በፈጠራ ስራ ለተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ

**********

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ስራ ለተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷል።

በኢትዮጵያ አእምሯአዊ ንብረት ባለስልጣን ቅጅና ተዛማጅ መብቶች ስራ የምዝገባ የፈጠራ ስራ የሰሩ መምህራንና ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ እንደገለፁት፥

ፈጠራ የሚጀመረው በአዕምሮ ውስጥ በመሆኑ ወደ ተግባር የሚቀየር ከመሆኑም በላይ ስራ ፈጠራ ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ትላልቅ ፈጠራዎችን ለመፍጠር የፈጠራ ሀሳብ ለመፍለቅ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የሀገራቱን ሁለንታዊ ልማትና እድገት ለማፋጠን የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ፤ መምህራንና ተማሪዎች የጀመሩትን የፈጠራ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር በየነ ባሹ በበኩላቸው፤

በዘንድሮ ዓመት ስድስት የፈጠራ ስራዎች በኢትዮጵያ አእምሯአዊ ንብረት ባለስልጣን ቅጅና ተዛማጅ መብቶች ስራ መመዝገቡን ጠቁማዋል።

ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራንና ተማሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.

Address

Hossana
667

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wachemo University -WCU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share