11/08/2024
የአቡዬ ልጅ ታምራት ቶላ
ሰሜን ሸዋ ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ከ110 አመት በላይ እድሜ አለው። በአሁኑ ወቅት ምዕመናኑ በአፈር የተሰራውን ቤተክርስቲያን በአዲስ መልክ እያስገነቡት ይገኛሉ። አንዱ አስተባባሪና አጋዥ ደግሞ ታምራት ነው።
ታምራት ቶላ ትውልድና እድገቱ ሰሜን ሸዋ ፥ አለልቱ ወረዳ ሉባዬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው። አትሌቱ በማራቶን ሀገራችንን በተደጋጋሚ ወክሎ ውጤታማ ሆኗል። በኦሪገን ወርቅ ፣ በለንደን አለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ በሪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያን አጥልቋል፤ በግማሽ ማራቶንና በሀገር አቋራጭም ስኬታማ ነበር።
ታምራት የተወለደበትን ቀዬ የማይረሳ በመንፈሳዊ ህይወቱም ጠንካራ መሆኑ ይነገርለታል። እንደ አዲስ ለሚገነባው የአቡዬ ቤተክርስቲያንም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ተብሏል።
በዚሁ አካባቢ ልምምድ ሲሰራና፣ ሲፀልይ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ግንባታ በቅርበት እንደ ባለቤት ሲከታተል እንደነበር ሰምተናል፤ የአካባቢው ማህበረሰብም ታምራትን "የአቡዬ ልጅ" ብለው ይጠሩታል።