05/08/2022
በውጣ ውረድ ውስጥ የታለፈ አስር ወርቃማ አመታት!!
በምዕራብ ኢትዮጵያ መልከዓ ምድር አሸብርቃ፤ የኦሮምያን ውብ ገፅታ በተላበሰው ጋራና ሸንተረር ተከባ የዓለም እስትንፋስ በሆነው ጥቅጥቅ ደን መሀል ተፈጥሮ አዳልቶ ያስቀመጣት የኢሉአባቦር እምብርት ላይ የዛሬ አስር ዓመት የሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሆነው መቱ ዩኒቨርሲቲ ተቆረቆረ!!
በኢትዮጵያ የመቻቻል ተምሳሌት፣ሰላምና አብሮነትን ለመጣባት ሁሉ በተግባር የምታስተምረው ኢሉአባቦር እጅዎችዋን ዘርግታ ወደ ዩኒቨርሲቲው የመጣውን ማህበረሰብ ተቀብሎ አስተምሮ ማሳደርን በተግባር ያሳየባቸው አስር ወርቃማ አመታት!!
በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ባለፈው በዚህ ግዙፍና የዞኑ አርማ በሆነው ተቋም ውስጥ እድሜያቸውን ከፍለው ለዛሬው የዓስር ዓመታት ጉዞ ስኬት ዋልታ ለሆኑት ሁሉ የማይለካ ክብር ይድረሳቸው!!
በመጣበት ጉዞ ሁሉ ችግሮችን ተሸክመው የፊት ለፊቱን መዳረሻ በማለም ወደፊት እንዲጓዝ የራሳቸውን አሻራ ላሳረፉት የተቋሙ ቀደምት ዓመራሮች በሙሉ ምስጋናቸው አይዘነጋም!!
ወቅቱ የለውጥ ሰዓት በነበረበት ጊዜ ወደ አመራር ስትመጣ የማንረሳቸውንና ትዝታ የሆኑንን ፈተናዎች ለማለፍ ባለህ በሳል የዓመራር ጥበብና ትዕግስት የማይታለፉ የሚመስሉ ቀናቶችን አሻግረህ የዛሬዋ ቀን ላይ ላደረስከው ውዱ የተቋሙ ፊት-አውራሪ የሆንከው ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ ፤
ለኔ ደግሞ መካሪዬ፣ታላቄ፣መከታዬ የሆንከው ውድ ወንድሜ እንኳን ለ10ኛው ዓመት ክብረ በዓል አደረሰህ!!
ባጠቃላይ እንግዳን ተቀብሎ በአብሮነትና በመቻቻል መኖር ምን እንደሚመስል በተግባር በማሳዬት የኢትዮጵያ ፋና ወጊ ለሆናችሁ ለኢሉአባቦር ህዝቦች በሙሉ እንኳን ለመቱ ዩኒቨርሲቲ 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል አደረሳችሁ!!