ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College

  • Home
  • Ethiopia
  • Kelela
  • ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College

ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College የኮሌጁ ራዕይ
በኢንዱስትሪ ውስጥ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት።

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ! ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
27/05/2026

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

 #ማስታወቂያ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ መመዘን ለምትፈልጉ በሙሉ
21/05/2026

#ማስታወቂያ
የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ መመዘን ለምትፈልጉ በሙሉ

 #ማስታወቂያ  #ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ
21/05/2026

#ማስታወቂያ
#ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ውጤታማነትን በተበለከተ የዳሰሳ ጥናት አቀረበ​ከለላ (ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም)  የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኢንተርፕራይዞች ላይ ...
07/05/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ውጤታማነትን በተበለከተ የዳሰሳ ጥናት አቀረበ
​ከለላ (ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም)
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኢንተርፕራይዞች ላይ የሚሰጠው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ያመጣውን ለውጥና ውጤታማነት ተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ዛሬ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ለአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች አቀረበ።
​ኮሌጁ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የቴክኒክና ሙያ ድጋፍ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በኢንተርፕራይዞቹ ዕድገት ላይ የፈጠረውን ተጽዕኖ ለመለየት የሚያስችል ሰፊ የዳሰሳ ጥናት የቀረበ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይም የኮሌጁ
መሪዎች፣ ኢንስትራክተሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
-​ጥናቱ በዋናነት ኮሌጁ ባለፉት ጊዜያት ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የቆየው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የክህሎት ማሻሻያ እና የማማከር አገልግሎት በኢንተርፕራይዞቹ ምርታማነት ላይ የፈጠረውን ተጨባጭ ለውጥ ለመፈተሽ ያለመ ነው።
​የጥናቱ ዋና ዋና ነጥቦች
​በቀረበው ጥናት ላይ እንደተመለከተው፣ ኮሌጁ የሚያደርገው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ኢንተርፕራይዞች፦
-​የቴክኖሎጂ ሽግግር፡ አዳዲስና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን እንዲለምዱ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል።
-​የምርት ጥራትና ብዛት፡ በሰለጠነ የሰው ኃይል የታገዘ ድጋፍ በመደረጉ የምርቶቻቸውን ጥራትና ብዛት ማሳደግ መቻላቸው ተረጋግጧል።
-​የአሰራር ስርአት፡ የሂሳብ አያያዝ፣ የገበያ ትስስርና የሥራ አካባቢ አደረጃጀትን (5S) በማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
​የአሰልጣኞች ድርሻና የቀጣይ አቅጣጫ
​የጥናት ሰነዱ ከቀረበ በኋላ በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች መካከል ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በድጋፍ ሂደቱ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይም ምክክር ተደርጓል። በተለይም አሰልጣኞች ወደ ኢንተርፕራይዞች በሚወርዱበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የአቅርቦትና የክትትል ክፍተቶች በዝርዝር ተነስተዋል።
-​የኮሌጁ አመራሮች በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ በጥናቱ የተለዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
-በመጨረሻም ​ይህ የዳሰሳ ጥናት ኮሌጁ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ በማጠናከር፣ ብቁና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር ለሚያደርገው ጉዞ እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግል መሆኑ ተመላክቷል።

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው​(ከለላ፤ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም)​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በማጠናከር የአካ...
04/05/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው
​(ከለላ፤ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም)
​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በማጠናከር የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ነው።
ዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የኮሌጁ አመራሮች፣የከለላ ወረዳና የከለላ ከተማ ስራና ክህሎት አመራሮችና ቡድን መሪዎች እንድሁም ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የኮሌጁ አሰልጣኞችና ዘርፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚገመግም መድረክ ተካሂዷል።
​የኮሌጁ አመራሮች በገለጹት መሰረት፤ ኮሌጁ ከመደበኛው የትምህርትና ስልጠና ስራው ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማላመድና ወደ ማህበረሰቡ በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል። ይህም በተለይ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስራ ለማቃለልና ገቢያቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው።
​የቴክኖሎጂ ሽግግር ዋና ዋና ትኩረቶች፡
​ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማላመድ፦ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚው ማድረስ።
​የእውቀት ሽግግር፦ ለኢንተርፕራይዞችና ለግለሰቦች ቴክኖሎጂዎቹን እንዴት መጠቀምና መጠገን እንደሚችሉ ተግባራዊ ስልጠና መስጠት።
​ምርታማነትን ማሳደግ፦ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በማስፋፋት የጥራትና የብዛት ምርትን ማረጋገጥ።
​በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተመለከተው፤ ኮሌጁ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት በርካታ ውጤታማ ስራዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በቀጣይም የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
​በመጨረሻም ኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግር የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ ለማረጋገጥ ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

