31/10/2015
Federal Ministry of Health,Ethiopia
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ ገልግሎት ተሸላሚ
-------------------------------------------
ዶ/ር ገርቢ ዱጉማ በ1954 ዓ.ም ሆሮጉድሩ ወለጋ ልዩ ስሙ አቤዶጎሮ በሚባል ስፍራ ተወለዱ ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሻምቡ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ 1963 ዓ.ም የተከታተሉ ስሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት እስከ 1966 ዓ.ም ተከታትለዋል፡፡
ዶ/ር ገርቢ ዱጉማ የመጀመሪያ ዲግሪአቸዉን ከ1969-1975 ዓ.ም እና የማስተርስ ዲግሪያቸውን ከ1982ዓ.ም- 1986 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ሞስኮ አገር ከሚገኘው ሌንግሬስ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡
ዶ/ር ገርቢ ከ1976ዓ.ም ጀምሮ በነጌሌ ቦረና ፤ በአለርት እና በራስ ደስታ ሆስፒታሎችና በኮልፌ ጤና ጣቢያ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመመደብ በከፍተኛ ሙያዊ ፍቅርና ስራ ወዳድነት አገልግለዋል፡፡
ዶ/ር ገርቢ ዱጉማ ከ1986ዓ.ም እሰከ አሁን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቆዳና የአባለዘር በሽታ ሀኪሚ እና የዩኒቨርስቲዉ መምህር ሆነዉ ስራቸዉን በብቃትና በታታሪነት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ዶ/ር ገርቢ ዱጉማ ከ30 አመታት በላይ በቅንነትና በህዝብ ተቆርቋሪነት ስሜት ሙያ ብቻ ሳይሆን የስነምግባርም አርአያ በመሆን ያገለገሉ አንጋፋ ባለሙያ ናቸዉ፡፡