Kemissie Polytechnic College

Kemissie Polytechnic College Kemssie Polytechnic College is opened at 2000E.C. with ICT and Construction Departments by involveme

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ በአዲሱ የተቋማዊ እሳቤ፣ በውስጥ ጥራት ማስጠበቅ (Quality Training) እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን ሰነዶች...
04/06/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ በአዲሱ የተቋማዊ እሳቤ፣ በውስጥ ጥራት ማስጠበቅ (Quality Training) እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን ሰነዶች ላይ ያተኮረ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

​ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የሥልጠና መድረክ ላይ፡

​የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፍ አስተባባሪዎች፣

​የዞን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አግባብነትና ጥራት ቁጥጥር ቡድን መሪ፣

​በከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ክላስተር ሥር የሚገኙት የባቲ እና የጨፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

​በኮሌጁ የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ ቡድን መሪ በኢንስትራክተር አህመድ እሸቴ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በዚህ ሥልጠና ላይ ሰፊ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን፣ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች በመቅረፍ የዓለም አቀፍ የደረጃ ማረጋገጫ (ISO Certified) ባለቤት ለመሆን መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በጥልቀት ተመክሯል። ለዚህም አዲሱን የተቋማዊ እሳቤ መነሻ በማድረግ የወጡ ስታንዳርዶችን (ደረጃዎችን) ሙሉ በሙሉ ለማሟላት የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት ተመላክቷል።

​የኮሌጁ ዲን አቶ ሙክታር ገዛኸኝ በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሥልጠናው እንዲሁ በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት በጥብቅ አሳስበዋል።

​“የሥልጠናው ዋነኛ ግብ ወደ ተግባር መለወጥ ነው” ያሉት አቶ ሙክታር፣ እያንዳንዱ የሥራ ኃላፊና ባለሙያ በተሰማራበት የሙያ መስክ አዲሱን እሳቤና የወጡ ስታንዳርዶችን መሠረት አድርጎ መፈጸም እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል። ዲኑ አክለውም፣ ይህንን ዕቅድ ከዳር ለማድረስ ኮሌጁ ከወዲሁ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ-ልማቶችን ለማሟላት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት አቤት፣  በመተሆሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት  ፣ በከሚሴ  2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን...
19/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት አቤት፣ በመተሆሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ በከሚሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን አስጀመረ
* ኮሌጅ በክልል ደረጃ እየተገበረ ያለውን የ“ዲጂታል አማራ” ስልጠና የንቅናቄ ሳምንትን በማስመልከት፣ በቀን 11/09/2018 ዓ.ም በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎችና ለመምህራን የመጀመሪያውን የማስጀመሪያ ፕሮግራም በታላቅ ደማቅ ስነ-ስርዓት ከፍቷል።
ይህ የንቅናቄ ሳምንት በክልሉ ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ለማሳደግና ማህበረሰቡን በክህሎት ለማብቃት ያለመ ሲሆን፣ ኮሌጁ ወደ ወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማቅናት የመማር ማስተማሩን ሂደት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
# # # የፕሮግራሙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* **የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፦** በዕለቱ የኮሌጁ ትምህርትና ስልጠናና ም/ዲን እና ህዝብ ግንኙነት በጋራ በመሆን ለትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ስለ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊነት እና ስለ ስልጠናው ይዘት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
* **የትብብር መንፈስ፦** የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ከተማሪዎችና መምህራን ጋር የነበረው የእርስ በእርስ ውይይት ለቀጣይ ስልጠናዎች ስኬታማነት ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል።
* **የተግባር ቁርጠኝነት፦** የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትውልድ ለመገንባትና የዲጂታል አማራ እቅድን ከግብ ለማድረስ የተያዘው ጉዞ በተስፋ መጀመሩን ያበሰረ ሆኗል።
፨ የንቅናቄ ሳምንት ማስጀመሪያ ፕሮግራም መምህራንና ተማሪዎች የዘመኑን የቴክኖሎጂ እድገት ተረድተው በስልጠናው በንቃት እንዲሳተፉ በር የከፈተ ሆኗል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ28ኛ ዙር ለውጭ ሀገር  የስራ  ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ222 ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
18/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ28ኛ ዙር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ222 ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የከሚሴ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ27ኛው ዙር የውጭ ሀገር ስምሪት ሰልጣኞች የብቃት ምዘና (CoC) እያካሄደ ነውየፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ27ኛ ዙር ወደ ውጭ ሀገር ለሚሰማሩ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት...
07/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ27ኛው ዙር የውጭ ሀገር ስምሪት ሰልጣኞች የብቃት ምዘና (CoC) እያካሄደ ነው
የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ27ኛ ዙር ወደ ውጭ ሀገር ለሚሰማሩ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት የሙያ ብቃት ምዘና መስጠት ጀመረ። በዚሁ የሲኦሲ (CoC) ምዘና ላይ በቤት አያያዝ (Housekeeping) እና በምግብ ዝግጅት (Food Preparation) የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ 169 ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ምዘናው ሰልጣኞች በቆይታቸው የቀሰሙትን ቲዎሪያዊና ተግባራዊ እውቀት በተገቢው መንገድ መገንዘባቸውን ለማረጋገጥ የታለመ ሲሆን፣ ብቃታቸውን ባረጋገጡ ሰልጣኞች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተከናወነ ይገኛል።
**የኮሌጁ የት/ት ስልጠናና ም/ዲን አቶ አሸናፊ አበራ እንደገለፁት
* ሰልጣኞቹ በውጭ ሀገር የሥራ ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል ስልጠናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ሲሰጥ ቆይቷል።
* የአሁኑ ምዘና ሰልጣኞቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠበቀውን የሙያ ስታንዳርድ ማሟላታቸውን የሚመዝን ነው።
ይህ የምዘና ሂደት ሲጠናቀቅ ብቃታቸውን ያረጋገጡ ሰልጣኞች በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እንዲሰማሩ የሚደረግ ይሆናል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 29/08/2018 ዓ.ም ለመደበኛ እና ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ማለትም  በግብርና ዘርፍ በሰብል ልማት፣ በእንሰሳት እርባታእና በዶሮ እርባታ፣ በኮንስትራክ...
07/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 29/08/2018 ዓ.ም ለመደበኛ እና ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ማለትም በግብርና ዘርፍ በሰብል ልማት፣ በእንሰሳት እርባታእና በዶሮ እርባታ፣ በኮንስትራክሽን ፣ በፈርኒቸር ስራ እና በICT ዘርፍ ለሰልጣኞችና ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሲ ኦ ሲ (coc) ምዘና እየሰጠ ይገኛል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  የጡብ ማምረቻ ቴክኖሎጅ  በኮንስትራክሽን  አሰልጣኝ በእንዳለ ተሾመ የዲዛይንና የምርት ስራን እና የብረት ስራውን በማነፋክቸሪን ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ጋር በጋ...
07/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጡብ ማምረቻ ቴክኖሎጅ በኮንስትራክሽን አሰልጣኝ በእንዳለ ተሾመ የዲዛይንና የምርት ስራን እና የብረት ስራውን በማነፋክቸሪን ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ጋር በጋራ በመሆን ቴክኖሎጅውን በመስራት የምርት ስራውን የሙከራ ሂደት በመፈተሽ በስኬት በማጠናቀቅ ለተጨማሪ የምርት ስራ ዝግጁ ከመሆኑም በላይ ። የጡብ ማምረቻ ቴክኖሎጅው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለውን የግብአት ችግር ከመቅረፍ ባለፈ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ እራሳቸውንና አገርን እንዲጠቅሙ ተጨማሪ እድል የሚፈጥር ቴክኖሎጅ ሆኗል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ለ26ኛ ዙር ለውጭ ሀገር  የስራ  ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 147 ሰልጣኞች  የሲ,ኦ,ሲ (coc) ምዘና በመስጠት ላይ...
17/04/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ለ26ኛ ዙር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 147 ሰልጣኞች የሲ,ኦ,ሲ (coc) ምዘና በመስጠት ላይ ይገኛል