 #ከለላ  ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሙያ ብቃት (COC) ተመዛኞች ምዘና መስጠት ጀመረ  ​ከለላ የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 16/08/2018 ዓ.ም በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች በመደበኛም ሆነ በአ...
24/04/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሙያ ብቃት (COC) ተመዛኞች ምዘና መስጠት ጀመረ
​ከለላ

የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 16/08/2018 ዓ.ም በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች በመደበኛም ሆነ በአጫጭር ለሰለጠኑ ሰልጣኞችና በስራ ላይ ያሉ የውጭ ተመዛኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘና መስጠት ጀምሯል።

​ኮሌጁ የሰለጠነና በገበያው ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የሙያ ብቃት ምዘና አንዱ መሆኑ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የተጀመረው ይህ ምዘና በንድፈ-ሐሳብ እና በተግባር የተደገፈ ሲሆን፣ ተመዛኞቹ በቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር የሚያሳዩበት ነው።

​ምዘናው ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የብቃት ማረጋገጫውን የሚያልፉ ተመዛኞች በሚሰማሩበት የሙያ መስክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ራሳቸውን ለመለወጥ ሰፊ እድል የሚያገኙ ይሆናል።

​" #ብቁ ዜጋ ለተሻለ የሀገር ግንባታ!"
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ​[ከለላ - ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም]​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአጠቃላይ ሠራተኞች  ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓ...
24/04/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
​[ከለላ - ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም]

​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

​በመድረኩ ላይ የዘጠኝ ወራቱ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ በተመዘገቡ ውጤቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ሪፖርቱን መነሻ በማድረግም ከኮሌጁ ሠራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በኮሌጁ አመራሮች አማካኝነት ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

​የኮሌጁ አመራሮች በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት፤ መድረኩ ተቋማዊ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለይቶ ለማረም ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። በቀሪው የበጀት ዓመት ጊዜያትም​ የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችንና ውጤታማ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፤
​በግምገማው ወቅት የታዩ ደካማ ጎኖችንና ያልተከናወኑ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ፤
​ለተቋሙ ዕድገትና ለሰልጣኞች ብቃት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
​በመጨረሻም መላው የኮሌጁ ሠራተኛ ለተቀመጠው ግብ መሳካት በጋራ እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል።

" #ብቁ ዜጋ ለተግባራዊ ክህሎት!"
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

ቀን 14/08/2018 ዓ.ም ​ #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ"ዲጂታል አማራ"   Amhara Initiative" ሥልጠና የንቅናቄ ሳምንት  ጀመረከለላ​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ  የዲጂታል ትራንስ...
22/04/2026

ቀን 14/08/2018 ዓ.ም
​ #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ"ዲጂታል አማራ" Amhara Initiative" ሥልጠና የንቅናቄ ሳምንት ጀመረ
ከለላ

​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን የታለመውን የ"ዲጂታል አማራ" (Digital Amhara Initiative) የክህሎት ሥልጠና የንቅናቄ ሳምንት ለአጠቃላይ ሠራተኞቹ መስጠት ጀምሯል።
​ይህ የንቅናቄ ሳምንት የተዘጋጀው በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠትና የሠራተኞችን የዲጂታል ግንዛቤ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መሆኑ ተገልጿል።
በሥልጠናው መርሃ ግብር ላይ እንደተገለፀው በወቅቱ ያለውን የቴክኖሎጂ ዕድገት በመጠቀም ተቋማዊ አሰራርን ዘመናዊ ማድረግ ተወዳዳሪነትና ውጤታማነትን ማረጋገጥ ነው።
ሠራተኞቹም በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን ይበልጥ ፈጣንና ጥራት ባለው መልኩ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዲጂታል ክህሎት ሥልጠናዎች ከጊዜው ጋር አብሮ ለመራመድ ና አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸው ገልፀዋል ።
​ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎታችንን ለማዘመንና የሠራተኞቻችንን የዲጂታል ብቃት ለማሳደግ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ተገልጿል ።
ስልጠናው ርዕሶች
1.Basic Digital Literacy
2.Intermediate Digital Literacy
3.Advanced Digital Literacy ሲሆኑ በመቀጠልም ፦
1.Content Creation
2.Website Development
3.Graphic Design
4.Digital Marketing
5.Network Configuration

