መገን ታይምስ Megen Times

መገን ታይምስ Megen Times በዚህ ፔጅ ስለ አማራነት ይቀነቀናል

03/09/2022
12/08/2022

"ወሎ አማራ ያልሆነ ማን አማራ ሊሆን ነው???
ስለ ወሎ እንሞግታለን ምክንያቱም ዉሸት ሲደጋገም እዉነት ይሆናል እንዲሉ የዋሾዎች ጩኸት እንደ እዉነት ሆኖ ከመቆጠሩ በፊት እዉነቱን መናገር ተገቢ ነዉ፡፡ እንግዲህ ቀደም ብሎ የነበረዉ የወሎ ጠቅላይ ግዛት 12አዉራጃዎች ነበሩት፡፡

እነሱም ደሴ ዙሪያ አዉራጃ፣ ወረሂመኖ አዉራጃ፣ ወረኢሉ አዉራጃ፣ቦረና አዉራጃ፣ ቃሉ አዉራጃ፣ ዋድላ ደላንታ አዉራጃ፣ አምባሰል አዉራጃ፣ የጁ አዉራጃ፣ ላስታ አዉራጃ፣ ራያና ቆቦ አዉራጃ፣ ዋግ አዉራጃ እና አዉሳ አዉራጃ ነበሩ፡፡

ወሎ ጠቅላይ ግዛት ወሎ የሚለዉን ስያሜ ያገኘዉ በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን በሰፈረዉ የወሎ ኦሮሞ ነገድ ነዉ፡፡
በዚህም የተነሳ አብዛህኞቹ የወሎ ጠቅላይ ግዛት የኦሮምኛ ስያሜዎች አሏቸዉ፡፡

የወሎ ጠቅላይ ግዛት አዉራጃዎች የቀድሞ ስያሚያቸዉ ላኮምልዛ፣ ቤተ-አማራ፣ አንጎት፣ ምድረ ገኝ ...እና የመሳሰሉት እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡
በ1983 ዓ.ም የመንግስት ለዉጥ በኋላ ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ አብዛህኛዉ የአዉሳ አዉራጃ ክፍል ወደ አፋር ክልል፣ አብዛህኛዉ የራያ ክፍል ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል ተካሏል (ራያ ያለ ህዝቡ ፈቃድ ቢሆንም የተካለለዉ)፡፡

ቀሪዉ የወሎ ክፍል ሰሜን ወሎ ዞን እና ደቡብ ወሎ ዞን ተብሎ የተደራጀ ሲሆን የዋግ አዉራጃ ራሱን ችሎ በብሄረሰብ ዞን የተደራጀ ሲሆን ጥቂት የኦሮሞ ተናጋሪዎች 5 ወረዳዎችን ይዘዉ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ተደራጅተዋል፡፡

ወሎ ማን ነዉ? የሚለዉን ለማየት ከተፈለገ እያንዳንዱ ሰዉ በቀረበለት መለኪያ ማን ነኝ ይላል? የሚለዉን ማየት ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ የብሄራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም ባደረገዉ ህዝብ እና ቤት ቆጠራ የህዝብ ስብጥሩን (Demography)ማየት ጠቃሚ ይሆናል፡፡

እዚህ ላይ የወሎ ህዝብ የሚቀርብለት መስፈሪያ አካባቢያዊ ማንነት እና ዜግነት ብቻ ከሆነ አንድ የወሎ አካባቢ ሰዉ “አንተ ማን ነህ?” ስትሉት “ወሎየ ከዚያ ኢትዮጵያዊ”ይላችኋል፡፡ መስፈሪያዊ ብሄርን ከጨመረ ግን ብሄሩን አስረግጦ ይነግራችኋል፡፡ እስቲ የብሄራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም ባደረገዉ ህዝብ እና ቤት ቆጠራ የህዝብ ስብጥሩን ወሎ ዉስጥ ምን እንደሚመስል እንደሚከተለዉ እንይ፦

1. ደቡብ ወሎ ዞን፡ በብሄር ስብጥር፤ አማራ 99.33%፣ ሌሎች 0.67%፤በአፍ መፍቻ ቋንቋ፤ አማርኛ 98.65%፣ሌሎች 1.35%።

2. ሰሜን ወሎ ዞን፡ በብሄር ስብጥር፤ አማራ 99.38%፣ ሌሎች 0.62%፤በአፍ መፍቻ ቋንቋ፤ አማርኛ 99.28%፣ሌሎች 0.78%

3. ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፡ በብሄር ስብጥር፤ አማራ 78.54%፣ ኦሮሞ 20.07%፣ ሌሎች 1.39%፤
በአፍ መፍቻ ቋንቋ፤አማርኛ 77%፣ ኦሮምኛ 22.02%፣ ሌሎች 0.88%

4. ዋግህምራ ብሄረስብ ዞን፡ በብሄር ስብጥር፤ አገዉ 52.92%፣ አማራ 45.45%፣ ትግሬ 1.39%፣ሌሎች 0.24%፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋ፤ አማርኛ 56.27%፣ ህምጥኛ 41.82%፣ትግሪኛ 1.67%፣ ሌሎች 0.24%

እንግዲህ ቀደም ብየ እንደገለጽኩት አንድ ወሎየን አንተ ባቀረብክልት መስፈሪያ ማንነቱን ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጥልሀል፡፡ እንግዲህ አማካይ ወሎን የህዝብ ስብጥር በብሄር ወስዳችሁ ብታዩት ወሎ አማራ ለመሆኑ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም፡፡ ከ94% በላይ አማራ ነኝ የሚል እና በአማርኛ አፉን የፈታ ህዝብ ባላበት ወሎ፤ ወሎ አማራ ካልሆነ ማን አማራ ሊሆን ነዉ?
ለዚያም ነዉ ህዝቡን ሂዳችሁ ጠይቁት የምለዉ፡፡

Address

Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መገን ታይምስ Megen Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share