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ለ27ኛ ዙር ለውጭ ሀገር  የስራ  ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ165 አሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል
17/04/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ለ27ኛ ዙር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ165 አሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአልማ (ከአማራ ልማት ማህበር) ከዩኒሴፍና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ መሰረት በቀበሌ ለተመለመሉ በእንጀራ መጋገር ፣ በፈሳሽ በሳሙና፣ በባልት...
14/04/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአልማ (ከአማራ ልማት ማህበር) ከዩኒሴፍና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ መሰረት በቀበሌ ለተመለመሉ በእንጀራ መጋገር ፣ በፈሳሽ በሳሙና፣ በባልትና ውጤየቶች፣ በበግና ፍየል ማድለብ ስራ ለሚሰማሩ ለአምሳ (50) ሰልጣኞች የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተከታታይ አስር ቀን ስልጠና ከሰጠ ቡሃላ የአልማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አዲሱ ንጉሴ የስራ መመሪያ በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 2/07/2018 ዓ ም በፀረ ኤድስ ፈንድ አባላት መዋጮ ድጋፍ ለሚደረግላት ህፃን ፋጡማ አህመድ ቤተሰብ የከሚሴ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ እና...
11/03/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 2/07/2018 ዓ ም በፀረ ኤድስ ፈንድ አባላት መዋጮ ድጋፍ ለሚደረግላት ህፃን ፋጡማ አህመድ ቤተሰብ የከሚሴ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ እና የመጠለያ ችግር ላለባቸው የከተማው ማህበረሰብ በሰጠው የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ ላይ የተጀመረውን የመኖሪያ ቤት ግንባታን የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ40000 (ከአርባ ሺህ ብር) በላይ ወጭ በማድረግ የማቴሪያል ግዥ በመፈፀም እና የኮሌጁን ማህበረሰብ በማስተባበር የሙያ የግንባታ ድጋፍ በማድረግ የውሃ ልክ የማሰርና የውስጥ ወለል ሊሾ በመስራት የመኖሪያ የቤት ችግርን እንዲቀረፍ በማድረግ ማህበራዊ ግዴታውን ከመወጣቱም በላይ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት እንደ ማሳያ አድርጎ ይመለከተዋል።

Address

Kemise

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251913666962

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kemissie Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Kemissie Polytechnic College:

Share