ከ5ቱ ሙያዎች አንዱን በሰልጣኙ ፍላጎትና ምርጫ የሚወሰድ ሲሆን ሁሉም ሰልጣኞች Basic digital Litracy መሰልጠን አለባቸው።በመሆኑም በእነዚህ ሙያዎች ስልጠናው በኮሌጁ የICT አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ድጋፍ እየተደረገ በonline የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል።

​"ዲጂታል ክህሎት ለተቀላጠፈ አገልግሎት!"

 #ማስታወቂያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና(COC) የተመዘገባችሁ በሙሉ
21/04/2026

#ማስታወቂያ
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና(COC) የተመዘገባችሁ በሙሉ

 #ማስታወቂያለስራ ፈላጊዎች  በሙሉ
30/03/2026

#ማስታወቂያ
ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ

 #ከለላፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርትና ስልጠና ቦርድ አመራር ከኮሌጅ አመራርና ከአጠቃላይ ሠራተኞች  ጋር ተወያየየካቲት 30/2018 ዓ/ም​ከለላ  የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርትና ሥልጠና...
09/03/2026

#ከለላፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርትና ስልጠና ቦርድ አመራር ከኮሌጅ አመራርና ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር ተወያየ

የካቲት 30/2018 ዓ/ም
​ከለላ

የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርትና ሥልጠና ቦርድ አመራር ከኮሌጁ አጠቃላይ ሠራተኞችና የአስተዳደር አካላት ጋር በዋና ዋና ተቋማዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሄደ።
​ውይይቱ በዋናነት ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማሳደግና ግልጽነት የሰፈነበት አሠራርን ለመዘርጋት ያለመ ሲሆን፣ በአራት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር ተወያይተዋል።
​የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች፡
1.​የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፦ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የታቀዱ የሥልጠና፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የፋይናንስ አስተዳደርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ያሉበት ደረጃ ተገምግሟል። በግምገማውም የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የታዩ ክፍተቶች ደግሞ በቀሪው ጊዜ እንዲታረሙ አቅጣጫ ተቀምጧል።
2.​የአመራርና የሠራተኛው ተግባቦት፦ በተቋሙ ውስጥ የሚታየውን የሥራ መንፈስ ይበልጥ ለማቀላጠፍ በአመራሩና በሠራተኛው መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነትና የመረጃ ፍሰት የተሻለ ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል። ቅሬታዎች በውይይት የሚፈቱበትና ግልጽነት የሰፈነበት የሥራ አካባቢ መፍጠር ለኮሌጁ ስኬት ወሳኝ መሆኑም ተገልጿል።
3.​የሀብትና በጀት አጠቃቀም፦ የኮሌጁን ውስን ሀብትና በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ ብክነትን ማስወገድና ለታለመለት የሥልጠና ተግባር ብቻ ማዋል ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ ተነግሯል። በተለይም ግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ተቋማዊ ፋይዳን ባስከበረ መልኩ እንዲመራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
4.​የሰላም ግንባታና የሠራተኛው ሚና፦ ኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደቱ በሰላም እንዲከናወንና ሰራተኛውም በሥራ ገበታው ላይ ያለስጋት እንዲገኝ የሰላም መረጋገጥ ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል። ሰራተኛው ለአካባቢው ሰላምና ለተቋሙ ደህንነት የራሱን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጥሪ ቀርቧል።
​የቦርዱ አመራር በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ የተጣለበትን የክህሎት ልማት ተልዕኮ እንዲወጣ የሁሉንም ሠራተኞች ቅንጅታዊ አሠራርና ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ አሳስበዋል። ሠራተኞችም በበኩላቸው የተነሱት አጀንዳዎች ወቅታዊ መሆናቸውን ገልጸው፣ ለተቋሙ ዕድገት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

​"ብቁ ዜጋ ለተግባራዊ ክህሎት!"

​ college

Address

Kelela

Opening Hours

Monday 08:00 - 20:30
Tuesday 08:00 - 20:30
Sunday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College:

Share